By using this site, you agree to the Privacy Policy and Terms of Use.
Accept
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ሾለ እኛ
Reading: “ቅዱስ ጊዮርጊስን ሳይጠቅሙ እንጠቅማለን ብለው የሚያስቡ አንድም ነገር ለክለቡ ሳይሰሩ ስድባቸው ከምንም ነገር የበረታብን የፌስቡክ አርበኞች አሉ”አቶ ዳዊት ውብሸት /የቅ/ጊዮርጊስ የቦርድ አባል/
Share
Notification Show More
Latest News
ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዜናዎች የኢትዮጵያ እግርኳስ ዳኞች ማህበር
በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ኢትዮጵያ ቡና ዜናዎች
አርባምንጭ ከተማ ሴኔጋላዊ አማካይ አስፈረመ
ዜናዎች አርባምንጭ ከተማ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች
አርባምንጭ ከተማ ጋናዊ አጥቂ አስፈረመ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ዜናዎች አርባምንጭ ከተማ
የ22ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዜናዎች የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
Aa
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
Aa
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ሾለ እኛ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ሾለ እኛ
Have an existing account? Sign In
Follow US
  • Advertise
Š 2023 Hatrick Spoert. Design by Tech-ethiopia.com All Rights Reserved.
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግዜናዎችቅዱስ ጊዮርጊስቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ

“ቅዱስ ጊዮርጊስን ሳይጠቅሙ እንጠቅማለን ብለው የሚያስቡ አንድም ነገር ለክለቡ ሳይሰሩ ስድባቸው ከምንም ነገር የበረታብን የፌስቡክ አርበኞች አሉ”አቶ ዳዊት ውብሸት /የቅ/ጊዮርጊስ የቦርድ አባል/

ዮሴፍ ከፈለኝ
ዮሴፍ ከፈለኝ 2 years ago
Share
SHARE

👉”ቅዱስ ጊዮርጊስን ሳይጠቅሙ እንጠቅማለን ብለው የሚያስቡ አንድም ነገር ለክለቡ ሳይሰሩ ስድባቸው ከምንም ነገር የበረታብን የፌስቡክ አርበኞች አሉ”

👉”የገጠመን ፈተናና ተግዳሮት ቢያሳዝነኝም ፈተናውን አልፈን ቡድኑን ውጤታማ ማድረጋችን አስደስቶኛል”

👉” ቅዱስ ጊዮርጊስ ከተቋቋመ ጀምሮ እንደ ባለፉት ሁለት አመታት በፈተናና በመከራ ያለፈበት አመት የለም…”

አቶ ዳዊት ውብሸት
/የቅ/ጊዮርጊስ የቦርድ አባል/

- ማሰታውቂያ -

ቅዱስ ጊዮርጊሶች ነገ ጠዋት በስካይላይት ሆቴል መግለጫ ጠርተዋል….ጳጉሜ 4/2015 ስለተጠናቀቀው ፕሮግራም ስኬትና ስለቀጣዩ ስራቸው ለመገናኛ ብዙሃን ለማብራራት መሆኑን መገመት ይቻላል ….የቦርድ አባሉና የገቢ አሰባሳቢ ኮሚቴ አስተባባሪው አቶ ዳዊት ውብሸት ደግሞ በአጠቃላይ ቅዱስ ጊዮርጊሳዊ ጉዳይ ከሀትሪክ ድረገጽ ባልደረባ ዮሴፍ ከፈለኝ ጋር በነበራቸው ቆይታ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ተገቢ ነው ያሉትን ምላሽ ሰጥተዋል…

ሀትሪክ:- አመሰግናለሁ …ለቃለ ምልልሱ….ጳጉሜ 4/2015 የተጠናቀቀው ፕሮግራም ስኬታማ ነበር..?

ዳዊት:- አዎ በጣም ስኬታማ ነበር…. አቅደን የተነሳነው 4 ሚሊዮን ብር ማግኘት ነበር ከፍ ካለ ደግሞ ወደ 5 ሚሊዮን ብር መሰብሰብ ነበር ..በመጀመሪያው ቴሌብርና በንግድ ባንክ 2.6 አካባቢ ተገኘ….ከዚያም ሰው ሁሉ በሚፈልገው መንገድና ባለው አቅም ገንዘቡን ሲያስገባ ቆየ…ይሄም ጥሩ ነበር ነገር ግን መጠኑን በሚፈለገው መንገድ ከፍ አላደረገውም… ከማን አንሼ ደጋፊዎች ማህበር 4ኛ አመቱን ሲያከብር እኛን ማገዝ አላማም ነበረውና ከመጡት ሰዎች 980 ሺህ ብር ተሰበሰበና ገቢውን ወደ 3.5 ሚሊየን ብር አደረሰው

ሀትሪክ:- የሴቶች ደጋፊዎቹ የአበባዮሽ ጭፈራስ…?

ዳዊት:– የክለባችን ደጋፊ የሆኑ ሴት ደጋፊዎች ገቢ ያላቸው አቅም አላቸው የተባሉ ጋር ሄደው ጨፍረው ከበአሉ አንድ ቀን በፊት ወደ 386 ሺህ ብር አካባቢ ሰበሰቡና አጠቃላይ ገቢውን 4.2 ሚሊዮን ብር እንዲሞላ አደረገው …

ሀትሪክ:- የሀገር ፍቅሩ ሲምፖዚየምስ…?

ዳዊት:- አዎ …ሀገር ፍቅርም በተካሄደ የስነጥበብና የመጽሀፍት ሲምፖዚየም ላይ ደጋፊዎቹ በክለባችን
ጽ/ቤት የነበረው አይዲ ፕሪንተር ተበላሽቶ ስለነበር አዲስ ሙሉ ማሽን ከሚያስፈልገው ነገር ጋር የተሟላ ገዝተው አስረከቡ …በአይነት ይሁን እንጂ ከመቶ ሺህ ብር በላይ ነው የወጣበት… ይህ ሲጨመር በትልቁ 5 ሚሊዮን ብለን 5 ሚሊዮን ብር በላይ ስለሚሆን እንደ ዕቅድ ስኬታማ ነበርን በዚህም ተደስተናል… በቁጥር ካየነው ከ100 ፐርሰንት በላይ ተሳክቷል ለዚህ በስራው ላይ የተባበሩትን በገንዘብ ያገዙትን በሙሉ አመሰግናለሁ

ሀትሪክ:- ቀጣይ ምን የታሰቡ ነገሮች አሉ…?

ዳዊት:- ጳጉሜ 4/2015 የተጠናቀቀውን ፕሮግራም በተመለከተ ሪፖርት ካቀረብን በኋላ ሳንቆይ ወደ ሁለተኛው ምዕራፍ እንሻገራለን… ቀጣይ ምዕራፍ 2000 ለሚሆኑ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎችና ለስፖርት ቤተሰቡ ብቻ የተዘጋጀ ፕሮግራም አለ… በዚህም ጥሩ ስኬት ይገጥመናል ብለን ተስፋ እናደርጋለን። ሶስተኛው የታሰበው ደግሞ ኮንሰርት ነው ነገር ግን የሀገሪቷ ሁኔታ እንድናዘጋጅ አላደረገንም… ከዚህም ኮንሰርት ከ5-10 ሚሊዮን ብር እንጠብቃለን… የመጨረሻው ውድድር ለማካሄድ አቅደናል …እነ ሲምባንና ሌሎች ታሪካዊ ክለቦችን አምጥተን በቶርናመንት ለማጫወት አስበናል…. ይሄ ደግሞ የአዲስ አበባ ስታዲየም ካለቀ የምናደርገው ይሆናል… ወደ አምስት ጨዋታ አድርገን በየጨዋታው ገቢ ለማግኘትና የምንወደውን ክለብ ለማገዝ አቅደናል… እያንዳንዱ ደጋፊ ባለበት የሚያዘጋጀው የገቢ ማሰባሰቢያ ስለሚኖር አጠቃላይ ገቢውን ለክለቡ በመስጠት የወጪውን አንድ ሶስተኛ ብንሸፍን ትልቅ ድጋፍ ይሆናል… ሌላው ከስፖንሰርና ሌሎች ዝግጅቶች ቢሸፈን አመርቂ ሾል መስራታችንን ማሳየት የምንችለው ይሆናል…

ሀትሪክ:-ክለቡን በደንብ እንደሚያውቅ ደጋፊ …እንደ ቦርድ አባልነት …ቅዱስ ጊዮርጊስ እዚህ ደረጃ በመድረሱ ምን ይሰማሀል..?

ዳዊት:- በጣም አዝኛለሁ ….ጥሩ ስሜት አልተሰማኝም ..
ነገር ግን ቅዱስ ጊዮርጊስ በውስጥም በውጪም ፈተና ገጥሞት ፈተናውን እያለፈ እዚህ የደረሰ ክለብ ነው… ከፖለቲካ አንጻር ከአሸናፊነቱ አንጻር ለምን አሸናፊው ሆነ በሚል ተግዳሮቶች ሲገጥሙት ኖሯል…. በአቶ ይድነቃቸው ጊዜ አልፎ ደርግን አልፈን በኢህአዴግ የደረሰብን ነገር የሚታወቅ ነው… ሽጉጥ ጠረጴዛ ላይ ተቀምጦ ታሸንፉና የምንባልበት፣ ተከበንም አንድ ሰው እስቲ እዚህ ይገባል ትሞታላችሁ ተብሎ ምን እንደደረሰብን በዛቻ አስፈራርተውንም አልፈናል…. ይሄ ሁሉ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው…. ጅማ ላይ የተከሰተው ችግር የተፈጠረብንን ጊዜ አልፈናል ….ተግዳሮቶች ነበሩ … እነዚያ ተግዳሮቶች ምክንያታቸውንና ፍላጎቶችን ቀድመን ስለምናውቅ በርጋታ በይደር ስናልፍ ኖረናል ….ባለፉት አመታት ግን ….

ሀትሪክ:- ባለፉት አመታት ከቀድሞዎቹ የተለየ ፈተና ነው ማለት ይቻላል.?

ዳዊት :-አዎ ባለፉት ሶስት አመታት የመጣነው ተግዳሮት ካላሰብነው አቅጣጫና ባልተዘጋጀንበት ጊዜ መሆኑ ይለያል …. እንዲህ አይነት ነገር በክለባችን ላይ ይፈጠራል ብሎ የሚያስብ አንድም ሰው አልነበረም ዝግጅትም አልነበረንም ድንገት እንደ ዱብዕዳ ነው የመጣው… ያ ደግሞ ይመጣል ይከፈለናል ብለን የምን ጠብቀው ክፍያ ባላገኘንበት ጊዜ መሆኑ አልጠበቅንም ይመጣል ያልነው ሲቀር በተጨማሪ ይቀጥላል ያልነው ስፖንሰርሺፕ ሲቀር የሚያመጣው ተጽዕኖ ከባድ ሆኖብናል … እውነት ለመናገር ቅዱስ ጊዮርጊስ ከተቋቋመ ጀምሮ ከቢራ ፋብሪካው ወጥቶ በራሱ ህዝባዊ ሆኖ ከመጣበት ጊዜ አንስቶ እንደ ባለፉት ሁለት አመታት በፈተናና በመከራ ያለፍንነት አመት የለም… በፊት ከነበሩት ቀድመን ከምንረዳቸው ተግዳሮቶች አንጻር የባለፉት አመታት ይለያሉ ከአቅም በላይ ሆኖብኗል ይሄ በመፈጠሩ በግሌ አዝኛለሁ መፈጠር ያልነበረበት መሆን ያልነበረበት ቢቻል ደግሞ ከክለቡ ጋርም ባይያያዝ ደስ ይለኝ ነበር

ሀትሪክ:- ግን ውጤታማ ነበራችሁኮ..?

ዳዊት:- ባለፉት ሁለት አመታት ከሜዳ ውጪ በተፈጠረው ነገር በገጠመን ፈተና ብከፋም ሜዳ ውስጥ ያገኘነው ስኬት ግን መጽናኛዬ ሆኗል፣ ያን ቻሌንጅ ከቦርድ ጓደኞቼ ጋር ተጋፍጩ ሁለት ተከታታይ አመታት የሊጉ ሻምፒዮን መሆናችን አሁን ደግሞ ለሶስተኛ ተከታታይ አመት ሻምፒዮን ለመሆን የሚንደረደር ቡድን መስራት ያስደስተኛል …ዋጋ እየከፈልን እየተፈተን ሻምፒዮን መሆን ደስ ይላል…. ባለፉት ሁለት አመታት በግል ስራዬ በቢሮዬ የሰራሁት ብትፈልግ አታገኝም …ሙሉ ጊዜዬን ለምወደው ክለብ ሰጥቻለሁ …እኔ ብቻ ሳልሆን የቦርድ አመራሮቹ ጉልበታችንን፣ እውቀታችንን፣ ጊዜያችንና ገንዘባችንን ጨምሮ የምንችለውን ሁሉ አድርገናል… አንዳንዴ ሁሉ ነገር ተደርጎ የሚፈለገው ተገኝቶ ውጤት ላይሳካ ይችላል ከአቅም በላይ የሆነ ወጪ አውጥተው የት ጋር እንዳሉ ሳይታወቅ የጨረሱ አሉ… ድሮ አቅም በነበረን ሰአት የምናረጋቸውን ነገሮች ምንም ሳይኖረን ለማሸነፍ መብቃት ሌላ የሚያስደስት ነገር ሆኖልናል። የገጠመን ፈተናና ተግዳሮት ቢያሳዝነኝም ፈተናውን አልፈን ቡድኑን ውጤታማ ማድረጋችን አስደስቶኛል

ሀትሪክ:- ሁለተኛውስ..?

ዳዊት:- ሁለተኛውማ ተጋጣሚያችን አል አህሊ ነገ የዋንጫ ጨዋታ አለበት… /ቃለምልልሱ የተደረገው ሃሙስ ማታ ነው/ ለጨዋታው ሲባል የኛ ጨዋታ በአንድ ሳምንት እንዲገፋ ተደረገ… በ16 የነበረው ጨዋታ ወደ 24 ተገፋ…. በ24 ተጫውተን መልሱ በ29 ነው ለሁለተኛው ጨዋታ መቼ ተዘጋጅተን መቼ ከድካም አገግመን ልንጫወት ነው..? በበረራ ብቻ ጊዜውን ልንጨርስ ነው ይህን ከግምት አስገብተን ውሳኔውን ወስነናል… በነገራችን ላይ እውነቱን እንነጋገር ከተባለ እስከ ረቡዕ ድረስ ካፍ ይሄ ሜዳ ተፈቅዷል ብሎ የሰጠው ወረቀት የለም… ክለባችንን ከከባድ ሪስክ ነጻ ያደረገ ውሳኔ እንደወሰንን ነው የሚሰማን….

ሀትሪክ:- ከአልአህሊ ጋር ምን አይነት ውጤት ይጠበቃል..?

ዳዊት:- ወደ ካይሮ የምንጓዘው ብርቱ ተፎካካሪ ሆነን የምንችለውን ለማድረግ እንጂ 100 ፐርሰንት አልአህሊን አሸንፈን ወደ ቀጣዩ ዙር እናልፋለን የሚል ነገር የለኝም ምክንያቱም ባለን አቅም አንገናኝም ከሰሞኑ ከቦሩሲያ ዶርትሙንድ ተጨዋች ገዝተዋል …ወደ 8 የሚጠጉ ፕሮፌሽናል ተጨዋቾች አሏቸው… እነሱ ከእኛ ጋር ለመጫወት አይደለም የሚዘጋጁት.. ..በሌላ ከፍታ ላይ ያሉ ናቸው.. ..በርካታ ተጨዋቾች ለቀውብናል ጨዋታ ተደራርቦባቸው ተዳክመው የመጡ፣ ወጣቶችና የውጪ ጨዋታ ልምድ የሌላቸው ወጣቶች ናቸው ይሄ በገሀድ የሚታይ ልዩነታችን ነው… ከነሱ ጋር መጫወታችን ለኛ እድል ነው… ተፎካካሪ መሆናችንን የምናሳይበት ጨዋታ ነው። ደረቴን ነፍቼ አልአህሊን አሸንፈን መቶ ፐርሰንት ወደ ቀጣዩ ዙር እናልፋለን ማለት አልችልም… ተፎካካሪ ሆነን ግጥሚያዎቹን አድርገን ልምድ ቀስመን እንመጣለን ብለን ስንነሳ ክለቡን አዘቅት ውስጥ መክተት የለብንም…ክለቡ ምንም ወጪ በሌለበት ከዕዳ ነጻ ሆኖ የሚደረግ ግጥሚያ መሆን አለበት ብለን ስለሆነ በውሳኔያችን የምጸጸትበትም ሆነ የማዝንበት ምክንያት የለም…
ሾለ ጨዋታው ካነሳን በሜዳችን ብንጫወት የመጀመሪያ አድቫንቴጃችን ደጋፊያችን ሁለተኛው ደግሞ የአየር ንብረት ነው… ሜዳ ግን የለንም እንደሀገር ስደቱን ተቀብለን እስከተሰደድን ድረስ ይህንንም መቀበል የግድ ይላል…የጨዋታዎቹ ውጤት ምንም ይሁን በጸጋ ተቀብለን በቀጣዩ አመት ተዘጋጅተምን እንሄዳለን..

ሀትሪክ:- የመጨረሻ ቃል…?

ዳዊት:- ማስተላለፍ የምፈልገው ነገር አለ….. ካፍ ምን ያደርጋል ..? የፌዴሬሽኑ የሃላፊነት ደረጃ የት ድረስ ነው..? የቅዱስ ጊዮርጊስ አካሄድ ምን ይመስላል..? የሚለውን እንደኳስ አዋቂ ጠንቅቆ ማወቅ ይገባል….ሁሉም ደጋፊ ማወቅ አይጠበቅበት ይሆናል… ሆኖም አንዳንዴ አንዱ ህጉን ባለማወቁ በትክክል ባለመገንዘብና የሚመጣውን ጫና ባለመረዳት የተለያየ ነገር ሊወራ ይችላል…ቅዱስ ጊዮርጊስን ሳይጠቅሙ እንጠቅማለን ብለው የሚያስቡ አንድም ነገር ለክለቡ ሳይሰሩ ስድባቸው ከምንም ነገር የበረታብን የፌስቡክ አርበኞች አሉ ይህችን ነገር ሲጠብቁ ስለነበር የገንዘብ ስብሰባው ስለተሳካልን በሱ ስላዘኑ ጨዋታው ወደ ካይሮ የዞረበትን ምክንያት ሳይረዱ ጫፍ ብቻ ይዘው ህዝቡንና ደጋፊውን ለማዋከብ የሚያደርጉትን ተግባር ማቆም አለባቸው። የፈለገ የእግርኳስ አዋቂ ይምጣ ከወሰነው የተለየ አይወስንም። በብዙ አንግል አይተን ብዙ ጊዜ ወስደን የወሰድነው ውሳኔያችን በመሆኑ አንጸጸትም ያም ሆኖ ግን አካሄዱ ላይ አለ የተባለ ስህተት ካለ ለመነጋገር ዝግጁ ነን….

You Might Also Like

ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ

በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?

አርባምንጭ ከተማ ሴኔጋላዊ አማካይ አስፈረመ

አርባምንጭ ከተማ ጋናዊ አጥቂ አስፈረመ

የ22ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

Share this Article
Facebook Twitter Email Print
By ዮሴፍ ከፈለኝ
Follow:
Editor at Hatricksport
Previous Article የኢንስትራክተር ዳንኤል ገ/ማሪያም የ90 ቀናት የዋሊየዎቹ ቆይታቸው ተጠናቋል…
Next Article ቅዱስ ጊዮርጊስና ጸሃይ ባንክ በጋራ ለመስራት ተስማሙ….

Follow US

Find US on Social Medias
127k Like
2.9k Follow
1.6k Follow
19.7k Follow

Weekly Newsletter

Subscribe to our newsletter to get our newest articles instantly!

ተነባቢ ዜናዎች
ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣዜናዎች

ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች

hatricksport team By hatricksport team 5 years ago
ሀትሪክ በነገው እትሟ ባለቀለሟሟዋ እና ሳምንታዊዋ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ነገም እናንተን በእትሟ ልታገኞት ስራዋን አጠናቃለች፤ ሀትሪክ በነገው እትሟ ምን ምን ጉዳዮችን ይዛ ወጥታ ይሆን፤
አሰልጣኝ ሲሳይ አብርሃም ድጋፍ አድርገዋል
በቻምፒየንስ ሊግ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከሊዮፓርድስ ጋር ነገ የመልስ ጨዋታውን ያደርጋል
ዋልያዎቹ ከስብስባቸው አንድ ተጫዋች ቀንሰዋል
- Advertisement -
Ad imageAd image
Global Coronavirus Cases

Confirmed

0

Death

0

More Information:Covid-19 Statistics
about us

Phone: 0993808668 Email: [email protected] .

Find Us on Socials

Š Hatrick Sport 2023 All Rights Reserved.

Removed from reading list

Undo
 

Loading Comments...
 

    Welcome Back!

    Sign in to your account

    Lost your password?