ሻምፒዮኖቹ ፋሲል ከነማዎች ከዩጋንዳ ብሔራዊ ቡድን ጋር ሊያደርጉት የነበረዉ የአቋም መለኪያ ጨዋታ በነገዉ ዕለት በባህርዳር ስታዲየም እንደሚከናወን ተረጋግጧል።
አፄዎቹ ለመጀመሪያ ጊዜ በሚካፈሉበት የአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ ላይ የማጣሪያ ጨዋታቸውን ከመስከረም ወር ጀምሮ እንደሚያደርጉ ይታወቃል።
በመጀመሪያው ዙር የማጣሪያ ጨዋታ ከሱዳኑ አል ሂላል ጋር የተደለደለው ፋሲል ከነማ ከጨዋታው አስቀድሞ በነገዉ ዕለት የወዳጅነት ጨዋታዉን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን ለመግጠም ባህርዳር ከሚገኘዉ የዩጋንዳ ብሔራዊ ቡድን ከ20 በታች ማለትም ከሁለተኛዉ ቡድን ጋር እንደሚያደርግ ታዉቋል።
በፋሲል ከነማ በኩል ጨዋታዉን የፊታችን ማክሰኞ በ25/12/2013 ለማድረግ ሀሳብ ያቀረቡ ቢሆንም የዩጋንዳ ብሔራዊ ቡድን ሰኞ ዕለት ወደ ኬንያ ለመጓዝ ቀጠሮ በመያዙ ምክንያት ጨዋታዉ ወደ ነገ 9:00 ሰዓት ሊቀየር ችሏል።
አስተያየት ይስጡ