ሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ በ2015 ዓ.ም የኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች ፕሪሚየር ሊግ የዉድድር ዘመን ላይ ጥሩ አቋም አሳይተዋል ካላቸዉ የክለቡ ተጫዋቾች ዉስጥ መልምሎ 5 ልጆችን ወደ ዋናው ቡድን አሳድጓል።
በዚህም መሰረት ወደ ዋናዉ ቡድን የተከላካይ አማካይ የሆነዉ ፂዮን ተስፋዬ ፣ የአጥቂ ስፍራ ተጫዋች የሆነዉ ዳመነ ደምሴ ፣ የመስመር አጥቂ የሆነዉ የአብስራ አስደሳች ፣ የአጥቂ አማካይ የሆነዉ ፋሲል ጩኒሳ እና የግራ መስመር ተመላላሽ ተጫዋች የሆነዉ ምትኩ አስፋው ወደ ዋናው ቡድን አድገዋል።