መነሻ ገጽ አትሌቲክስ በ44ኛው የዓለም ሀገር አቋራጭ ሻምፕዮና ኢትዮጵያ 2ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀቀች
አትሌቲክስዜናዎች

በ44ኛው የዓለም ሀገር አቋራጭ ሻምፕዮና ኢትዮጵያ 2ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀቀች

አጋራ
አጋራ

44ኛው የዓለም ሀገር አቋራጭ ሻምፕዮና በዛሬው ዕለት በአውስትራሊያ ባትረስተ ከተማ ተደርጓል ።

በአምሰት የውድድር ዘርፎች በ28 አትሌቶች የተወከለችው ኢትዮጵያ በአጠቃላይ 2 የወርቅ 7 የብር እና 1 የነሀስ ሜዳልያ በማስመዝገብ የሁለተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቃለች ።

በዕለቱ በቀዳሚነት በተደረገው የድብልቅ ሪሌይ የ8 ኪ.ሜ ውድድር ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በ23:21 የኬንያ አትሌቶችን ተከትለው በሁለተኝነት አጠናቀዋል ።

በሴቶች ከ20 ዓመት በታች የ6 ኪ.ሜ ውድድር ሰናይት ጌታቸው በ20:53 በቀዳሚነት ስታጠናቅቅ መዲና ኢሳ በሰባት ሰከንዶች ዘግይታ የሁለተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቃለች ።

ለምለም ንብረት 5ኛ ፤ መሰረት የሻነህ 7ኛ ፤ ትነበብ አስረስ 8ኛ እንዲሁም መልክናት ውዱ 11ኛ ደረጃን በመያዝ ሲያጠናቅቁ በአጠቃላይ ድምር ውጤት በ15 ነጥቦች ኢትዮጵያ የቡድን አሸናፊ ሆናለች ።በወንዶች ከ20 ዓመት በታች የ8 ኪ.ሜ ውድድር ቦኪ ድሪባ በ24:31 የሶስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቋል ። በውድድሩ ኬንያውያኑ እስማኤል ኪፕሪኩይ እና ሬይኖልድ ቼሩዮት የአንደኛ እና የሁለተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀዋል ።

በረከት ዘለቀ 5ኛ አቤል በቀለ 7ኛ በረከት ነጋ 8ኛ ኩማ ግርማ 13ኛ እንዲሀም ይስማው ድሉ በ15ኝነት ውድድራቸውን ፈፅመዋል ።

በአዋቂ ሴቶች የ10 ኪ.ሜ ውድድር ኢትዮጵያ በፅጌ ገብረሰላማ አማካኝነት የብር ሜዳልያ አስመዝግባለች ። ፅጌ የገባችበት ሰዓት 33:56 ሲሆን ውድድሩን በቀዳሚነት ካጠናቀቀችው ኬንያዊቷ ቤትሪስ ቺቤቶ በስምንት ሰከንድ ዘግይታ ነው ።

በመድረኩ ተጠብቃ የነበረችው ለተሰንበት ግደይ ውድድሩን በቀዳሚነት ለማጠናቀቅ ተቃርባ የነበረ ቢሆንም ባጋጠማት ድንገተኛ ጉዳት ውድድሩን ለማቋረጥ ተገዳለች ። ፎቲን ተስፋይ 5ኛ ፤ ሀዊ ፈይሳ 6ኛ ፤ ጌጤ አለማየሁ 12ኛ እንዲሁም ውዴ ከፋለ 15ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድራቸውን አጠናቀዋል ።

በአዋቂ ወንዶች የ10 ኪ.ሜ ውድድር በሪሁ አረጋዊ በ29:26 የሁለተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቋል ። በውድድሩ ኡጋንዳዊው ዳኮብ ኪፕሊሞ በ29:17 በመግባት የወርቅ ሜዳልያ ባለቤት ሆኗል ።

ሀይለማርያም አማረ 9ኛ ፤ ሞገስ ጥዑማይ 10ኛ ጪምዴሳ ደበሌ 11ኛ ሰለሞን ባረጋ 12ኛ እንዲሁም ጌታነህ ሞላ በ14ኝነት ውድድራቸውን አጠናቀዋል ።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

ገዛኸኝ ደሳለኝ (ሸገር ከተማ) : ክለቡ ከ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረገው የ26ኛ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ በድል ሲቀጥሉ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋም አሸንፈዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን ወደ ቋቱ ሲከት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨዋታ ብልጫ...