የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አምበል የሆነዉ ሽመልስ በቀለ በአሰልጣኝ ስዩም ከበደ የሚመራዉን ሲዳማ ቡና ለመቀላቀል ከስምምነት ላይ መድረሱ ታዉቋል።
ከዚህ ቀደም በሀገር ውስጥ ለሀዋሳ ከተማ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ መጫወት የቻለዉ እንዲሁም በግብፅ ሊግ ለአስር አመታት ያህል መጫወት የቻለዉ የመሐል ስፍራ ተጫዋቹ ሽመልስ በቀለ ወደ ሀገር ቤት በመመለስ ሲዳማ ቡናን ለመቀላቀል ከስምምነት ላይ መድረሱ ሲገለፅ ፤ የቀረዉ ነገርም ተጫዋቹ በግብፁ ክለብ ENPPI ቀሪ የአንድ አመት ኮንትራት ስላለዉ በሁለቱ ክለቦች መካከል ያለዉ ስምምነት ይሆናል።
በዚህም የሁለቱ ክለቦች ድርድር በስምምነት ከተጠናቀቀ ሽመልስ በቀለ በይፋ ለሲዳማ ቡና ፊርማዉን እንደሚያኖር ይጠበቃል።