የቀድሞዉን አሰልጣኙን ውበቱ አባተ ዋና አሰልጣኝ አድርጎ ከሾመ በኋላ ለአዲሱ የውድድር አመት ዝግጅት በርከት ያሉ ተጫዋቾችን ወደ ስብስቡ መቀላቀል የቻለዉ ፋሲል ከተነማ ተጨማሪ ተጫዋች ማስፈረሙ ታውቋል።
በዚህም ከዚህ ቀደም ለአዳማ ከተማ ፣ ሲዳማ ቡና እና ያለፈውን የውድድር አመት ደግሞ ለወልቂጤ ከተማ መጫወት የቻለዉ ወጣቱ የመስመር ተከላካይ ዮናታን ፍስሃን በሶስት አመት የኮንትራት ውል አፄዎቹን መቀላቀሉን ክለቡ ይፋ አድርጓል።