በአሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ እየተመሩ በዝወዉሩ ላይ በንቃት በመሳተፍ ተጫዋቾችን ወደ ቡድናቸዉ በመቀላቀል ላይ የሚገኙት ጅማዎች በዛሬዉ ዕለት ደግሞ የተከላካይ አማካይ የሆነዉን አልሰሪ አልመሐዲንን አስፈርመዋል።
ከዚህ ቀደም ለድሬዳዋ ከተማ እና ወልዋሎ አዲግራት ዩንቨርስቲ ተጫዉቶ ማሳለፍ የቻለዉ አማካዩ ያለፉትን ሁለት የዉድድር አመታት ደግሞ በወልቂጤ ከተማ ማሳለፉ ይታወሳል።
በዛሬዉ ዕለት ደግሞ ለጅማ አባጅር ለመጫወት ፊርማዉን ማኖሩ ተረጋግጧል።