ወጣቱ የግብ ዘብ ወደ ወላይታ ድቻ አምርቷል!!

የኢትዮጵያ ከ23 አመት በታች ቡድን አባል የነበረዉ የባህርዳር ከተማዉ ግብ ጠባቂ ፅዮን መርዕድ ወደ ወላይታ ድቻ ማምራቱ ተረጋግጧል።

በዝዉዉር መስኮቱ ባህር ዳር ከተማ ሁለቱን ግብ ጠባቂዎች ማለትም አቡበከር ኑሪን ከጅማ አባጅፋር እንዲሁም ፋሲል ገ/ሚካኤልን ከሰበታ ከተማ ማስፈረማቸዉ ይታወቃል። ይህንንም ተከትሎ ያለፉትን ሁለት የዉድድር አመታት በጣና ሞገዶቹ ቤት ማሳለፍ የቻለዉ ግብ ጠባቂዉ ፅዮን መርዕድ ቀሪ የአንድ አመት ኮንትራት እያለዉ ከክለቡ ጋር በስምምነት ከተለያየ በኋላ በዛሬው ዕለት ለወላይታ ድቻ ለሁለት ዓመታት የሚያቆየውን ፊርማ ማኖሩ ታዉቋል።

Writer at Hatricksport

Facebook

Ermias Misganaw

Writer at Hatricksport