የዋሊያዎቹ የባህርዳር ጉዞ ተሰረዘ

 

ከታማኝ የመረጃ ምንጭ በተገኘ ዜና ዋሊያዎቹ ወደ ባህርዳር የመሄዳቸው ዕቅድ መሠረዙ እየተነገረ ነው፡፡
ባህርዳር ላይ የመልስ ጨዋታውን የሚያደርጉት ዋሊያዎቹ ባህርዳር ላይ የመዘጋጀት ዕቅድ ቢይዙም ኮቪድ 19 ከመከላከል አንጻር ሆቴል ውስጥ ቡድኑን ማሳረፍና የሚጠበቀውን የመከላከል ተግባር ለማካሄድ ተገቢ ባለመሆኑ ጉዞው መሠረዙን የደረሠው መረጃ ያስረዳል፡፡ ከኒጀር መልስ ግን ቡድኑ ለዝግጅት ጨዋታው ወደሚደረግበት ባህርዳር ይጓዛል ተብሎ ፕሮግራም መያዙ ታውቋል፡፡

 

Editor at Hatricksport

Facebook

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport