ሲዳማ ቡና በነገው ዕለት ልምምድ ይጀምራሉ !
ከቀናት በፊት የኮሮና ቫይረስ ምርመራ የተደረገላቸው የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ የቡድን አባላት በዛሬው ዕለት ውጤቱ ሲደርሳቸው ሁሉም የቡድን አባላት ነፃ መሆናቸው ለማወቅ ተችሏል ።
ሀትሪክ ስፖርት ከ ሲዳማ ቡና ክለብ ዋና አሰልጣኝ ዘርአይ ሙሉ ጋር ቆይታን ስታደርግ በነገው ዕለት በሀዋሳ አርቴፍሻል ስታዲየም በጊዜያዊነት ልምምድ መስራት እንደሚጀምሩ አሳውቀውናል ።
ከዚህ በተጨማሪም ሁሉም የቡድን አባላት ከ 72 ሰዓታት ቆይታ በኋላ የቫይረሱን ምርመራ በድጋሚ የሚደርግላቸው ይሆናል ።