የኢትዮጵያ ቡና ተጨዋቾች ዛሬ የኮቪድ ምርመራ ይደረግላቸዋልክለቡ ከቀናቶች በኋላ ዝግጅቱን ይጀምራል


የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የዘንድሮ የውድድር ዘመን ጅማሬን በናፍቆትና በጉጉት እየጠበቀ የሚገኘው ኢትዮጵያ ቡና ዛሬ ከእዚህ ሰዓት ጀምሮ በህክምና ባለሙያዎች ለቡድኑ ተጨዋቾች የኮቪድ ምርመራ የሚያደርግላቸው መሆኑ ታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የእዚህ ዓመት የውድድር ተሳትፎ ላይ ጠንካራ ቡድንን ይዞ ይቀርባል ተብሎ የሚጠበቀው ኢትዮጵያ ቡና ለአዲሱ የውድድር ዘመን በስኳዱ ላሰባሰባቸው በርካታ ተጨዋቾች ዛሬ የኮቪድ ምርመራን እንዲያደርጉ ጥሪ ባደረገበት ሁኔታ አብዛኛዎቹ ተጨዋቾች ለምርመራው በስፍራው ለመድረስ የተቃረቡ ሲሆን ክለቡን በዝውውር መስኮት ከመከላከያ የተቀላቀለው አበበ ጥላሁን ወደ አዲስ አበባ ከሰዓት የሚደርስ በመሆኑ ለእሱ ለብቻው ይኸው ምርመራ የሚደረግለት መሆኑም ታውቋል፡፡

ኢትዮጵያ ቡና ለዘንድሮው የሊግ ውድድር ተሳትፎ ከማምራቱ በፊት እስካሁን የቡድኑ ተጨዋቾች የሚያርፉበትን ካምፕ እና የመለማመጃ ስፍራውን ከኮቪድ ወረርሽኝ ነፃ ለማድረግ አስፈላጊውን የፅዳት ፕሮግራም ያደረገ ሲሆን ከዛም ባሻገር ቡድኑ ባወጣው ጨረታም አሁን ላይ ስሙን ማወቅ ባንችልም የክለቡ አስመጋቢ የምግብ ባለሙያም መታወቁ ተገልጿል፡፡

ኢትዮጵያ ቡና በዛሬው ዕለት ለተጨዋቾቹ ይሄን የኮቪድ ምርመራ ካደረገ በኋላም የፕሪ-ሲዝን ዝግጅቱን ቅዳሜ ወይንም ደግሞ ሰኞ ሊጀምሩ እንደሚችሉም እየተገለፀ ይገኛል፡፡

Editor at Hatricksport website

Facebook

መሸሻ ወልዴ

Editor at Hatricksport website