መነሻ ገጽ ከ 20 ዓመት በታች ” የጋና ጋዜጠኞች ባለሙያዎችና ተጨዋቾቾን በደንብ ያከብራሉ”
ከ 20 ዓመት በታችዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

” የጋና ጋዜጠኞች ባለሙያዎችና ተጨዋቾቾን በደንብ ያከብራሉ”

አጋራ
አጋራ

“የኢትዮጵያን ህዝብ ይቅርታ የምንጠይቀው በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ያስመዘገብነው ውጤት አመርቂ ባለመሆኑና የሜዳ አድቫንቴጃችንን ባለ መጠቀማችን ነው” አሰልጣኝ ፍሬው ሃ/ገብርኤል

የኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን በጋና የሶስት ቀናት ቆይታው ምቹና መልካም ጊዜ እንዳሳለፈ አሰልጣኝ ፍሬው ሃ/ ገብርኤል ተናገረ።

አሰልጣኙ ዛሬ ከቀትር በኋላ በፌዴሬሽኑ ጽ/ቤት በሰጠው መግለጫ “ውጤቱ ጥሩ ነው ማለት አልሻም አሸንፈን የምንመጣበትን ዕድል ባለመጠቀማችን የማለፍ ዕድላችን ሳይሳካ ቀርቷል..የኢትዮጵያን ህዝብ ይቅርታ የምጠይቀው በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ያስመዘገብነው ውጤት አመርቂ ባለመሆኑና የሜዳ አድቫንቴጃችንን ባለ መጠቀማችን ነው በእስካሁኑ ውጤት በኢትዮጵያ ተሰርቶ የማያውቅ ታሪክ ለሰሩት ተጨዋቾቼ ክብር አለኝ ፌዴሬሽኑንና አብረውኝ የለፉ አሰልጣኞችን አመሰግናለሁ በጣም ለደገፉንም በጣም ለተቹንም እንደ ግብዓት ስለሆነን አመሠግናለሁ በቀጣይ ውድድሮች አሉን ጠንክረን የምንዘጋጅ ይሆናል ለአለም ዋንጫ ለማለፍ ከጫፍ መድረሳችን የሚያስመሰግነን ነው በቀጣይ ጠንካራ ሆነን ለመቅረብ ጠንክረን እንደምንሰራ ተስፋ አደርጋለሁ” በማለት ተናግሯል።

“ከኛ ሜዳ ይልቅ በነሱ ሜዳ የተሻለ የኳስ ቅብብል ነበረን የሚያስቆጩ ኳሶች ስተናል ግልጽ ግብ ተሽሮብናል ጋናዊያን ደጋፊዎች ግቡ ተገቢ ነበር መጽደቅ አለበት ብለው ሲከራከሩ ሳይ ደነገጥኩ እንደ ሜዳቸው ሳይሆን እንደ ሜዳችን አይተን ነው የተጫወትነው ኳስ የሚያውቁ ደጋፊ መሆናቸውን አሳይተውናል ላሸነፉን እንኳን ደስ አላችሁ ብለን መጥተናል” በማለት አስረድቷል።

በኢትዮጵያና በጋና እግርኳስ መሃል የታው ልዩነት ምንድነው የተባለው አሰልጣኙ ” የጋና ብሄራዊ ቡድን ከኛ የተሻለ ነገር አላየሁበትም ከጋና በላይ የከበደን የታንዛኒያ ብሄራዊ ቡድን ነው ከውድድሩ በላይ ያየሁት ጥሩ ነገር በጋና የሴት ሊግ በቲቪ ይተላለፋል ጋዜጠኞቹ ባለሙያና ተጨዋቾችን ያከብራሉ ከምስራቅ አፍሪካ ታንዛኒያ ከምዕራቡ ደግሞ ጋና የሴቶቹ ጨዋታ ይተላለፋል” በማለት ልዩነቱን አስቀምጠዋል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ኢትዮጵያን በውጪዜናዎች

በካናዳ የኢትዮጵያዊያን የባህል እና ስፖርት ሊግ በይፋ ተመሠረተ

በካናዳ የኢትዮጵያ የባህል እና ስፖርት በሚል ስያሜ ሊግ ተቋቋመ። የኢትዮጵያን ባህል ለአለም...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የ32ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች አህመድ ረሺድ (ድሬደዋ ከተማ) : በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀምራዊ ለባሾቹ እና የጣና ሞገዶቹ ጣፋጭ ሦስት ነጥብን ወደ ቋታቸው ከተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ባህርዳር ከተማ ወሳኝ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና ሲሸነፍ በተጠባቂው ጨዋታ መቻል በጎል ፌሽታ ነገሌን ረቷል

በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በሀድያ ሆሳዕና ሽንፈት ሲያስተናግድ...