መነሻ ገጽ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና አዳዲስ ማሊያዎቹን ተረከበ
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ኢትዮጵያ ቡና አዳዲስ ማሊያዎቹን ተረከበ

አጋራ
አጋራ

*…ከራይድ ጋር የገቡት ስምምነት ይዘት በቅርቡ ይፋ ይሆናል..

ኢትዮጵያ ቡናና ከሀ እስከ ፐ የተፈራረሙት ስምምነት አንዱ አካል የሆነው ብራንድ ሾፕ ከአንድ ወር በኋላ እንደሚከፈት ሁለቱም ወገኖች በሰጡት አስታወቀ።

በሳፋሪ አዲስ ሆቴል በተሰጠ መግለጫ ላይ የክለቡ ፕሬዝዳንት መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞ እንደተናገሩት “በኢትዮጵያ ክለቦች ታሪክ ፈር ቀዳጅ የሆነው ብራንድ ሾፕ አራት ኪሎ በሚገኘው አምባሳደር ሞል እንከፍታለን በዚህም ደስተኛ ነን” ብለዋል።

የክለቡ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶገዛኸኝ ወልዴ በበኩላቸው “በሁለቱ ስምምነት ዋናው ቡድን፣ከ20 እና ከ17 አመት በታችና የሴቶች ቡድን የሚለብሷቸው 500 ማሊያም ዛሬ እንረከባለን በዚህ ውስጥ ለቡድኖቹ አሰልጣኞች 100 ማሊያዎች ለአሰልጣኞች ቡድን መጠቀሚያ ደግሞ 50 ቲሽርት ተካቷል በአጠቃላይ ለነኚህ ማሊያዎች 3ሚሊዮን ሃያ አምስት ሺህ ብር ወጪ ተደርጓል” በማለት ተናግረዋል።

” በገበያው ላይ ያለውና ከባድ ፈተና የሆነብን ማሊያ አስመስሎ የመስራትና የመሸጥ ሙከራው ነው በቡና ማሊያና ብራንድ እየታተመ ለገበያ መቅረቡ እንዲቆም ለማድረግ የደጋፊያችንን ትብብር እንጠይቃለን ከደጋፊው ጋር እንደሚሳካልንም ተስፋ እናደርጋለን” ያሉት አቶ ገዛኸኝ ” በቡና ሎጎ ያለበት ማሊያ፣ ቱታ፣ አርማ፣ሰዓት፣ አንሶላና ሙሉ ሱፍ እንዲሁም ሌሎች ክለቡን የሚመለከቱ ቁሳቁሶች ከአንድ ወር በኋላ ለሽያጭ የሚቀርቡ ይሆናል ስራው በዋናነት ሁለቱ ወገኖች ባቋቋሟቸው የጋራ ኮሚቴ ይመራሉ”በማለት አስረድተዋል።

ከሀ እስከ ፐ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ፍሬዘር ዐቢይ በበኩላቸው “የክለቡን ማሊያ ዲዛይኑን ከቦርዱና ከደጋፊዎች ጋር ተነጋግረን እነሱም ሀሳባችንን ተቀብለው የብራንድ ሾፑ ተግባራዊ ሆኗል። የትጥቅ ምርቱ 50 በመቶ ከሀገር ውስጥ 50 ከመቶ ከውጪ ነው ብራንድ ሾፑን በመክፈት ኢትዮጵያ ቡና የመጀመርያ ክለብ በመሆኑ ደስተኞች ነን ከዚህ በፊትም ከሀበሻ ቢራ ጋር ባለን ግንኙነት የሀበሻ ብራንድ ሞል ከፍተናል የቡና ደጋፊ ትልቅ ሀብት ነው ያንን የምንሰራበት ይሆናል ኢትዮ.ቡና ለኛ እንደቤተሰብ ነው የቡድኑ ደጋፊ ነን ግንኙነታችን ቢዝነስ ተኮር ብቻ አይደለም” በማለት ተናግሯል።ክለቡ የዋናው ቡድን ሶስት አይነት ማሊያዎች ቱታና የአሰልጣኞችን ትጥቅ ያስተዋወቀ ሲሆን በቅርብ ቀናት ውስጥ ከራይድ ጋር ስለገቡት ስምምነት ይፋ እንደሚያደርጉ አመራሮቹ አስታውቀዋል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና የሊጉን መሪነት ሲያጠናክር ኤሌክትሪክ እና አፄዎቹም አሸንፈዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ሲዳማ ቡና ፣ ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ እና ፋሲል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

ገዛኸኝ ደሳለኝ (ሸገር ከተማ) : ክለቡ ከ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረገው የ26ኛ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...