ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 18ኛ ሳምንት በተደረጉ ጨዋታዎች አምስት ጨዋታዎች በመሸናነፍ ሁለት ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ሲጠናቀቁ 24 ጎሎች በ22 ተጫዋቾች ተቆጥረዋል። የጎሎቹ አገባብ ሁለቱ በፍፁም ቅጣት ምት ቀሪዎቹ በጨዋታ የተቆጠሩ ናቸው። በሳምንቱ 29 ተጫዋቾችና የቡድን አመራሮች በቢጫ ካርድ ሲገሰፁ ሶስት ተጫዋች ቀይ ካርድ ተመልክተዋል።
የኢትዮጵያ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ማክሰኞ ሚያዝያ 3 2015 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያ(ዎች)ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ የተለያዩ ውሳኔዎችን አስተላልፏል።
- ማሰታውቂያ -
በተጫዋች ደረጃ በተላለፉ ውሳኔዎች ይስሀቅ ተገኝ (አርባምንጭ ከተማ) የጨዋታ ጊዜ ሆን ብሎ በማባከን ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ 1 ጨዋታ እንዲታገድና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 /አንድ ሺ አምስት መቶ/ እንዲከፍል፣ ዓለምብርሀን ይግዛው(ፋሲል ከነማ) በከባድ የአጨዋወት ጥፋት ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ 3 ጨዋታ እንዲታገድና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 3000 /ሶስት ሺ/ እንዲከፍል፣ አምሳሉ ጥላሁን(ፋሲል ከነማ) ሁለተኛ ቢጫ ካርድ የሚያሰጥ ጥፋት በመፈፀሙ ቀይ ካርድ አይቶ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ 1 ጨዋታ እንዲታገድ ሲወሰን አብነት ደምሴ(ኢትዮ ኤሌትሪክ ) እና አብዱልባሲጥ ከማል(ሃዋሳ ከተማ) 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ በመመልከታቸው 1 ጨዋታ እንዲታገዱና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 /አንድ ሺ አምስት መቶ/ እንዲከፍሉ ተወስኗል።
በክለቦች ደረጃ በተላለፉ ውሳኔዎች የፋሲል ከነማ ቡድን አራት ተጫዋች በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ የገንዘብ ቅጣት ብር 5000 /አምስት ሺ/ እንዲከፍል ሲወሰን የክለቡ ደጋፊዎች የእለቱን ዳኛ አፀያፊ ስደብ ስለመሳደባቸው ሪፖርት በመቅረቡ የክለቡ ደጋፊዎች ለፈፀሙት ጥፋት ክለቡ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት ብር 50000/ሃምሳ ሺህ/ እንዲከፍል እንዲሁም መቻል በተመሳሳይ በሳምንቱ ጨዋታ የክለቡ ደጋፊዎች የእለቱን ዳኛ አፀያፊ ስደብ ስለመሳደባቸው ሪፖርት በመቅረቡ ብር 50000/ሃምሳ ሺህ/ እንዲከፍል ተወስኗል።