መነሻ ገጽ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ኢትዮጵያ መድኅን በደጋፊዎቹ ያልተገባ ባህሪ ለቅጣት ተዳርጓል
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ኢትዮጵያ መድኅን በደጋፊዎቹ ያልተገባ ባህሪ ለቅጣት ተዳርጓል

አጋራ
አጋራ

 

ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 17ኛ ሳምንት በተደረጉ ጨዋታዎች ሰባት ጨዋታዎች በመሸናነፍ አንድ ጨዋታ በአቻ ውጤት ሲጠናቀቅ 21 ጎሎች በ18 ተጫዋቾች ተቆጥረዋል። የጎሎቹ አገባብ ሁለቱ በፍፁም ቅጣት ምት ቀሪዎቹ በጨዋታ የተቆጠሩ ናቸው። በሳምንቱ 38 ተጫዋቾችና የቡድን አመራሮች በቢጫ ካርድ ሲገሰፁ ሁለት ተጫዋች ቀይ ካርድ ተመልክተዋል።

የኢትዮጵያ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ረቡዕ መጋቢት 27 2015 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያ(ዎች)ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ የተለያዩ ውሳኔዎችን አስተላልፏል።

በሳምንቱ መርሃ ግብር በተጫዋቾች ደረጃ በተላለፈ ቅጣት አማኑኤል ዮሀንስ (ኢትዮጵያ ቡና) ሁለተኛ ቢጫ ካርድ የሚያስጥ ጥፋት በመፈፀሙ ቀይ ካርድ አይቶ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ 1 ጨዋታ እንዲታገድ ፣ ሀቢብ መሀመድ(ኢትዮጵያ መድን ) የተለያዩ አምስት ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ የተመለከተ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት አንድ ጨዋታ እንዲታገድና የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 /አንድ ሺ አምስት መቶ/ እንዲከፍል ሲወሰን ኮፊ ሜንሰህ(ለገጣፎ ለገዳዲ) ዳኛን አፀያፊ ስድብ በመሳድብ ቀይ ካርድ አይቶ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ 3 ጨዋታ እንዲታገድ እና 3000 ብር እንዲከፍል እንዲሁም ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ በቀይ ካርድ ተወግዶ ወደ መልበሻ ክፍል በመሄድ ላይ እያለ የኢትዮጰያን ዳኞችን አፀያፊ ስድብ ስለመሳደቡ ሪፖርት የቀረበበት በመሆኑ ለፈፀመው ጥፋት ከተቀጣው ቅጣት በተጨማሪ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት ተጨማሪ 3/ሶስት/ ጨዋታ እንዲታገድና ብር 3000/ሶስት ሺ/ እንዲከፍል በመወሰኑ በድምሩ የ6 ጨዋታና 6000 ብር ቅጣት ተላልፎበታል።
አዱኛ ፀጋዬ(ሲዳማ ቡና) በቴክኒክ ክልል ውስጥ የሚገኘውን መስታወት ስለመስበሩ ሪፖርት የተደረገበት በመሆኑ ተጫዋቹ ባጠፋው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት ብር 10, 000 /አስር ሺ/ እንዲከፍል ሲወሰን በተጨማሪም የተሰበረውን ንብረት እንዲተካ ወይም እወዳዳሪውአካል የሚያቀርበውን የንብረትን ዋጋ እንዲከፍል ተወስኗል፡፡

በክለቦች ደረጃ በተላለፈ ቅጣት ኢትዮጵያ መድን በ17ኛ ሳምንት ጨዋታ የክለቡ ደጋፊዎች የእለቱን ዳኛ አፀያፊ ስደብ ስለመሳደባቸው ሪፖርት የቀረበ በመሆኑ የክለቡ ደጋፊዎች ለፈፀሙት ጥፋት ክለቡ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት ብር 50000/ሃምሳ ሺህ/ እንዲከፍል ተወስኗል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሽንፈት ሲገጥመው በድንጉዛ ደርቢ የጦና ንቦቹ እና ኤሌክትሪክ ድል ቀንቷቸዋል

በሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ተከታታይ ሽንፈትን በሸገር ሲያስተናግድ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

አዳማ ከአስር ፈረሰኞቹ ከሦስት እና ነብሮቹ ከአራት ጨዋታዎች በኋላ አሸንፈዋል

በሊጉ የሳምንቱ የመክፈቻ ቀን ጨዋታ አዳማ ከተማ በጎል ደምቆ ሲያሸንፍ ቅዱስ ጊዮርጊስ...

ዜናዎችየአዲስአበባ እግርኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጠዋል የተባሉት ሁለት ዳኞች ወደ መጡበት እንዲመለሱ ተደረገ

በዮሴፍ ከፈለኝ በወልዋሎ እና ነገሌ አርሲ ጨዋታ ላይ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ ሁለት...

ቅዱስ ጊዮርጊስዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንፊፋ

ፊፋ ቅዱስ ጊዮርጊስ ላይ ጥሎት የነበረውን የዝውውር ዕገዳ በጊዜያዊነት አነሳ

ቅዱስ ጊዮርጊስ በአራት የቀድሞ ተጫዋቾች ቀርቦበት በነበረው ክስ በፊፋ ጥሎበት የነበረው የተጫዋቾች...