የጨዋታ ዘገባ | ፈረሰኞቹ ተከታታይ ድል አስመዝግበዋል

 

የሶስተኛ ሳምንት የ ቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የመጀመሪያ ቀን መርሀ ግብር ዛሬም ቀጥለው ሲካሄዱ የሸገር ክለቦችን ባለ ድል አድርጎ ተጠናቋል ።

ረፋድ አራት ሰዓት ላይ በጀመረው መርሀ ግብር ፈረሰኞቹ ተከታታይ ድል ሲያስመዘግቡ ከጨዋታ ብልጫ ጋር ሀዋሳ ከተማን አሸንፈው ለመውጣት ችለዋል ። ከሁለት ሳምንታት በኋላ ወደ ሜዳ የተመለሰው ጌታነህ ከበደ ኮከብ ሆነ በዋለበት ጨዋታ ላይ ሁለት ጎሎችን ሲያስቆጥር በርካታ የግብ እድሎችን ፈጥሮ ታይቷል ።

ከመስመር በሚነሱ ኳሶች የማጥቃት አማራጫቸውን አስፈተው የገቡት ፈረሰኞቹ ከቀኝ መስመር በተሻገረችው ኳስ እና ጌታነህ ከበደ በሞከራት አስደንጋጭ ሙከራ ታጅበው ጨዋታቸውን ሲጀምሩ አቤል ያለው በመልሶ ማጥቃት የግል ብቃቱን ተጠቅሞ ወደ ግብ የሞከራት ኳስ እና በግቡ አግዳሚ ታካ የወጣችው ሙከራዎች በፈረሰኞቹ በኩል የሚጠቀስ ነበር ።

ከአስደንጋጭ ሙከራዎች ቆይታ በኋላ የመጀመሪያ ግባቸውን ያገኙት ፈረሰኞቹ አቤል ያለው በግራ መስመር ይዞት የገባውን እና ማሊያዊው አዲስ ፈራሚ ኔግላንዴ ፈረሰኞቹን ቀዳሚ ያደረገች ግብ ማስቆጠር ችሏል ። በእለቱ ድንቅ ብቃቱን ሲያሳይ የቆየው አቤል ያለው ላይ በፍፁም ሳጥን ውስጥ የተሰራውን ጥፋት ጌታነህ ከበደ የፈረሰኞቹን መሪነት ያጠናከረች ግብ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል ።

ለእረፍት ከመውጣታቸው በፊት ከግራ መስመር በመነሳት ይዞት የገባውን ኳስ ለ ጌታነህ በማቀበል የግብ መጠኑን ወደ ሶስት ከፍ በማድረግ ለእረፍት መውጣት ችለዋል ።

ከእረፍት መልስ ሁለቱም ቡድኖች በማጥቃቱ ረገድ ሲሳተፉ ሀዋሳ ከተማዎች ከቆሙ ኳሶች የግብ እድልን ሲፈጥሩ ተስተውሏል ። ለዚህም ከእረፍት መልስ ሀዋሳ ከተማዎች ከሳጥን ውጪ ያገኙትን ቅጣት ምት ሞክረው ፓትሪክ ማታሲ ያወጣባቸው ሙከራ ተጠቃሹ ነው።

በተቃራኒው ፈረሰኞቹ አሸናፊነታቸውን ያረጋገጡበትን ግብ ከማዕዘን ምት አቤል ያለው ያሻማውን የሀዋሳ ከተማው ዳዊት ታደሰ በራሱ ላይ አስቆጥሯል ።

ሀዋሳ ከተማዎች ከሽንፈት ያልታደገችውን ግብ በፍፁም ቅጣት ምት ሳጥን ውስጥ አብድልከሪም ኳስ በእጅ መንካቱን ተከትሎ የተሰጠችውን ፍፁም ቅጣት ምት ወጣቱ የፊት መስመር ተጫዋች ብሩክ በየነ ከመረብ ሊያሳርፍ ችሏል ።

ውጤቱን ተከትሎ ፈረሰኞቹ በሊጉ ሁለተኛ ላይ ሲቀመጡ ሀዋሳ ከተማዎች የመጨረሻውን ደረጃ ላይ ለመቀመጥ ተገደዋል ።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor