መነሻ ገጽ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ድሬዳዋ ከተማ አሰልጣኝ ዮርዳኖስ ዓባይን ማሰናበቱ ርግጥ ሆኗል
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግድሬዳዋ ከተማ

ድሬዳዋ ከተማ አሰልጣኝ ዮርዳኖስ ዓባይን ማሰናበቱ ርግጥ ሆኗል

አጋራ
አጋራ

👉…. አራት ተከታታይ ጨዋታ ተሸንፏል
👉….ማግኘት ካለበት 20 ነጥብ ያሳካው 18ቱን ብቻ ነው

የድሬዳዋ ከተማ እግርኳስ ክለብ ውጤታማ አላደረገኝም ያለውን አሰልጣኝ ዮርዳኖስን ዓባይን ከአዳማ ወደ ድሬዳዋ መጥራቱ ተሰማ።

ከታማኝ የክለቡ ምንጭ በተገኘ መረጃ አሰልጣኙ ነገ ጠዋት ከክለቡ አመራሮች የስንብት ደብዳቤ እንደሚደርሰው ተገልጿል። ክለቡ የአንድ አመት ኮንትራት ለአሰልጣኙ ሲሰጥ በውስጥ ውል መሰረት አንደኛ ዙር ሲጠናቀቅ 20 ነጥብ እንደዚሁም በተከታታይ 4 ጨዋታ ያለመሸነፍ ግዴታ ውስጥ አስገብቶ ነው። ክለቡ ባለፉት 6 አመታት አራት ጨዋታ በተከታታይ አለመሸነፉን ተከትሎ አሰልጣኙም ይህን ውጤት ማስቀጠል አንዳለበት በውሉ ውስጥ አካቷል። ያም ሆኖ አሰልጣኙ በወላይታ ድቻ 1ለ0፣ በአዳማ ከተማ 2ለ0፣ በአርባምንጭ ከተማ 3ለ1 እንዲሁም በቅዱስ ጊዮርጊስ 2ለ0 ተሸንፎ የክለቡን አራት ተከታታይ ጨዋታ ያለመሸነፍ ጠንካራ ጉዞ ማስቆሙ ክለቡን ቅር አሰኝቷል።

ባለፉት አራትና አምስት አመታት ላለመውረድ የመጫወቱ ተመሳሳይ ስህተት ላለመድገም ሂሳብ በመስራት ላለመውረድ በአንደኛ ዙር የግድ 20 ነጥብ ያስፈልጋል ብሎ ለአሰልጣኙ ግዴታ ያስቀመጠ ቢሆንም አሰልጣኙ በአንደኛ ዙር ማግኘት ካለበት 45 ነጥብ ያሳካው 18 ነጥብ ብቻ መሆኑ የማሰናበት ርምጃ እንዲወሰድበት አድርጓል። የክለቡ አመራሮች በሁለቱ ውል ግዴታ መሠረት አንደኛ ዙር ላይ አሰልጣኙን ማሰናበት እየቻሉ አለማባረራቸው ታማኝ ምንጫችን ገልጿል።

ያም ሆኖ ክለቡ ሊጉ ለብሄራዊ ቡድን ሲባል ከመቋረጡ በፊት ሁለት ተከታታይ ጨዋታ ድሬዳዋ ላይ ስለሚካሄድ ከሲዳማ ቡናና ከለገጣፎ ለገዳዲ ጋር የነበረውን ጨዋታ በአደራ መልክ እንዲመራ ለአሰልጣኙ በደብዳቤ መግለጹ ታውቋል። ከሲዳማ ቡና ጋር በፎርፌ 3ለ0 ሲያሸንፍ ትላንት ደግሞ በለገጣፎ ለገዳዲ 2ለ1 መረታቱ የመጨረሻ ውሳኔ እንዲወሰድበትና ከአዳማ ወደ ድሬዳዋ እንዲመለስ ማድረጉ ታውቋል።

የክለቡ ታማኝ ምንጭ መረጃ መሠረት የአሰልጣኙና የክለቡ መለያየት ከውጤት ውጪ ሌላ ምክንያት እንደሌለው በአጽንኦት ገልጾ ከዚያ ውጪ የሚናፈሰው ወሬ እውነት ያልሆነና ክለቡን የማይወክል መሆኑን ገልጿል። በ18ኛው ሳምንት መርሃ ግብር የፊታችን ሰኞ 9 ሰአት ከሀድያ ሆሳዕና ጋር የሚጫወቱት ድሬዳዋዎች በቀጣይ ጨዋታዎች በምክትል አሰልጣኞቹ እንደሚገቡ ተገልጿል። ድሬዳዋ ከተማ በእስካሁኑ 17 ጨዋታ 5 ጊዜ አሸንፎ 6 ጊዜ አቻ ወጥቶ 6 ጊዜ ተሸንፎ በ21 ነጥብ 11ኛ ደረጃ በመያዝ ከወራጅ ቀጠና 3 ነጥብ ብቻ ከፍ ማለቱ ድሬዳዋ ከተማዎችን ማስቆጣቱ ታውቋል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

ገዛኸኝ ደሳለኝ (ሸገር ከተማ) : ክለቡ ከ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረገው የ26ኛ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ በድል ሲቀጥሉ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋም አሸንፈዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን ወደ ቋቱ ሲከት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨዋታ ብልጫ...