ወልቂጤ ከተማ የጨዋታ ማጭበርበር ተካሂዶብኛል ሲል ከሰሰ

በኢትዮዽያ ፕሪሚየር ሊግ ድሬዳዋ ከተማ ሻምፒዮኑ ፋሲል ከነማን 3 ለ1 መርታቱን ተከትሎ ፋሲል ከነማ ላይ ቅሬታዎች እየተሰሙ ነው።

በተለይ በድሬዳዋ ማሽነፍ ቀጥተኛ ተጎጂ የሆነው ወልቂጤ ከተማ “ፋሲል ከነማ ሆን ብሎ ድሬዳዋ ከተማን ለመጥቀም ከአቅም በታች በመጫወት የጨዋታ ማጭበርበር በመፈጸሙ የተቀረጸውን ቪዲዮ በማየት በገለልተኛ ወገን እንዲጣራና ርምጃ እንዲወሰድ እንጠይቃለን” ሲል የኢትዮዽያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንን አሳስቧል።

“ቅራኔ የሚፈጥረውን ይህን አስነዋሪ ድርጊት የሀገራችንን ክለቦች ሰላማዊ ግንኙነት የሚያበላሽና ጥቁር ነጥብ የሚያስጥለውን የፋሲል ከነማ ድርጊት እንዲመረመር እንጠይቃለን” ያለው ወልቂጤ ከተማ “የብሄራዊ ቡድንን በአሰልጣኝነት በመራ አሰልጣኝ መከወኑ ከወር በፊት ኒጀር ስፖርታዊ ጨዋነትን ተከትላ ማሽነፏ ብሄራዊ ቡድናችን ለአፍሪካ ዋንጫ ማለፉን በመርሳት ስነምግባር በሌላቸው የብሄራዊ ቡድኑ ተጨዋቾች መፈጸሙ በስነምግባራቸው ምስጉን የሆኑ አሰልጣኞችና ተጨዋቾችን አንገት ያስደፋ ድርጊት ነው” በማለት ኮንኖ ህጋዊ መፍትሄ እንዲሰጠው ጠይቋል።

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport