የ ዲ ኤስ ቲቪ የቡድን አባላት ተሸነፉ

የቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ በተለያዩ ከተሞች መካሄዱን አስመልክቶ የ ዲ ኤስ ቲቪ የቡድን አባላት በተለያዩ ጊዜያት ጨዋታቸውን እንደሚያካሂዱ ይታወቃል ።

ይህንንም ተከትሎ በዛሬው ዕለት የ ዲ ኤስ ቲቪ  ሙሉ የቡድን አባላት ከ ከዋልያዎቹ የአሰልጣኞች ክፍል እና ከ ሊግ ካምፓኒው ሙሉ የቡድን አባላት ጋር ጨዋታቸውን በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ስታዲየም ማካሄድ ችለዋል ።

አዝናኝ በነበረው እና አስራ ስድስት ጎሎች በታየበት የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ የ ዲ ኤስቲቪ አባላት 9 ለ 7 በሆነ ውጤት ሽንፈትን ቀምሰዋል ።

የዋልያዎቹ ዋና አሰልጣኝ ውበቱ አባተ አራት ጎሎችን ከመረብ በማሳረፍ ቁልፍ ሚናን ሲጫወቱ የ ዲኤስቲቪ የካሜራ ባለሙያው ብሩክ መክብብ በተቃራኒው ሀትሪክ መስራት የቻለ ተጫዋች ሆኗል ።

የ ዲኤስቲቪ የጨዋታ አስተላላፊ የሆኑት ጋዜጠኛ ሰዒድ ኪያር ሁለት ጎሎችን እንዲሁም ጋዜጠኛ መኮንን ሀይሉ ለግብ የሚሆን ኳስ አመቻችቶ በማቀበል ሀትሪክ መስራት ችሏል ።

በዚህ ጨዋታ ላይ የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ኢንስትራክተር አብርሀም መብርሀቱን ጨምሮ የ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከ ሀያ አመት በታች ዋና አሰልጣኝ ተመስገን ዳና በስታዲየም በመገኘት ጨዋታውን መታደም ችለዋል ።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor