ኢትዮጵያዊቷ መሳይ ተመስገን ፊርማዋን ለያንጋ ፕሪንስአኑራለች።

ያለፉትን ቀናት ወደ ታንዛኒያ አምርታ በያንጋ ፕሪንስስ ክለብ ልምምድ ስትሰራ የቆየችው ኢትዮጵያዊቷ የመስመር አጥቂ መሳይ ተመስገን ሰሞኑን የህክምና ምርመራዋን ካጠናቀቀች በኋላ ለክለቡ ፊርማዋን ለአንድ አመት አኑራለች።
ከኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ በኋላ በመቻል እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቆይታ ያደረገችው ተጫዋቿ ከተሳኩ የንግድ ባንክ ጊዜዋ በኋላ ከአረጋሽ ካልሳ ፣ አረያት ኦዶንግ ፣ ንቦኝ የን እና ሴናፍ ዋቁማ ቀጥላ በታንዛኒያ ፕሪምየር ሊግ የምትጫወት አምስተኛዋ ኢትዮጵያዊ ተጫዋች ሆናለች።
አስተያየት ይስጡ