አሰልጣኝ ፍሬው ሀይለገብርኤል የዩጋንዳ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ በመሆን ተሾመ
የቀድሞው የደደቢት ፣ ሲዳማ ቡና ፣ የኢትዮጵያ ከሀያ እና የዋናው ሉሲዎቹ የሴቶች ብሔራዊ ቡድኖች አሰልጣኝ ሆኖ ያገለገለው እንዲሁም የኢትዮጵያ ሴቶች ከሀያ አመት በታች ቡድንን ለሴካፋ ዋንጫ ያበቃው አሰልጣኝ ፍሬው ሀይለገብርኤል በዩጋንዳው ካምፓላ ኪዊንስ የሴቶች ክለብን እየመራ የሀሪቱን ፕሪምየር ሊግ እና የጥሎ ማለፍ ዋንጫን ማንሳት የቻለ ሲሆን ከወራቶች በፊት ደግሞ ከክለቡ ጋር ከተለያየ በኋላ በይፋ ለቀጣዮቹ ሁለት አመታት የዩጋንዳ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሆኖ ተሹሟል።
አሰልጣኙ ከሴቶች ክለብ በተጨማሪ ቢሾፍቱ አውቶሞቲቭን በከፍተኛ ሊጉ ማሰልጠኑ ይታወሳል።
አስተያየት ይስጡ