መነሻ ገጽ The BiG Interview ”በሙስና ከተጨማለቀና በወረደ እግር ኳስ በሚገኘው ገንዘብ ሆዴን የምሞላበት፤ ልጆቼን የማሳድግበት ሞራል በማጣቴ ነው ከስልጠናው ዞር ያልኩት”ኢንስትራክተር አብርሃም ተክለሃይማኖት
The BiG InterviewUncategorizedሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ

”በሙስና ከተጨማለቀና በወረደ እግር ኳስ በሚገኘው ገንዘብ ሆዴን የምሞላበት፤ ልጆቼን የማሳድግበት ሞራል በማጣቴ ነው ከስልጠናው ዞር ያልኩት”ኢንስትራክተር አብርሃም ተክለሃይማኖት

አጋራ
አጋራ

በይስሐቅ በላይ




ሀትሪክ፡- የኢትዮጵያ እግር ኳስ ከዓለም
151ኛ ነው፤ እግር ኳሱም ከዓለም ቀርቶ
በአፍሪካ ደረጃ ተፎካካሪ መሆን አልቻለም፡
፡ በዚህ በደከመ እግር ኳስ ኢስትራክተር
ተብለህ ስትጠራ ምን ይሰማሀል? ውስጥህስ
በደስታ ይሞላል….?

ኢንስትራክተር አብርሃም፡- እውነት
ለመናገር በተለይ አሁን አሁን ኢስትራክተር
ተብሎ መጠራት በጣም ያሳፍረኝ አንገቴን
ያስደፋኝ ጀምሯል፤ የኢትዮጵያን እግር ኳስ
በሙያችን መለወጥ ሣንችል ኢንስትራክተር
መባል ብቻውን ሙሉ የደስታ ስሜት
እንዳይሰማህ ያደርጋል፡፡ እውነቱን ንገረኝ
ካልከኝ በዚህ ስያሜም ስጠራ ከመኩራራት
ከመደሰት ይልቅ ማፈር ከጀመርኩ
ሰነባብቻለሁ፡፡

ሀትሪክ፡- ግን እኮ አንተ ይሄንን
ማዕረግ ለማግኘት ብዙ ታግለሃል፤እንደውም
ኢንስትራክተር የሆንከው ከሕግ ውጪ
የፌዴሬሽኑን ስልጣንህን ተጠቅመህ ነው
በሚል ቅሬታ የሚያቀርቡብህ በርካቶች
ናቸው?

ኢንስትራክተር አብርሃም፡- በነገራችን
ላይ ከእኔ የሚበልጡ ሊኖሩ ይችላሉ፤
እኔ ከሁሉም የምበልጥ የተለየሁ ሰው
ነኝ ባቅልልም የማንስበት ሁኔታ ግን አለ
አልልምⵆ ሌላው እንደ ከፍተኛ ባለሙያ
ለኢስትራክተርነት እበቃለሁ የሚለውን
ያስቀመጠኝ ሰው ይመልሰዋል፤ እኔ
የማውቀው አንድ ሀቅ ግን በአቋራጭ
ሄጄ ይሄን ስያሜ አላገኘሁትም፡፡ በጣም
የሚገርምህ ሊያስቀሩኝ የሞከሩ ብዙ የታገሉ
ሰዎች ሁሉ ነበሩ አልተሳካላቸውም እንጂ፡
፡ በአጠቃላይ ለቦታው ብቁ መሆኔን ነው
የማውቀው፡፡ ምንአልባት ያንሰዋል ካልተባለ
በስተቀር ይበዛብኛል ለማለት ይቸግረኛል፡፡
ሀትሪክ፡- አብርሃም ራሱን በራሱ ነው
የሾመው ለቦታው ማስታወቂያ ሲወጣ
የሚቀናቀኑትንና የሚፎካከሩትን ታላላቅ
አሰልጣኞች ለመጣል ብሎ ከ50 አመት
በታች የሚል መስፈርት እንዲወጣ በማድረግ
መመዘኛውን በራሱ ልክ አስፍቶ ነው
ኢስትራክተር የሆነው ብለው ነቀፌታ
ለሚያቀርቡብህ መልስህ ምንድነው፤ ?
ኢንስትራክተር አብርሃም፡- እንደእዚህ
አይነት ቅሬታን ያቀረቡ ሰዎች በወቅቱ
ነበሩ፤ እኔ አሁን አልዋሽምⵆ ሰዎች
ኢስትራክተር መሆንን እንደ ልዩ ነገር
አይተውት በወቅቱ በጣም ተረበሹ እንጂ
ኢንስትራክተር መሆን ማለት ምንም ማለት
አይደለም፤ ምንም አይገኝበትም፤እኔ አሁን
ኢንስትራክተር ሆኜም የተለየ ያገኘሁት
ነገርም የለም፤ምናልባት ካሜሮን ወይም
ካይሮ መመላለስን እንደ ትልቅ ነገር
ካልተወሰደ በስተቀር፡፡ ከ50 አመት በታች
የሚለውን መስፈርት በራስ ልክ አስፍተህ
ራስህ ሄድክበት ለሚለው ተራ ወቀሣ ይሄን
ክራይቴሪያ እኛ ሳንሆን ራሱ ካፍ ነው
ያወጣው በኋላ ላይ ሻረው እንጂ፡፡ እኔ
ለኢንስትራክተርነት ኮርስ የሄድኩት በዚህ
መንገድ አይደለም፡፡ በወቅቱ እኔ የብ/ቡድን
አሰልጣኝ ነበርኩ፤ የሁለት አመት ኮንትራት
ነበረኝ፡፡ ከዚህ ውስጥ ስድስት ወሩን ሰርቼ
አንድ አመት ተኩል ሲቀረኝ በወቅቱ በክለቦችና
በፌዴሬሽኑ መካከል የተፈጠረውን ውዝግብ
ተከትሎ ፌዴሬሽኑ ለሁለት አመት በፊፋ
በመታገዱ የብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝነት
ሥራዬም ቆመ፡፡ ፌዴሬሽኑ የሁለት አመት
ኮንትራት ስላለኝ ደሞዝ የመክፈል ግዴታ
ስለነበረበት ያለ ሥራ ከምንከፍለው የቴክኒክ
ክፍሉን ይምራ ብለው በኃላፊነት መደቡኝ፡፡
የብ/ቡድኑን ሥር ትቼ አንዳንድ ኮርሶችንና
የወጣቶችን እንቅስቃሴ እንድከታተል ተደረገ፡
፡ በዚህ ሂደት ውስጥ እያለን ካፍ ሁለት
ሰዎችን ለኢስትራክተርነት ላኩ አለ፡፡ በወቅቱ
የነበሩት የቴክኒክ ኮሚቴዎች እነ ሸዋረጋ
ደስታ ፕሮፌሰር ወንድሙ፣ሲያምረኝ፣
አሰግድ ተስፋዬ እኔንና ገ/መድህን ኃይሌን
መረጡን፡፡ እኔ በአንደኝነት በመመረጤ
በካፍ ሙሉ ወጪ፣ ገ/መድህን ደግሞ
ወጪውን ራሱ ሸፍኖ ይሄድ ተባለ፡፡ ገ/
መድህን ወጪህን ሸፍነህ ሂድ ሲባል ̎እምቢ̏
ብሎ ቀረ እኔ ሄድኩ፡፡ ፅሁፌን አቀረብኩ፤
በቃ የተሰጠውን ኮርስ ወስጄ ኢስትራክተር
ሆንኩ፤ ይሄ ነው ሂደቱ እንጂ እኔ በአቋራጭ
ኢንስትራክተር አልሆንኩም ከ50 ዓመት
በታች የሚለው መመዘኛም በኋላ ላይ ተሻረ
እንጂ የካፍ ክራይቴሪያ ነው፡፡

ሀትሪክ፡- …አሁን…አሁን… ከእግር ኳሱ
አካባቢ… ርቀሃል… ምነው በሠላም ነው…?

ኢንስትራክተር አብርሃም፡- ጥያቄህ በዚህ ቢታረም ደስ ይለኛል እኔ ከእግር ኳሱ
አልራኩም፤ ምንአልባት ከስታዲየም ወይም
ከክለብ አሰልጣኝነት ርቄ ካልሆነ በስተቀር፡
፡ ምክንያቱም ሁላችሁም እንደምታውቁት
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ችግር መሠረቱ
ነው፤ በሥራ በተግባር እንዳየሁት ችግሩን
ለመፍታት የበኩሌን ማድረግ አለብኝ በማለት
መሠረት በማንጠፍ ሥራ ላይ ጠንካራ
መሠረት እንዲኖረው ለማድረግ “ሀ” ብዬ
ጀምሬ በታዳጊዎች ሥልጠና ላይ እየሰራሁ
ነው፡፡ እንግዲህ እናንተ ጋዜጠኞችም ብዙ
ትኩረት ስለማታደርጉበት በወጣቶች ላይ
የሚሰራን ሥራ ሰው ብዛት ስለማያውቀው
የጠፋሁ መሰሎህ ይሆናል እንጂ ውሎዬና
አዳሬን በታዳጊዎች ላይ አድርጌ እየሠራሁ
ነው፡፡

ሀትሪክ፡- …እውነታው … አንተ
የምትለው ከሆነ ታዲያ… ሰሞኑን በአንተ
ፕሮጀክት ዙሪያ የሠማሁት ውሸት ነው
ማለት ነው…?

ኢንስትራክተር አብርሃም፡- …ምን
ሠማህ…?

ሀትሪክ፡- …አብርሃም የአዲስ አበባውን
ፕሮጀክት ዘግቶታል ብለውኝ… ማመን
አልቻልኩም…?

ኢንስትራክተር አብርሃም፡- …የተባለው
ትክክል ነው…፤ …የአዲስ አበባው የታዳጊዎች
ሥልጠና ሥራዬን ከዘጋሁት ሁለት ወር
አካባቢ ሆኖኛል፡፡

ሀትሪክ፡- የአዲስ አበባውን ፕሮጀክት
የዘጋህበት የተለየ ምክንያት አለህ?

ኢንስትራክተር አብርሃም፡- ሌላ ምንም
የተለየ ምክንያት የለውም፤ በሜዳ እጦት
ምክንያት ነው ሥልጠናውን ያቋረጥኩት፤
ላለፉት ሁለትና ሶስት አመታት ቦሌ
መድሃኒያለም ት/ቤት ነበር የምንሰራው፤
ምስጋና ለት/ቤቱ ዳይሬክተር አቶ
ዳንኤል ይግባና እሱ ተባብሮኝ እዛ ነበር
የምንሰራው፤በኋላ ላይ ከላይ መጣ በተባለ
ትዕዛዝ ሜዳው እንደማይከራይና መጠቀም
እንደማንችል ነገሩን፡፡ ያለ ሜዳ ታዳጊዎችን
ማሰልጠን የማይታሰብ ነው፡፡ አዲስ አበባ
ያለውን የሜዳ ችግር እንደምታውቀው ነው፡
፡ እየተከራየሁ፣ እየለመንኩ መስራት ከባድ
ሆነብኝ፤ በዚህና በዚህ ምክንያት ብቻ ነው
ያቋረጥኩት፡፡

ሀትሪክ፡- አብርሃም መቐሌ ላይ መሽጎ
ለመስራት ሲል ነው የአዲስ አበባውን
ማሰልጠኛ የዘጋው የሚለው ወሬ ታዲያ
ከምን መነሻነት ሊነሣ ቻለ?

ኢንስትራክተር አብርሃም፡- የአዲስ
አበባው መዘጋት ከመቐሌው ጋር የሚያገናኘው
ነገር የለም፤ የመቀሌውን የጀመርኩት
የአዲስ አባውን ከዘጋሁት በኋላ አይደለም፡
፡ መጀመሪያም ሁለቱም ጋር እየተመለላስኩ
ነበር የምሰራው፡፡ አሁንም ሃሳቤ ሁለቱን
ጎን ለጎን ለማስኬድ ነበር፤ ግን እንዳልካው
የሜዳ ችግር ትልቅ እንቅፋት ሆኖብኝ፤
በመቐሌ ግን ትልቅ ድጋፍ ነው እየተደረገለኝ
ያለው፡፡ የመቐለ ዩኒቨርስቲ ከፍተኛ ትብብር
እያደረገልኝ ነው፤ በተለይ ፕሮፌሰር ሂንዲያ
ባደረጉልኝ ቀና ትብብር ወደ 200 የሚጠጉ
ህፃናትን ይዤ ወደ አራት የሚጠጉ አሰልጣኞች
ተቀጥረው እየሠራን ነው፡፡ ለወደፊቱም ሰፋ
አድርገን የመስራት ሃሣቡ አለን፤አሁን ግን
የመቐሌውን አጠናክረን እየሠራን እንገኛለን፡፡

ሀትሪክ፡- …ገ/መድህን ኃይሌ ጅማ
አባጅፋርን ሻምፒዮን አድርጎ ወደ መቀሌ
ከተማ፣ ደደቢት የአዲስ አበባ ቡድንነቱንና
መቀመጫውን ትቶ ወደ መቀሌ አሁን ደግሞ
አንተም የአዲስ አበባውን ማሰልጠኛ ዘግተህ
ወደ መቀሌ… አብርሽ እንደው ደፊርከኝ
ካላልከኝ በስተቀር ይሄ አጋጣሚ ከወቅቱ
የፖለቲካ ጡዘትና መቀሌ ከመመሸግ ጋር አልተገጣጠመም…?

ኢንስትራክተር አብርሃም፡- …(በጣም
ሳቅ)… አንተ ነገሮችን ወዴት እየወሰድካቸው
ነው?…፤ …(አሁንም ሳቅ)…የማይገናኝ ነገር
ለማገናኘት እየሞከርክ ነው፡፡ ገ/መድህን ኃይሌ
ወደ መቐሌ የሄደው ከጅማ አባጅፋር በፊት
ቃል የገባላቸው ነገር ስላለ ይመስለኛል፣
ደደቢትም ወደዚያ የሄደው ተቸግሮ እንደሆነ
ነው የምገምተው፣ አብርሃምም ወደ መቐሌ
ያመራው እዚህ የገጠመው የሜዳ ችግር በዚያ
አካባቢ በቀላሉ በመቀረፉና በመቐሌ የእግር
ኳስ መነሳሳትና እያደገ የሄደበት ሁኔታ ስላለ
እንዲሁም በተለይ በህፃናት ላይ ለምሰራው
ሥራ ብዙ ድርጅቶች ድጋፍ ለመስጠት ፍላጎት
በማሳየታቸውና ሙያዊ ድጋፌን በተለይ
በህፃናት ላይ እንድሰጥ ፍላጎት በመታየቱ
ብቻ ነው ነገሮች ወደ መቐሌ ያመሩት፡፡
ከዚህ ውጪ ግን አንድ ያለው ሀቅ ምንድነው
የአካባቢው ተወላጅ በመሆኔ ጡረታ ስወጣ
ግን ወደ መቐሌ መሄዴ የማይቀር ነው፡፡
ምክንያቱም እናቴም ቤት ያለኝም እዚያው
ስለሆነ ከዚህ አንፃር ወደዚያ ላመራ እችላለሁ
መጨረሻ ላይ፡፡

ሀትሪክ፡-በመቐሌ እየሠራህ ያለኸው
የታዳጊዎች ስልጠና ውጤቶች ለትግራይ
ክለቦች ብቻ እንዲመግቡ ታስቦ ነው ?

ኢንስትራክተር አብርሃም፡- …(እየሳቀ)…
አንተ ሰውዬ ጥያቄዎችህ ጤነኛነት ይጎላቸዋል
ልበል?… (አሁንም ሳቅ)…ለምን ለመቐለ
ብቻ…? …ከተሰካልኝ ለአለም፣ ለአውሮፓ
ታርጌቴ እዛ ድረስ ነው፡፡ በአምስትና በ10
አመት ጊዜ ውስጥ አንድ ሁለት ወጣቶች
ሜድትሪያንን ተሻግረው አውሮፓ ውስጥ
ሲጫወቱ ማየት ነው ህልሜ እንጅ ፍራንክ
እየለቃቀምኩ በዚያች በማገኛት ገንዘብ
ለመጦር አይደለም የምሰራው፡፡

ሀትሪክ፡- አንተ ወደ ታዳጊዎች
ስልጠና ፊትህን ለማዞር ከመወሰንህ በፊት
በበርካታ ክለቦች የምትፈለግ ስመ ጥር
አሰልጣኝ ነበርክ፤ በአሰልጣኝነት በሚሊዮን
የሚቆጠር ብር በሚታፈስበት ጊዜ ሲነየር
ክለቦችን ማሰልጠን በቃኝ ብለህ ታዳጊዎችን
ለማሰልጠን ማሰብህ በተለይ ከገቢ አንፃር
ለመወሰን አልተቸገርክም?

ኢንስትራክተር አብርሃም፡- በጣም ከባድ
ነው፤ ብዙ ሰዎችም ውሳኔዬን ከዕብደት ጋር
ያያዙቱም ነበር፡፡ በተለይ ደግም የአሰልጥንልን
ጥያቄ ከበርካታ ክለባች እየመጣ፣ ቆጥሬው
ሳይሆን ፅፌው እንኳን የማላውቀው ሚሊዮን
ብሮች እየቀረቡልኝ ስገፋ የታዘቡ ጤነኝነቴን
ሁሉ እስከመጠራጠር ደረሰው ነበር፡፡ በጣም
ቅርብ ከሆኑኝ ሰዎች ጋርም የሃሣብ ጦርነት
ውስጥ እስከመግባትም ደርሼ ነበር፤ ገና
ከመነሻው ይሄንን ውሳኔ ስወስን ብዙዎች
እንዳሰቡት የክለብ አሰልጣኝነቱን በማቆሜ
በተለይ በኢኮኖሚ በኩል የደረሰብኝን ጉዳት
አውቀዋለሁ፤ ምን እንደገጠመኝ፣ እኔና
ቤተሰቦቼ እንዴት እንደተሰቃየን ፈጣሪ ነው
የሚያውቀው። ኑሮ እየከበደኝ በመምጣቱ
ውሳኔዬ ልክ አልነበረም እንዴ? እስከማለት
ሁሉ ደርሼ ነበር፡፡ ምክንያቱም ከአንድ ክለብ
ሚሊዮን ብርና ደሞዝ በመቶና ሁለት መቶ
ሺዎች በምታፍስበት ጊዜ ጥለህ መውጣት
ከባድ ውሳኔ ነው፡፡ እኔ በኑሮዬ የሞላኝ
የተረፈኝ የተንደላቀቀ ኑሮ የምኖር አይነትሰውም አይደለሁም፤ እንደ አንድ ተራ
ዜጋ የምኖር ሰው ነኝ፡፡ ግን ለገንዘብ ብዬ
አዕምሮዬ የማያምንበት የተጨማለቀ ነገር
ውስጥ መቆየት የለብኝም ብዬ ጨክኜ ወደ
ታዳጊዎች ስልጠና ለመግባት ወስኜ ከስልጠና
ራሴን አገለልኩ፡፡

ሀትሪክ፡-ይሄን ሁሉ ገንዘብ ገፍተህ
ታዳጊዎችን ወደ ማሰልጠን ከባድ ውሳኔ
የገፋህ ዋናው ምክንያትህ ምንድነው…?

ኢንስትራክተር አብርሃም፡- በቃ…
የኢትዮጵያ እግር ኳስ እንኳን በዓለም በአፍሪካ
ደረጃ ተወዳዳሪ መሆን አልቻለም፤ እግር ኳሱ
ከማደግ ይልቅ ቁልቁል እየተንደረደረ እየወረደ
እያየሁ እዛ ውስጥ መቆየትና በደከመ እግር
ኳስ ደሞዝ እየበላሁ መኖርን ውስጤ
መቀበል አልቻለም፡፡ በየጊዜው ከአምሮዬ ጋር
እየተጣለሁ ሠላሜን እየተነጠኩ መኖርን
ውስጤ እሼ አላለም፡፡ በወረደ እግር ኳስ
ኪሴን እየሞላሁ ከአዕምርዬ ጋር እየጣለሁ
ከምኖር ለምን በኢትዮጵያ እግር ኳስ ችግር
ላይ በመስራት ገንዘብ አጥቼ እግር ኳሱን
በአቅሜ ለምን ለመታደግ አልሞክርም
አልኩና ታዳጊዎችን የማሰልጠን ሃብን ይዤ
መጓዝን መረጥኩ፡፡ ምክንያቱም የኢትዮጵያ
እግር ኳስ ችግር መሠረቱ ነው፤ ስለዚህ
መሠረት በማንጠፍ ሥራ ላይ መድከም
አለብኝ በማለት ለሀገሬ አንድ ጡብ ላስቀምጥ
ብዬ ወስኜ መንቀሳቀስ ጀመርኩ፡፡ የእግር ኳሱ
የመጀመሪያ ድክመታችን ወይም ሽንፈታችን
መሠረት ላይ ታዳጊዎች ላይ በትክክለኛው
መንገድ አለመስራታችን መሆኑን በስልጠና
ህይወቴና ወደተለያዩ ሀገሮች በሄድኩበት ጊዜ
ተረድቼዋለሁ፡፡ ስለዚህ በዚህ ላይ መድከም
አለብኝ አልኩ፡፡ በዚህ ውሳኔዬ መራብ
ካለብኝም እራባለሁ፤ግን ደግሞ ሁሌም
ከህሊና ወቀሳ አድናለሁ በማለት የቀረቡልኝን
የበርካታ ክለቦች ጥያቄና ሚሊዮን ብሮችን
ረግጬ ምንም ወደማይገኝበት የታዳጊዎች
ስልጠና አመራሁ፡፡ የአዕምሮዬን ሠላም
ለማግኘት ስል ይሄን ውሳኔ ባልወስን ኖሮ
ከደካማው እግር ኳስ ደሞዝ እያገኘሁ ሆዴን
እየሞላሁ መኖር እችል ነበር፡፡ ይሄንን ደግሞ
አዕምሬዬ እሺ ብሎ ሊቀበለው ስላልቻለ በዚህ
ደረጃ ገንዘብ ከማግኘት ይልቅ መራብ ይሻላል
ብዬ መርጬ ወደ ህፃናቶች ፊቴን ማዞርን
መርጫለሁ እንጂ ሚሊየነር የመሆን እድሉ
ነበረኝ፡፡

ሀትሪክ፡-በአሁኑ ሰዓት ከእግር ኳሱ
ይልቅ ተጠቃሚ የሚሆኑት አሰልጣኞችና
ኮሚቴዎች ናቸው፤ በተለይ አንዳንድ አልጣኞች
ከተጨዋቾች ገንዘብ በመቀራመታቸው በእግር
ኳሱ 40/60 የሚባል አሣፋሪ ነገርም እየሰማ
ነው፤ በእግር ኳሱ እንደአለፈ አሰልጣኝ ጥቂት
አሰልጣኞች በዚህ ደረጃ ዘቅጠው መገኘታቸው
ምን ስሜት ይፈጥርብሃል?

ኢንስትራክተር አብርሃም፡- መቼም ሰው
ስትሆን ህሊና የሚባል ነገር ሊኖርህ ይገባል፤
የምትሰማው ነገር እንደ አሰልጣኝ ያሳፍርሃል
ያሸማቅቅሃል፡፡ በዚህ ነገር የተነሣ ራሴን
እንደ አሰልጣኝ ለመቁጠር ራሴን አሰልጣኝ
ነኝ ብዬ ለመጥራት እስከማፈር ደርሻለሁ፡
፡ ዛሬ ዛሬ አሠልጣኝነት የተናቀ ሙያ
እየሆነ እየመጣ ነው፡፡ ዛሬ ሳር ቅጠሉ ንፋሱ
ሁሉ የሚያወራው ይሄን የዘቀጠ ነገር ነው፡
፡ ከዚህች ድሃ አገር በእግር ኳሱ ከአንድ
ቢሊዮን ብር በላይ እየፈሰሰ እግር ኳሱ ቁልቁል
ወርዶ የግለሰቦች ኪስ መደለቡ የሚያሳዝን
ነው፡፡ አንድ አሰልጣኝ እንዴት ተጨዋች
በላቡ በድካሙ ካመጣው ገንዘብ ያውም
40/60 ይካፈላል? ይሄ ነውር ብቻ ሣይሆን
ትልቅ ወንጀልም ነው፡፡ ዛሬ ከሚያገኘው
ገንዘብ የምንቀራመተው ተጨዋች እኮ
ቤተሰብ አለው፤ ነገ የጨዋታ
ዘመኑ ሲያልቅ ወይም በጉዳት ሲገለል እኮ ብሩን
ተቀራምተነው ለማኝ ዜጋ ነው የምናፈራው፡፡
አሁን በተጨዋቾችና በአሰልጣኞች መካከል
ያለው ጤናማ ያልሆነ ግንኙነት መነሻውም
ይሄ ነው፡፡ በዚህ በጣም ታፍራለህ፤
ለዚህም ነው እግር ኳሱ እየወረደ እዚህ
የተጨማለቀ ነገር ውስጥ ተቀምጬ ደሞዝ
እየበላሁ እየተጦርኩ አልኖርም፤ በሙስና
የተጨማለቀ እግር ኳስ ውስጥ ተዘፍቄ
ኑሮዬን ልገፋ በዚህ መንገድ በማገኘው ገንዘብ
ልጆቼን የማሳድግበት ሞራል የለኝም ብዬ
ከቦታው ዞር ማለትን የመረጥኩት፡፡

ሀትሪክ፡- በአሰልጣኝነት ዘመንህ
ክለብ ለመግባት ገንዘብ ተጠይቀህ ወይም
ሊሞዳሞዱህ የሞከሩ ሰዎች አጋጥመውህ
ያውቃሉ?

ኢንስትራክተር አብርሃም፡- …አረ
በፍፁም…! ምክንያቱም አይደፍሩኝም፤
አመራሩንም፣ ተጨዋቾቹንም በሚዲያም
ይሁን በሌላ ፊት ለፊት ደፍሬ ስለምናገር
እግዚአብሔር ይስጣቸው በዚህ ደረጃ
ደፍረውኝ አያውቁም፡፡

ሀትሪክ፡- ተጨዋቾችስ ሌላ ቦታ
በለመዱት መንገድ አንተጋ ለመግባት
የ40/60 ጥያቄ ያቀረቡበት አጋጣሚስ ገጥሞህ
ያውቃል?

ኢንስትራክተር አብርሃም፡- ተጫዋቾቹ
ጋም ተመሳሳይ ነገር ነው ያለው፤
ስፖርት ውስጥ ስትኖር ማን ምን
እንደሆነ ሁሉም ያውቃል፡፡ ከዚህ
መነሻነት እነሱም ስለሚያውቁኝ
በዚህ ደረጃ ደፍሮ የጠየቀኝ
ተጨዋች የለም፡፡ ከዚህ ውጪ
ደግሞ እኔ ደላላዎች ነን ባዮችን
አላስጠጋቸውም፡፡ በእነሱ የጥቅም
ኔትወርክ ውስጥም ሆኜ አልሰራም፡
፡ ተጨዋች እንኳን የምመለምለውና
ከክለብ ክለብ የማዛውረው በደላላ
ሳይሆን በራሴ በመሆኑ በዚህ
በኩል አልተነካካሁም፤
አልተደፈርኩም፡፡

ሀትሪክ፡-ሰሞኑን ግን ከዚህ
አንተ ከምትለው ነገር ጋር
የሚጋጭ አንድ ነገር ናሁ ቲቪ ላይ ቀርቦ
ነበር፡፡ ምናልባት ተከታትለኸው ይሆን?

ኢንስትራክተር አብርሃም፡- …(እንደመገ
ረም እያለ)… ምንድነው እሱ..? አረ
አልተከታተልኩም…?

ሀትሪክ፡- ቀደም ሲል ለመከላከያ፣
ሐዋሳ ከነማ…. የተጨዋተው ቢኒያም
(ግስላ) ከአሜሪካ በስካይፕ ገብቶ ከተጨዋች
ገንዘብ የሚቀበሉ 20 ሙሰኛ አሰልጣኞች
ብሎ የአልጣኞችን ስም ዝርዝር ሲዘረዝር
የአንተን ስም ያየሁት ይመስለኛል ብልህ ምን
ይሰማሃል…?

ኢንስትራክተር አብርሃም፡- …(አሁንም
በግርምት ውስጥ ሆኞ)… የማን የእኔን
የአብርሃም ስም?…እንዲህ ተብሎም ከሆነ
ለአብርሃም ተ/ኃይማኖት ገንዘብ ሰጠሁት
ካለ ሰው ጋር አገናኘኝ ማስረጃ አምጣ ነው
የምለው፤ መቼም የሰው ገንዘብን የሚያክል
ነገር በልቼ ረስቼዋለሁ አልልም፡፡ በነገራችን
ላይ ይሄ የምትለው ተጨዋች ከእኔ ጋር
አብሮ አልሠራም፡፡ አንድ ጊዜ ቡና ሊገባ
መጥቶ መመለሱን ነው የማውቀው፡፡

ሀትሪክ፡- ባለፈው በተካሄደው
የፌዴሬሽኑ ምርጫ ላይ ከትግራይ
ክልል ተወክለህ ወደ አመራርነት
እንደምትመጣ በስፋት ተወርቶ
ነበር፤ በኋላ ግን እንኳን ወደ
ምርጫ ልትመጣ ከትግራይ
ውክልና ሳታገኝ ቀርተሃል…
የዚህ ምክንያቱ ምን ነበር…?

ኢንስትራክተር አብርሃም፡- …ፖለቲከኛ አይደለሁማ…፤…
ፖለቲከኛ ስላልሆንኩ አልተወ
ከልኩም፡፡

ሀትሪክ፡- …ፖለቲካና ውክልናን ምን
አገናኛቸው…?…አልገባኝም…?

ኢንስትራክተር አብርሃም፡- በእግር
ኳሱ እንደዚህ አይነት ውክልና የሚፈቀደው
ለፖለቲኛ ከሆነ ውሎ አድሯል፤እኔም
ለመወከል ግዴታ ፖለቲከኛ መሆን ነበረብኝ፤
እኔ ደግሞ የስፖርት ሰው እንጂ ፖለቲከኛ
ስላልሆንኩ ከትግራይ ውክልና ማግኘት
አልቻልኩም፡፡ በአጭሩ የትግራይ ፌዴሬሽን
ነው ውክልና የነፈገኝ፤ የክልሉ ፌዴሬሽን
ውክልና እንዲሰጠኝ ብዙ ርቀት በመሄድ
የክልሉ የወቅቱ ፕሬዚዳንት አቶ አባይ
ወልዱ ድረስ ሄጄ ማመልከቻ አስገብቻለሁ፤
ግን ዞር ብሎ ያየኝ ሰው የለም፡፡ ለእግር ኳስ
አመራርነት የስፖርት ሰው የለም፡፡ ለእግር
ኳስ አመራርነት የስፖርት ሰው ሣይሆን
ፖለቲከኛ መሆን አለበት የሚሉ ሰዎች ካሉ
ቦታ አይኖርህም፤የሆነው ይሄ ነው፡፡

ሀትሪክ፡- …በዚህ መልኩ ከእጩነት
ውጪ መሆንህስ አሣምኖሃል…?

ኢንስትራክተር አብርሃም፡- …በፍፁም
አላሳመነኝም፤ የሚያስተምርም አይደለም፤
ግን ጊዜ እየጠበኩ ነው አንድ ቀን ይሄን
ሸፍጥ አወጣዋለሁ፡፡ ለሀገርም ለእግር ኳስም
ማሰብ ይሄ ነው ወይ? ብዬ ጠይቄ መልስ
የሚሰጥ አካል ሲኖር እጠይቃለሁ፤ ለጊዜው
ግን ከምርጫው በፊት ተሸንፌ መቀመጥን
ነው የመረጥኩት፤ ግን ይሄን ሁሉ ጊዜ
የሚፈታው ነው፡፡

ሀትሪክ፡- በውሳኔው ውስጥህ ክፉኛ
መጎዳቱን ንግግርህ ያሳብቅብሃል…፤ ውሳኔው
የማያሳምንህ ከሆነ ለምንድነው ውክልና
የተነፈኩት ብለህ ለምን አልጠየቅክም…?

ኢንስትራክተር አብርሃም፡- ከላይ
እንዳልኩህ የክልሉ ፕሬዚዳንት ድረስ ደብዳቤ
አስገብቼ ጠይቂያለሁ፤ ለምርጫው ለመወከል
የሚያስችለኝን ፕሮፓዛል ልኬ ራሴም
በአካል ሄጂ የሚመለከታቸውን ጠይቄያለሁ፡
፡ የሚገርምህ በዚሁ ጉዳይ የሚመለከተውን
አንድ ፀሐፊ አግኝቼ ጠየኩት ምን ብሎ
እንደመለሰልኝ ታውቃለህ? ̎አይ አንተ
ዝም ብለህ ነው የምትለፋው የምትመረጥ
አይመስለኝም˝ አለኝ፡፡ ለምን ስለው “ሌሎች
ተመርጠዋል” አለኝ፡፡ እነማን ናቸው ስለው
“አልነግርህም ምስጢር ነው̎ ብሎ ዘጋብኝ፡
፡ በዚህ ተስፋ ሣልቆርጥ የስፖርት ኮሚሽን
ኃላፊው ጠየኩት፤ መልስ አልሰጠኝም፡
፡ በአጭሩ የእኔ ጉዳይ የተዘጋ ፋይል
ሆነ፤ በዚህ የተነሣ ተውኩት ብቻ ሣይሆን
ለምርጫ ሳልቀርብ ውክልና ስጡኝ ባልኳቸው
መቀሌዎች ከምርጫው በፊት ተሸንፌ
መጣሁ፡፡ የነበረው ይሄ ነው ወደፊት ታሪክ
ይፈርደዋል፡፡

ሀትሪክ፡- በአሰልጣኝነት ዘመንህ
የማይረሣህ ትልቅ ደስታን አጎናፅፈኝ
የምትለው አጋጣሚ…?

ኢንስትራክተር አብርሃም፡- ከውስጤ
የማይጠፋ ትልቅ ደስታን በስልጠና ህይወቴ
አገኘሁ ካልኩ አስቀድሜ የምትጠራው ከሴቶች
ብ/ቡድን (ሉሲዎች) ጋር ያገኘሁትን ድል
ነው፡፡ የሴቶች ስለሆነ ነው መሠል በወቅቱ
ከፍ ያለ ትኩረት ተነፈገ እንጂ በትልቅነት
የማነሣው፣ የእግር ኳስ ደስታን ያገኘሁበት
አጋጣሚ ነበር፡፡ ያ ውጤት የተመዘገበው
ዛሬ ወንድም ሴትም አኩል ነው በተባለበት
የመንግሥት ካቢኔም 50 በመቶ ሴቶች
በሆኑበት በአሁን ሰዓት የመጣ ውጤት ቢሆን
ኖሮ ትልቅ ታሪክ ተደርጎ ይነሣ ነበር፡፡ ያኔ
የክለቦች ውጤት ከስኬትም በላይ ለወንዶቹ
(ዋልያዎቹ) መነቃቃትንም ትልቅ ተፅዕኖ
የፈጠረም ነበርና ትልቅ ቦታ አለኝ፡፡

ሀትሪክ፡- በእግር ኳስ አሰልጣኘነቴ
ያዘንኩበት የምትለው አጋጣሚ…?

ኢንስትራክተር አብርሃም፡- በእግር ኳስ
ከሚያስደስተው ይልቅ የሚያሳዝነው ሚዛን
ይደፋል፡፡ ግን ሁሌም ባሰብኩት ቁጥር
ልቤን በሀዘን የሚያደማው የጉና እግር ኳስ
ክለብ ጉዳይ ነው፡፡ የጉናን ነገር ባሰብኩት
ቁጥር በጣም ነው የማዝነው፤ የጉናን ቡድን
ከምንምነት አንስትን እነ አል-አህሊን የመሰሉ
የአህጉሪቱ ታላላቅ ቡድኖች የሚሳተፉበት
የአፍሪካ የክለቦች ሻምፒዮና ውደድር ላይ
አድርሰንው ተፈረካክሶ ታሪክ ሆኖ መቅረቱ
ሁልጊዜ ያስቆጨኛል፡፡ ጉና በኢትዮጵያ እግር
ኳስ የራሱን አሻራ ያስቀመጠ እነ ዳንኤል፣
የማነ፣ ሚኬኤሌ፣ መኮንን፣ ጥላሁን (በረኛ)
፣ተካ ገ/መድህን እነ እስጢፋኖስን የመሳሰሉ
ታላላቅ ተጨዋቾችን ለሀገር ያፈራ ምርጥ
ቡድን ነበር፡፡ ስለ ጉና ባሰብኩ ቁጥር ከልቤ
አዝናለሁ፡፡

ሀትሪክ፡-የእኔ ትልቁ አሰልጣኝ ነው ብለህ
የተለየ ቦታ የምትሰጠው ለማን ነው..?

ኢንስትራክተር አብርሃም፡- በእርግጥ
አላሰለጠነኝም…!…ያም ቢሆን ግን
ለኢንስትራክተር መግሥቱ ወርቁ ገደብ
የሌለው አድናቆት ነው ያለኝ፡፡ ብዙዎች
ስለ ተጨዋችነት ችሎታው ስለ አሰለጣጠኑ
ስለውጤታማነቱ የሚናገሩትን ስሰማ ስለ እሱ
የበለጠ ክብር እንዲኖረኝ አድርጓል፡፡ ካይሮ
ለካፍ ስልጠና በሄድኩበት ጊዜ ስለ መንግሥቱ
ያልተነሣበትን ጊዜ አላስታውስም፡፡ “እናንተ
ጥሩ ተጨዋች፣ የእግር ኳስ መምህር
አሰልጣኝ ነበራችሁ” ሲሉኝ ክብር ብቻ ሣይሆን
እቆጫለሁ፡፡ በደንብ አግኝቼው በእግር ኳስ
ቋንቅ ባለማውራቴ በጣም እቆጫለሁ፡፡ ግን
አንድ መፅናኛዬ አንድ ጊዜ ወደ ብራዚል
ልሄድ ስል አግኝቼው አውርቼዋለሁ፡፡
መግሥቱ በቅርበት አያውቀኝም ግን አንዴ
የእሱን ምክርና ልምድ ፈልጌ አግኝቼው
መንጌ ብራዚል ልሄድ ነው፤ እንዴት ልማር?
ምን ላድርግ? ብዬ ጠይቄው “አንተ እድለኛ
ሰው ነህ እኛ ያላገኘነውን ትልቅ እድል ነው
ያገኘኸው̎ ብሎ ቁም ነገር ያለው ምክሮኛል፤
ከመንጌ ውጪ እንደዚህ ነው የምለው
አሰልጣኝ የለም።

ሀትሪክ፡- ከባህር ማዶስ የትኛው
አሰልጣኝ ቀልብህን ይስባል…?

ኢንስትራክተር አብርሃም፡- ለማንቸስተሩ
ስር አሌክስ ፈርጉስን ክብም ፍቅርም አለኝ፡
፡ የሥራ ዲሲፒሊኖቸው፤ አንድ ቦታ
ተረጋጋቶ ውጤት ማምጣት እንደሚቻል
የክለቡን ታላቅነት እንዴት ማስቀጠል
እንደሚቻል በረዥሙ የስልጠና ህይወታቸው
ትምህርት የሰጡ ሰው በመሆናቸው በዛ
ያለ አክብሮት አለኝ፡፡ አሁን አሁን ደግመ
የጋርዳዮላ “የስልጠናና የአጨዋዋት ፍልስፍና
ይማርከኛል” የእግር ኳስን ደረጃም ያሰማ
አሰልጣኝ ነው፡፡ ?

ሀትሪክ፡-በሀገርና በክለብ ደረጀ ድጋፍህን
ያለስስት የምትሰጠውስ ለማነው…?

ኢንስትራክተር አብርሃም፡– ባርሴሎና
ቀድመው ምርጫዬ ነው አሁን ቀደም
ሲል በእነ ዮኸን ክራይፍ የተነሣ ልቤ ወደ
ሆላንድ ያደላ ነበር፡፡ አሁን ከክለብ ባርሴሎና
እየደከሙ በመጡብኝም ወደ ብራዚል ብ/ቡድን
አደላለሁ፡፡

ሀትሪክ፡-ከተጨዋቾችስ?

ኢንስትራክተር አብርሃም፡- ኦው…
ለብራዚላዊው ሮናልዲሆ ጎቾ የተለየ ቦታ
አለኝ፡፡ ለሜሲም እንደዚሁ አድናቆት አለኝ፡
፡ ሮናልዲኒሆ ጎቾን ግን ሲጫወትም ልምምድ
ሲሰራም በአካል ስላየሁት ለዚህ ተዓምረኛ
ተጨዋች የተለየ አድናቆት አለኝ፡፡ እንደነዚህ
አይነት ተጨዋች እግር ኳስን በፍቅር
እንድትወድ የማስገደድ ውሳኔ የማስቀየር
አቅም ያላቸው ናቸው፡፡

ሀትሪክ፡- “በደንቃራ በቅሎ ቃጭል
ተጨምሮ” እንደሚሉ አበው በደካማው እግር
ኳሳችን ላይ የዘር ችግር ገብቶበት ውድድሮች
እየተሰረዙ፣ ስታዲየሞች ዘር ተኮር የሆኑ
አስፀያፊ ስድቦች የሚደመጡበት ቦታ ከሆነ
ውሎ አድሯል፡፡ በዚህ ላይ አንተ ምን
ትላለህ….?

ኢንስትራክተር አብርሃም፡- ከሁሉም
ነገሮች ከባዱና አሳሳቢው ለደካማው እግር
ኳሳችን ሌላው ፈተና ሆኖ ብቅ ያለው ደግሞ
ይሄ ነው፡፡ “እከሌ ቡድን አይምጣብኝ፤ ወይም
ወደ እከሌ ክልል አልሄድም”፣ በሁለቱ ክልሎች
መካከል ባለ ችግር ውደድሮች ተቋርጠዋል
መባሉ የክልል መንግሥታት ሳይቀር በጉዳዩ
ላይ የገቡበት ዘመን ላይ መድረሳችን በጣም ነው
የሚያሳፍረው፡፡ እግር ኳሱ ለዘመናት ጠፍሮ
ከያዘው ችግር ሳይላቀቅ ራሳችን በፈጠርነው
ሌላ ችግር መቀፍደዱ በጣም በጣም ነው
የሚያሳዝነው ይሄንን ስሰማና ሣይም በጣም
አፍራለሁ ኢትዮጵያ እኮ የአፍሪካ እምብርት
ናት፤ እኛ ለአፍሪካ ስለነፃነት ስለወንድምነት
ሁሉም ኃይማኖቶች በእኩል የሚኖሩባት
ሀገር መሆንዋን ለአፍሪካ ያስተማረን አፍሪካን
አንድ ያደረግን አፍሪካዊያንን ለነፃነታቸው
ያገዝን ነን፡፡ ለአፍሪካ እዚህ መድረስ ትልቁን
ሚና የተጫወቱት የእኛ መሪዎች ናቸው፡፡
ኃይለ ስላሴ፣ መንግሥቱና መለስ ለአፍሪካ
ጥሩ ሥራ ሠርተዋል፡፡ እነዚህን ሰዎች
ያፈራች ለአሀገሪቱ ትልቅ ሚናን የተጫወተች
ሀገር ዛሬ ወደ ኋላ መመለሷን የሚያሳይ
አሣፋሪ ነገር ውስጥ መግባቷ ያውም ከዘር
ከሃይማኖት ነፃ በሆነው ስፖርት እዚህ ውስጥ
መዘፈቋ የሚያሳዝን አንገት የሚያስደፋ
ነው፡፡ ዘር ስፖርት ውስጥ ገብቶ ውድድር
እስከማቋረጥ መድረሱ በምንም ሁኔታ
አይደገፍም፡፡ ስፖርት ውስጥ ዘርን ፖለቲካን
ጨምረው የሚያተራምሱ ወገኖች እጃቸውን
ሊሰበስቡ ስፖርቱን ለቀቅ ሊያደርጉት ይገባል፡
፡ ስፖርቱን እንዴት እናሳድገው የሚል
ቁጭት በሁላችንም ውስጥ ሊፈጠር ሲገባ
ኋላቀር በሆነ ነገር ውስጥ መዘፈቃችን
አዕምሮአችን አለመሰልጠኑን ስለሚያሳየኝ
ሁሉም ሊያውግዘው ይገባል፡፡

ሀትሪክ፡- በአሠልጣኝነት ህይወትህ በጉና
መፍረስ በጣም እንዳዘንክ ተናግረሃል በአንድ
ወቅት ግን የአየር ኃይል አዛዥ የሆኑት
ወንድምህ ሜጀር ጄኔራል አበበ ተ/ኃይማኖት
በኢህአዲግ የፖለቲካ መከፋፈል ከኃላፊነት
በመነሳትቸው አኩርፈህ ቡድኑ ሀገር
በወከለበት አመት እንዲወርድ አድርገሃል
በሚል መታማትህን ታውቃለህ….?

ኢንስትራክተር አብርሃም፡- … (በጣም
ሳቅ)… አንተ ጉደኛ ሰው ነህ… (አሁንም ሳቅ)… ይሄንን ደግሞ ከየት አገኘኸው…?
ያነሣኸው ነገር እውነትነት አለው በዚህም
ተወንጂያለው፡፡ ነገሩ እንዴት መሰለህ ጉና
በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ በአፍሪካ የክለቦች
ሻምፒዮና ላይ ተሳትፎ በዚያው አመት
ክለቡ ወረደ፡፡ በወቅቱ ያጠፋነው ትልቅ
ጥፋት እዛ ያደጉትን ተጨዋቾች ቀንሰን
ኢንተርናሽናል ልምድ ያላቸው በሚል
አዳዲስ ተጨዋቾችን አመጣን፡፡ በዚህ
የተነሣ ቡድኑ ከአዳዲሶቹ ጋር ሊዋሃድ
አልቻለም፡፡ ውጤት አጣን በመጨረሻም
እጣ ፈንታችን መውረድ ሆነ ወረድን፡፡
ይሄ የሆነው በ1994 ዓ.ም አካባቢ፡፡ ልክ
ቡደኑ በወረደበት አጋጣሚ ደግሞ የአየር
ኃይል አዛዥ የነበረው ወንድሜ በፖለቲካው
መከፋፈል የተነሣ እሱም ከሥልጣን ወርዶ
ነበረና አብርሃም ጉናን ያወረደው ሆን ብሎ
ነው ወንድሙ ከኃላፊነት በመነሣቱ አኩርፎ
ወይም መበቀሉ ነው ተብሎ በጣም ተወራ፡፡
ወሬው ከወሬነት አልፎ የክልሉ ፕሬዚዳንት
የነበሩት አቶ ፀጋይ በርሄ ጋር ሁሉ ደረሰ፡
፡ እሣቸው “ይሄ አይገናኝም አብርሃምን
አውቀዋለሁ እንደዚህ የሚያደርግ ሰው
አይደለም” ብለው አዳኑኝ እንጂ ሆን
ተብሎ በህይወቴ ላይ የተቃጣ ሙከራ ነበር
የተደረገብኝ፡፡ ከዚያ በኋላ በጣም በመበሳጨቴ
እዚያ መቀመጥ የለብኝም ብዬ ወደ አዲስ አበባ
መጥቼ ኢትዮጵያ ቡና ገባሁ፡፡

ሀትሪክ፡- የቡና ቆይታህ እንዴት ነበር…?
ኢንስትራክተር አብርሃም፡-ኢትዮጵያ ቡና
በጣም ትልቅ ክለብ ነው፤ የበርካታ ደጋፊ
ባለቤት የሆነን ክለብ ማሰልጠን ትልቅ እድል
ነው፡፡ ግን እንደ እድል ሆኖ በክለቡ ብዙ
አልቆየህም 10 ወር ብቻ ነው የቆየሁት፡፡

ሀትሪክ፡- ለምን…..?

ኢንስትራክተር አብርሃም፡- በቡና
ተረጋግቼ እንዳልሰራ የሚፈልግ የሆነ ግሩፕ
ነበር፡፡ ይሄ ግሩፕ የስዩም ቲፎዞዎች ስለነበሩ
ስዩም እንዲመለስ እኔ ላይ የተለያዩ ጫናዎችን
ከማሳደር አልፈው ምራቅ እስከመታፋት
ደረሱ፡፡ በተለይ ከቀድሞ ክለቤ ጉና ጋር አበበ
በቂላ ስታዲየም ተጨዋተን 2ለ1 ከተሸነፍን
በኋላ ነገሮች ሁሉ መልካም አልነበሩም፡
፡ አስፀያፊ ቃላት ሲሰነዝሩብኝ በውጤቱ
ተበሳጭተው ነው ብዬ ዝም አልኩኝ፡
፡ እነሱ ግን በዚህ ሳይቆሙ ምርቃቸውን
እስከመታፋት ደረሱ፡፡ ያን ጊዜ ትዕግስትም
ልክ አለው እየተተፋብኝማ አላሰለንም ሰብዓዊ
ክብሬ ተጥሶ እየተተፋብኝ ከማሰለጥን ብለቅ
ይሻላል ብዬ በቡና 10 ወራትን ብቻ አሳልፌ
ወጣሁ፡፡

ሀትሪክ፡- ቡናን በዚህ መልኩ መልቀቅህ
ይቆጭሃል…?

ኢንስትራክተር አብርሃም፡-በመልቀቄ
ሣይሆን ይሄንን ትልቅ የኒውክላር ያህል
ትልቅ ኃይል ያለው ደጋፌ ከምኞቱ ከውጤት
ጋር ሳላገናኘው በመውጣቴ ብቻ ነው
የምንቆጨው፡፡ በቡና አሠልጣኝነቴ የደጋፊውን
የዋንጫ ጥም ሣልቆርጥ መውጣቴ ዛሬም
ድረስ ይቆጨኛል፡፡ የሚገርምህ ነገር ዛሬም
ድረስ ልጄ የቡና መዝሙር ከአፉ አይጠፋም፡
፡ እኔ የክለቡ አሰልጣኝ በነበርኩበት ወቅት
እቤት ለመነሳሳት ስሜት ውስጥ ለመግባት
መዝሙሩን እሰማው ስለነበር ያኔ በአዕምሮዋ
መዝሙሩ ታትሞ በመቅረቱ ዛሬም ስለ እግር
ኳስ ሲነሣ የቡና መዝሙር ከአፏ አይጠፋም፡፡

ሀትሪክ፡- ቡናን በማሰልጠንህ አገኘሁት፣
አሳካሁት የምትለው ነገር ምንድነው…?

ኢንስትራክተር አብርሃም፡- ወደ ቡና
ስመጣ ከፍተኛ ጫና እንዳለብኝ በጋለ ምጣድ
ላይ እንደምቀመጥ አውቄ ነው የመጣሁት፡
፡ ግን ቡናን ማሰልጠን ክብር ነው የዚህ
የሚያምር ደጋፊን ክለብ ከመምራት የበለጠ
ለአንድ አሠልጣኝ ትልቅ እድል የለም ብዬ
ነው የገባሁበት ቡናን በማሰልጠኔ ተምሬ
ተፈትኜ ነው የወጣሁት፡፡ እንደ አንድ
አሰልጣኝ ይሄን መሰሉ ፈተና መፈተንና
ጫናን መቋቋም ያስፈልጋል ለቀጣይ የስልጠና
ህይወትም ትልቅ ትምህርት የምታገኝበት
ነው፡፡ በቡና ውስጥ ማሸነፍና መሸነፍ
ያላቸውን ዋጋ የተረዳሁበት ቤትም ነው፡፡
ብዙ ደጋፊ የሌለበት ክለብ ውስጥ ስትሠራ
የማይታወቀውን አውቄበታለሁ፡፡ ከዚህ
በተረፈ ደጋፊው የድግፍ ድባቡ፣ መዝሙሩ
ለውጤት ያለው ጉጉት ያለህን እውቀት
እንዳትሰስት ምን ሠርቼ እንዴት አሸንፌ ነው
የማስደስተው ከዚህ እንድታስብም ለአፍህታም
እንዳታሸልብ ያደርግሀል፡፡

ሀትሪክ፡-የዛሬው ቆይታችንን በምስጋና
አጅቤ ከመቋጨቴ በፊት አብርሃም ኢንቨስተር
ለመሆን እየተንደረደረ ነው፤ በኢንቨስትመንት
ሥራ ተጠምዷል የሚል ወሬ ሰምቻለሁና
እውነት ውሸት ለሚለው መልስ ስጠኝና
እንለያይ…. ?

ኢንስትራክተር አብርሃም፡- … (በጣም
ሳቅ)… እውነት ነው በአቅሜ ኢንቨስተር
ለመሆንም እየተፍጨረጨርኩ ነው፡፡ መቐሌ
ላይ ባገኘሁት ቦታ የስፖርት ትጥቆች
ማምረቻ ፋብሪካን ለመክፈት እየተንደፋደፍኩ
ነው፡፡ አምላክ ከረዳኝ ይሄን አስቤያለሁ፡፡

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
Uncategorized

FIFA temporarily lifts transfer ban on St. George

Saint George's has had its transfer ban imposed by FIFA temporarily lifted...

Uncategorized

29ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች ዳግም ወንድሙ (ሀዲያ ሆሳዕና) : ክለቡ ከ መቐለ 70 እንደርታ...

Uncategorized

ሀይለየሱስ ባዘዘው ከዳኝነት አለም ራሳቸውን አገለሉ

ሀያ አምስት አመታቶችን በዳኝነት ያገለገሉት ዶ/ር ሀይለየሱስ ባዘዘው ከዳኝነት አለም በይፋ ማቆማቸውን...

Uncategorized

ወልዋሎ ወደ ግማሽ ፍፃሜው ማለፉን አረጋገጠ

በኢትዮጵያ ዋንጫ የሩብ ፍፃሜ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ወልዋሎ ዓ/ት ዩኒቨርስቲ በመለያ ምት...