መነሻ ገጽ መቐለ ከተማ ሪፖርት | ኢትዮጵያ ቡና በሜዳው ከጅማ አባጅፋር ነጥብ ሲጋራ፡ ወላይታድቻን ያስተናገደው መቀለ ከተማ ከሊጉ መሪ ጅማ አባጅፋር ያለውን የነጥብ ልዩነት አጥቧል፡፡
መቐለ ከተማሪፖርትኢትዮጵያ ቡና

ሪፖርት | ኢትዮጵያ ቡና በሜዳው ከጅማ አባጅፋር ነጥብ ሲጋራ፡ ወላይታድቻን ያስተናገደው መቀለ ከተማ ከሊጉ መሪ ጅማ አባጅፋር ያለውን የነጥብ ልዩነት አጥቧል፡፡

አጋራ
አጋራ

 

የ22ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ኘሪሚዬር ሊግ ከትናንት በስቲያ እና ትናንት የተካሄደ ሲሆን ዛሬም ቀጥሎ አዲስአበባ እና መቀለ ላይ በተካሄዱ 2 ጨዋታዎች የተመዘገቡት ውጤቶች ኘሪሚዬር ሊጉ ሁለት መልክ ይዞ እንዲዘልቅ የሚያደርግ ነው፡፡በደረጃ ሰንጠረዡ ከወገብ በላይ የተቀመጡት ክለቦች አሁንም በዋንጫው ፍክክር ውስጥ የመቆየት ዕድል ሲኖራቸው ከወገብ በታች ያሉት ለብቻቸው ሌላ ሁለት ምድብ ከተመዋል ፡፡አንደኛው ምድብ በወራጂ ቀጠና ሲገኝ ሌላኛው ምድብ በወራጂ ቀጠናው አፋፋ ላይ ሰፍሰዋል፡፡

ኢትዮጵያ ቡና ከ ጅማ አባጅፋር

☞በበርካታ ተመልካች ታጂቦ ሸገር ላይ ኢትዮጵያ ቡና በሜዳው የሊጉን መሪ ጅማ አባጅፋር ያስተናገደበት ተጠባቂ ጨዋታ ያለግብ አቻ ተጠናቋል፡፡

በፌደራል ዳኛ ማናዬ ወ/ፃድቅ በመሃል ዳኝነት የጀመረው ይሄው ጨዋታ ባለሜዳዎቹ ኢትዬጵያ ቡናዎች ከጨዋታው ጅማሮ አስከመጨረሻው ደቂቃ ግብ ለማስቆጠር በትልቅ ተነሳሽነት እና ፍላጎት የተጫዎቱ ሲሆን እንግዳዎቹ አባጅፋሮች በጨዋታው የማሸነፍ ፍላጎት ቢኖራቸውም ሜዳ ላይ የነበራቸው እንቅስቃሴ ግባቸውን ላለማስደፈር ቅድሚያ እንደገቡ የሚያታይ ነበር፡፡ቡናዎች ከባለፈው ሳምንት የሸገር ደርቢ ረጃጂም ኳስ ወጥተው በአጭርና ፈጣን የመልሶ ማጥቃት አጨዋወትን በመከተል ግብ ለማግኘት ቢጫዎቱም የጅማአባጅፋር ተከላካይ ክፍል ጥንካሬ እንዳለ ሁኖ የቡናዎች አጥቂ ክፍል ኳስን ወደ ግብ የመቀዬር ችግር ጎልቶ የሚታይ ነበር፡፡ቡናዎች በሙሉ ሰዓት ያደረጓቸው ኢላማቸውን የጠበቁ የግብ ሙከራዎችም ጥቂት ሲሆኑ ግብ ለማግኘት ወደ ፊት የሚያደርጉት ሽግግር በተጋጣሚዎቻቸው የአማካኝ ስፍራ ተጨዋቾች በተደጋጋሚ ይቋረጥ ነበር፡፡

ጅማ አባጅፋሮች ከተጋጣሚያቸው የሚነጥኩትን ኳስ ወደ ግብ ለመድረስ በሚያደርጉት እንቅስቃሴ አብዛኛውን በግራና ቀኝ መስመር በኩል ሰብረው ለመግባት ጥረት ያደረጉ ሲሆን ያምቢሆን ዛሬ ጥረታቸው ፍሬአፍርቷል ለማለትአያስደፍርም፡፡በጨዋታው ኢትዬጵያ ቡና በዋንጫ ፉክክሩ ከመቆየቱም ባለፈ መሪውን ጅማ አባጅፋር በማሸነፍ ያለውን የነጥብ ልዩነት እንደሚያጠብ ሲጠበቅ ፡የሊጉ ክስተት ጅማ አባጅፋር ቀጥተኛ ተፎካካሪውን ኢትዬጵያ ቡና አሸንፎ ከተከታዬቹ ያለውን የነጥብ ልዩነት ያሰፋል ተብሎ ሲጠበቅ የታሰበው ሁሉ ሳይሆን ሁለቱ ክለቦች ያለ ግብ ነጥብ ተጋርተው ወደ ዋንጫው የሚደረገው ጉዞ አሁንም ከአንድ ፈረስ ግልቢያ ይልቅ የበርካታ ፈረሶች መናጠጫ መሆኑ ሊጉ በየሳምንቱ ተጠባቂና የበርካቶችን ትኩረት እየሳበ መጥቷል፡፡

ሁለቱ ክለቦች ነጥብ መጋራታቸውን ተከትሎ ባለሜዳዎቹ ኢትዮጵያ ቡናዎች ነጥባቸውን 33በማድረስ በሰንጠረዡ 5ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጡ ጅማ አባጅፋሮች በ39 ነጥብ ሊጉን ይመራሉ፡፡

የአሰልጣኞች አስተያየት

አሰልጣኝ ዲዲዬ ጎሜስ – ኢትዮጵያ ቡና

ጨዋታውን ተቆጣጥረን ለመጫወት ያደረግነው ጥረት ጥሩ ነበር፡፡በተለይም በሁለተኛው የጨዋታ አጋማሽ የበለጠ ተሽለን ግብ ለማግኘት ብንጫዎትም ጎል አለማስቆጠራችን የፊት ክፍሉን ድክመት ለማሻሻል ብዙ መስራት እንዳለብን አመላካች ነው፡፡ተጨዋቾቸ ለማሸነፍ የነበራቸው ተነሳሽነት የሚያስደስት ነበር፡፡

አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ – ጅማ አባ ጅፋር

በጨዋታው የምንፈልገውን ውጤት አስመዝግበናል፡፡ከጨዋታው ሶስት ማግኘት እንደ አማራጭ ያሰብነው ነበር፡፡ግብ ላለማስተናገድ ጥንቃቄ መርጠን ተጫውተናል፡፡አለመሸነፋችን ለቀጣይ ጨዋታ ትልቅ ተቀሜታ ይሰጠናል፡፡

መቀለ ከተማ ከ ወላይታድቻ

☞በሜዳው ወላይታ ድቻን ያስተናገደው መቀለ ከተማ በሁለቱ የጨዋታ አጋማሽ ሁለት ጋናውያን ባስቆጠሩት ግብ ወላይታድቻን 2-0 በመርታት ከሊጉ መሪ ጅማ አባጅፋር ያለውን የነጥብ ልዩነት በማጥበብ ወደ ዋንጫውን የሚያደርገውን ጉዞ አጠናክሯል፡፡

ባለፈው ሳምንት ሁለቱም ቡድኖች ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈው ሲገናኙ ትልቅ ፉክክር እንደሚስተናገድበት የተጠበቀው ጨዋታ በመጀመሪያው የጨዋታ አጋማሽ እንግዳዎቹ ድቻዎች የኳስ ቁጥጥሩን የበላይነት በመውሰድ ግብ ለማስቆጠር ሲሞክሩ በባለሜዳዎቹ መቀለዎች የሚሰነዘርባቸውን ጥቃት በጥብቅ በመከላከሉ በኩል ጥሩ ነበሩ፡፡መቀለዎች የተወሰደባቸውን የመሃል ሜዳ የበላይነት የሇላ ሇላ ቢመልሱም ከዚህ አሰቀድሞ ጨዋታው ሃይል የተቀላቀለበት ስለነበር የወላይታ ድቻዎቹ የጀርባ አጥንት የሆነው ጀኮ አረፋት እንዲሁም አመለ ሚልኪያስ በጉዳት ተቀይረው ሲዎጡ ሜዳ ውስጥ የቆዩት ለ10ደቂቃ ብቻ ነበር፡፡

ጨዋታው ሲቀጥል ድቻዎች መሃል ሜዳው ላይ የነበራቸውን ብልጫ ሲነጠቁ ግባቸውም በተደጋጋሚ የግብ ሙከራዎችን ሲያስተናግድ በወንደሰን ገረመው ድንቅ ብቃት ኳሶች ቢመክኑም መቀለዎች በ26ኛው ደቂቃ ፉሴይኒ በመስመር በኩል ወደ ግብ ያሻገረውን ኳስ አቼምፖንግ በጭንቅላቱ በመግጨት ቡድኑን ቀዳሚ አድርጓል፡፡

ከግቧ መቆጠር በሇላ ድቻዎች የአቻነት ግብ ፍለጋ ወደ መቀለ የግብ ክልል ቢደርሱም የሚያደርጓቸው የግብ ሙከራዎች ያን ያህል ያለቀላቸውም አልነበሩም፡፡ይልቁንም ድቻዎች ግብ ለማግኘት ግባቸውን ለቀው በሚዎጡበት ቅፅበት በተጋጣሚያቸው የሚሰነዘርባቸው የግብ ሙከራ አስፈሪ ነበር፡፡በሁለተኛው አጋማሽ ወላይታድቻዎች የአቻነቷን ግብ ለማግኘት ሲንቀሳቀሱ ገና በጊዜ በ49ኛው ደቂቃ የመቀለ ከተማው ሌላኛው ጋናዊ ፉሴይኒ ከርቀት ከመረብ ጋር ያገናኛት ግብ የቡድኑን መሪነት ወደ ሁለት ከፍ ስታደርግ ግቧ በድቻዎች ላይ ይዛ የመጣችው የስነልቦና ጫና ትልቅ ነበር፡፡

በጨዋታው ባለሜዳዎቹ መቀለዎች ሌላ ግብ ያክላሉ ወይስ ወላይታ ድቻ ግብ አስቆጥሮ ጨዋታው ሌላ መልክ ይዞ ይቀጥል ይሆን ተብሎ ሲጠበቅ ቀሪ የድቻዎችም ሆኑ የመቀለዎች የግብ ሙከራ ተሳክቶ ኳስ ከመረብ ጋር ሳይገናኝ ጨዋታው በባለሜዳዎቹ መቀለ ከተማዎች 2-0አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡
በጨዋታው ውጤት መቀለ ከተማ 2 ቀሪ ተስተካካይ ጨዋታ እያላቸው ከመሪው ጅማ አባጅፋር ያለቸውን የነጥብ ልዩነት ወደ 4 ዝቅ በማድረግ በ35 ነጥብ 2ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጡ ወላይታ ድቻዎች 2ቀሪ ተስተካካይ ጨዋታው እያላቸው በ27 ነጥብ በነበሩበት 9ኛ ደረጃ ቆይተዋል፡፡

የአሰልጣኞች አስተያየት

አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ-መቐለ ከተ

በጨዋታው መጀመሪያ እነሱ የተሻሉ ቢሆኑም ቀስ በቀስ ወደ ጨዋታው በመመለስ ግብ አስቆጥረናል፡፡የተሻልን ስለነበርን አሸንፈናል፡፡በውጤቱ ደስ ብሎኛል ፡፡ደጋፊዎቻችንም ማመስገን እፈልጋለሁ፡፡

አሰልጣኝ ዘነበ ፍስሀ-ወላይታ ድቻ

በጨዋታው ተጋጣሚዎቻቸውን መቀለዎች የተሻሉ ስለነበሩ አሸንፈውናል፡፡የጨዋታው ውጤቱም ይገባቸዋል፡፡እናም እንኳን ደስ አላችሁ ማለት እፈልጋለሁ፡፡

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ኢትዮጵያ ቡና የፋይናስ ችግር እንገጠመው ተገለፀ

ኢትዮጲያ ቡና ካለበት የፋይናንስ ቀዉስ ለማዉጣት ከቡናዉ ሴክተር የሚገኘዉ ገንዘብ መጨመር አለበት...

ኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

“ኢትዮዽያ ቡናን ብትነኩ ከመቃብሬ ተነስቼ አጠፉቹሀለው” መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ

በዛሬው ዕለት ኢትዮጵያ ቡናን ከምስረታው አንስቶ በተለያዩ ሀላፊነት ከአርባ አመት በላይ መርተው...

ኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዝውውር ዜናዎች

በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?

የግብ ዘቡ የመዲናይቱን ክለብ በድጋሚ ሊቀላቀል ነው። በአሰልጣኝ ሳምሶን አየለ የሚመሩት ኢትዮጵያ...