በአቤኔዘር አበበ
በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ኢትዮጵያ ቡናን 1-0 በማሸነፍ ወሳኝ ሦስት ነጥቦችን አሳክቷል።

በጨዋታው የመጀመሪያ አጋማሽ ሁለቱም ቡድኖች የግብ ዕድሎችን ቢፈጥሩም በተለይ ኢትዮ ኤሌክትሪክ በመስመር በኩል ያደረጋቸው የማጥቃት እንቅስቃሴዎች የተሻሉ ነበሩ። ቡድኑ በጨመረው ጫና የግብ ማስቆጠሪያ ዕድል ፈጥሮ፣ አሸናፊ ተገኝ ያሻማውን ኳስ አቤል ሀብታሙ በ45+2ኛው ደቂቃ በግሩም ሁነታ የግንባር ኳስ ወደ ግብነት በመቀየር ቡድኑን መሪ አድርጓል። የመጀመሪያው አጋማሽም በዚሁ ውጤት ተጠናቋል።ከዕረፍት መልስ ኢትዮጵያ ቡና ወደ ጨዋታው በጠንካራ ጫና ተመልሶ በተደጋጋሚ ወደ ተጋጣሚው የግብ ክልል ቢደርስም የፈጠራቸውን ዕድሎች ወደ ግብነት መቀየር አልቻለም። ኢትዮ ኤሌክትሪክ በተደራጀ የመከላከል አጨዋወት የቡናን ጥቃቶች በመመከት የአንድ ግብ መሪነቱን እስከ መጨረሻው ማስጠበቅ ችሏል
ኢትዮጵያ ቡና 0-1 ኢትዮ ኤሌክትሪክ
⚽️ አቤል ሀብታሙ 45+2′
አስተያየት ይስጡ