መነሻ ገጽ ዜናዎች ነገሌ አርሲ አዳማ ከተማን ስያሸነፊ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስና ሸገር ከተማ ነጥብ ተጋሩ
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ነገሌ አርሲ አዳማ ከተማን ስያሸነፊ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስና ሸገር ከተማ ነጥብ ተጋሩ

አጋራ
አጋራ

በአቤኔዘር አበበ

ነገሌ አርሲ በዴሴሬ ፓስካል ብቸኛ ግብ አዳማ ከተማን 1ለ0 በማሸነፍ ሙሉ ሦስት ነጥብ ሲያሳካ ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስና ሸገር ከተማ 2ለ2 ተለያይተዋል።

ነገሌ አርሲ በጨዋታው የኳስ ቁጥጥሩን በመያዝ የተሻለ አቀራረብ ያሳየ ሲሆን፣ በ33ኛው ደቂቃ ከቤ ቡዙነህ ያሻገረውን ኳስ ዴሴሬ ፓስካል ወደ ግብነት በመቀየር ቡድኑን መሪ አድርጓል። የመጀመሪያውም አጋማሽ በነገሌ አርሲ 1ለ0 መሪነት ተጠናቋል።
በሁለተኛው አጋማሽም ነገሌ አርሲ የኳስ ቁጥጥሩን በመያዝ ቢጫወትም ተጨማሪ ግብ ማስቆጠር አልቻለም። አዳማ ከተማም አቻ ለመሆን ያደረገው ጥረት ሳይሳካለት ጨዋታው በነገሌ አርሲ 1ለ0 አሸናፊነት ተጠናቋል።

ቅዱስ ጊዮርጊስ 2–2 ሸገር ከተማ

በሌላኛው የዕለቱ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስና ሸገር ከተማ በተመሳሳይ የግብ ብዛት 2ለ2 ተለያይተዋል።
ቅዱስ ጊዮርጊስ በጨዋታው መጀመሪያ ኳስን ተቆጣጥሮ ወደ ተጋጣሚው የግብ ክልል በተደጋጋሚ ቢደርስም፣ ሸገር ከተማ በ29ኛው ደቂቃ የሁለቱ ተከላካዮች አለመግባባት ተጠቅሞ በአሚር አብዶ ግብ ቀዳሚ ሆኗል። የመጀመሪያው አጋማሽም በሸገር ከተማ 1ለ0 መሪነት ተጠናቋል።
ከዕረፍት መልስ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጫናውን በማሳደግ በ51ኛው ደቂቃ በአማኑኤል ኤርቦ አማካኝነት የአቻነት ግብ አስቆጥሯል። በ73ኛው ደቂቃም ናትናኤል ዳንኤል ቅዱስ ጊዮርጊስን መሪ አድርጓል።
ሸገር ከተማ ግን ተስፋ ሳይቆርጥ ባደረገው ጥረት በ79ኛው ደቂቃ በቢንያም ፍቅሩ አማካኝነት የአቻነት ግብ በማስቆጠር ነጥብ መጋራት ችሏል። ጨዋታውም 2ለ2 በሆነ ውጤት ተጠናቋል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...