በአቤኔዘር አበበ
የጦና ንቦቹ በርበሬዎቹን 6ለ0 በሆነ ውጤት አሸነፉ!

በጥሩ ፉክክር በተጀመረው ጨዋታ ወላይታ ድቻ በ25ኛው ደቂቃ ሱሌማን ሀሚድ ከሳጥን ውጭ በርቀት በመምታት ባስቆጠረው ግብ መሪነቱን ያዘ። በጫናው የቀጠለው ቡድኑ በ36ኛው ደቂቃ መሳይ ሰለሞን ባስቆጠረው ግብ የመጀመሪያውን አጋማሽ 2-0 በሆነ ውጤት መርቶ አጠናቋል።ከዕረፍት መልስም የጦና ንቦቹ የበላይነታቸውን አስቀጥለዋል። በ48ኛው ደቂቃ መሳይ ሰለሞን የግሉን ሁለተኛ ግብ ሲያስቆጥር፣ በ55ኛው ደቂቃ ቴዎድሮስ ታፈሰ የቡድኑን አራተኛ ግብ አከለ።ጫናውን ያልቀነሰው ወላይታ ድቻ በ76ኛው ደቂቃ በያኦቪ ጆሴፍ አማካይነት አምስተኛ ግቡን አስቆጠረ። በ82ኛው ደቂቃ ደግሞ የሀላባ ከተማ ግብ ጠባቂ ራያን ኦቢን ከሳጥን ውጭ ኳሱን በእጁ በመንካቱ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናበተ።በጨዋታው መጨረሻ መሳይ ሰለሞን ሦስተኛ ግቡን በማስቆጠር ሀትሪክ ሰርቷል። በዚህም ወላይታ ድቻ 6-0 በሆነ ውጤት አስደናቂ ድል በማስመዝገብ ጨዋታውን አጠናቋል።
አስተያየት ይስጡ