በሊጉ የሦስተኛ ሳምንት የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ነገሌ አርሲ 3ለ0 በሆነ ውጤት ኢትዮጵያ ቡናን በማሸነፍ የአመቱን የመጀመሪያ ድል አግኝቷል።

በመጀመሪያዎቹ አስራ አምስት ደቂቃዎች ቡናማዎቹ ጥሩ አጀማመርን በማድረግ በይበልጥ ሦስተኛው ሜዳ ላይ በድግግሞሽ መታየት ቢችሉም ዳንኤል ዳርጌ ያለቀለት ዕድልን አግኝቶ ጋናዊው የግብ ዘብ እድሪሱ አብዱላሂ ካመከናት አጋጣሚ በኋላ በሽግግር የጨዋታ መንገድ ከመስመር ከመስመር መነሳት መርጠው መንቀሳቀስን የመረጡት ነገሌ አርሲዎች የቡናማዎቹን የመከላከል ድክመት ተጠቅመው መሪ መሆን ችለዋል።
20ኛው ደቂቃ ከእጅ መነሻዋን አድርጋ ከቤ ብዙ ብዙነህ በጥልቀት ወደ ሳጥን ይዞ የገባትን ኳስ ራምኬል ጀምስ ወደ ውጪ ያወጣት ትመስል የነበረችን ኳስ ከቤ ፈጥኖ ደርሶ ወደ ውስጥ መሬት መሬት አሻግሮ አጥቂው ገብረመስቀል ዱባለ መረብ ላይ በማሳረፍ ሰጎኖቹን መሪ ማድረግ ችሏል።
በኳስ ቁጥጥሩ ብልጫውን ይወሰዱ እንጂ ጥንቃቄ ላይ ደካማ የነበሩት ኢትዮጵያ ቡናዎች ሁለተኛ ጎል ለማስተናገድ ተገደዋል። 28ኛው ደቂቃ በረከት ግዛው አሾልኮ የሰጠውን ኳስ ገብረመስቀል ዱባለ ለማግኘት ወደ ሳጥን ሲያመራ በአምበሉ ራምኬል ጀምስ መጠለፉን ተከትሎ የዕለቱ ዋና ዳኛ ሔኖክ አበበ የሰጡትን የፍፁም ቅጣት ምት አማካዩ ዳዊት ተፈራ አቡበከር ኑራ መረብ ላይ በማሳረፍ ጨዋታው በነገሌዎች 2ለ0 ውጤት ተጋምሷል።
ከዕረፍት ጨዋታው ሲመለስ በይበልጥ ወደ ቅኝት ውስጥ ለመግባት የተጫዋች ለውጦችን በማድረግ የቀጠሉት ኢትዮጵያ ቡናዎች እንደነበራቸው የሜዳ ላይ ብልጫ ግን የተጋጣሚያቸውን ሦስተኛው የሜዳ ክፍል ላይ ሲደርሱ ጥድፊዎቻቸው ጥራት ያላቸውን ዕድሎች መፍጠር እንዳይችሉ ሲያደርጋቸው በአንፃሩ ነገሌ አርሲዎች ያስቆጠሩት ጎል በማስጠበቅ በመልሶ ማጥቃት ለመጫወት ያደረጉት ጥረት ተሳክቶላቸው ድልአዲስ ገብሬ በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች ተስፋዬ አሸብር ላይ በሳጥን ውስጥ ጥፋት በመስራቱ የተሰጠውን የፍፁም ቅጣት ምት ጋናዊው አጥቂ ኮሊንስ ኮፊ በማስቆጠር ድልአዲስ ገብሬም በቀጥታ ቀይ ከሜዳ ከወጣ በኋላ በመጨረሻም ጨዋታው በነገሌ አርሲ 3ለ0 አሸናፊነት ተጠናቋል።
አስተያየት ይስጡ