መነሻ ገጽ ዜናዎች ሀዋሳ ከተማና ንግድ ባንክ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስና አዳማ ከተማ ነጥብ ተጋሩ
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀዋሳ ከተማና ንግድ ባንክ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስና አዳማ ከተማ ነጥብ ተጋሩ

አጋራ
አጋራ

በክፋያ ምክያት 7 ተጫዋች ሳይዝ የገባው ሀዋሳ ከተማ ነጥብ ተጋራ!ቅዱስ ጊዮርጊስ የበላይነት በወሰደበት ጨዋታ ከአዳማ ከተማ ነጥብ አቻ ተለያይተዋል

ሀዋሳ ከተማ በተከታታይ ሶስት ጨዋታ በሜዳው ሶስት ነጥብ ማሳካት ተስኖታል።

ጨዋታው በተጀመረ በ4ኛው ደቂቃ ዴቪድ ኦፓንግ በጌታነህ ከበደ ላይ በሠራው ጥፋት ሀዋሳ ከተማ የፍጹም ቅጣት ምት አገኘ። ጌታነህነ ከበደ ቅጣት ምቱን ወደ ግብነት በመቀየር ቡድኑን መሪ አደረጓል የመጀመሪያ አጋማሽ በዛ ውጤት ተጠናቋል።በሁለተኛው አጋማሽ የተሻለ ጫና የፈጠረው ንግድ ባንክ፣ ቅዱስ ዳዊት ያሻማውን ኳስ ሎዌ ሎኛ በግንባሩ በመግጨት በ84ኛው ደቂቃ የአቻነት ግብ አስቆጠረ። በዚህም ሁለቱ ቡድኖች ነጥብ ተጋሩ።

የቅዱስ ጊዮርጊስ የበላይነት በታየበት ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቋል ።

ቅዱስ ጊዮርጊስ 1-1 አዳማ ከተማበ ሌላኛው የዕለቱ ጨዋታ አዳማ ከተማና ቅዱስ ጊዮርጊስ እኩል አንድ ግብ በማስቆጠር አንድ አንድ ነጥብ ወስደዋል።በመጀመሪያዎቹ 15 ደቂቃዎች የተሻለ ብቃት ያሳየው አዳማ ከተማ፣ በ10ኛው ደቂቃ ከአቡበከር ሳኔ ያሻማትን ኳስ ቢንያም አይተን ወደ ግብነት በመቀየር ቡድኑን መሪ ችሏል። ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ ጨዋታው ለመመለስ ቢጥርም አጋማሹ በአዳማ ከተማ መሪነት ተጠናቋል።በሁለተኛው አጋማሽ ቅዱስ ጊዮርጊስ የበለጠ ተነቃቅቶ በማጥቃት በ63ኛው ደቂቃ ከማዕዘን ምት የተሻማውን ኳስ አብዱልሃሚድ ሙባረክ በግንባሩ በመግጨት የአቻነት ግብ አስቆጠረ። ከዚያ በኋላ ተጨማሪ ግብ ሳይቆጠር ጨዋታው በአቻ ውጤት ተጠናቋል።በዚህም የሦስተኛው ሳምንት የመጨረሻ ቀን ጨዋታዎች ሁለቱም በአቻ ውጤት ሲጠናቀቁ፣ አራቱ ቡድኖች እያንዳንዳቸው አንድ ነጥብ አግኝተዋል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...