በአቤኔዘር አበበ
ጋሞ ጨንቻ ተከታታይ የሜዳ ላይ ጨዋታ ሳያሸንፍ ቀርቷል!

በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሦስተኛ ሳምንት የመጨረሻ ቀን ጨዋታ መቻል ጋሞ ጨንቻን 1ለ0 አሸንፏል።
በጨዋታው የተሻለ ብልጫ ወስዶ የተንቀሳቀሰው መቻል፣ በ44ኛው ደቂቃ ቲቶ ኦኬሎ ባስቆጠረው ድንቅ የመቀስ ምት ግብ መሪነቱን ያዘ። በአንጻሩ ጋሞ ጨንቻ በመጀመሪያው አጋማሽ የተለየ የማጥቃት ጫና መፍጠር ተቸግሮ አጋማሹ በመቻል መሪነት ተጠናቀቀ።
በሁለተኛው አጋማሽ ሁለቱም ቡድኖች የግብ ዕድሎችን ቢፈጥሩም ወደ ግብነት መቀየር አልቻሉም። መቻል በጨዋታው የነበረውን ብልጫ በመጠቀም የቲቶ ኦኬሎን ግብ ጠብቆ በመውጣት ሙሉ ሦስት ነጥብ አግኝቷል።
የሙሉ ሰዓት ውጤት
ጋሞ ጨንቻ 0-1 መቻል
⚽️ 44′ ቲቶ ኦኬሎ
አስተያየት ይስጡ