በአቤኔዘር አበበ
ወጣቱ አጥቂ አንተነህ ተፈራ ደምቆ በዋለበት ጨዋታ ባህር ዳር ከተማ ወላይታ ድቻን 3-1 በማሸነፍ ወሳኝ ድል ማሳካት ችሏል

በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሦስተኛ ሳምንት የመጨረሻ ቀን ጨዋታ ባህር ዳር ከተማ ወላይታ ድቻን 3-1 በማሸነፍ ወሳኝ ሦስት ነጥቦችን አሳክቷል።በጨዋታው የባህር ዳር ከተማ ወጣት አጥቂ አንተነህ ተፈራ በ15ኛው ደቂቃ ቡድኑን መሪ ያደረገችውን ግብ አስቆጥሮ የመጀመሪያው አጋማሽ በባህር ዳር ከተማ 1-0 መሪነት ተጠናቋል።ከዕረፍት መልስ በ54ኛው ደቂቃ አንተነህ ተፈራ ለራሱና ለቡድኑ ሁለተኛ ግብ በማስቆጠር መሪነቱን አስፍቷል። ወላይታ ድቻ በ63ኛው ደቂቃ በመልካሙ ቦጋለ ግብ ልዩነቱን ወደ አንድ ቢያጠብም፣ በጭማሪ ደቂቃ 90+4 ብሩክ ሰሙ ለባህር ዳር ከተማ ሦስተኛውን ግብ በማስቆጠር የቡድኑን ድል አረጋግጧል።በዚህም ባህር ዳር ከተማ ወላይታ ድቻን 3-1 በማሸነፍ የሦስተኛውን ሳምንት የመጨረሻ ጨዋታ በድል አጠናቋል።የሙሉ ሰዓት ውጤትወላይታ ድቻ 1-3 ባህር ዳር ከተማ
አስተያየት ይስጡ