የወላይታ ድቻው አሰልጣኝ ከባድ ቅጣት ሲጣልባቸው ባህርዳር ከተማ እና ወላይታ ድቻም ተቀጡ።

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሦስተኛ ሳምንት የመጨረሻ ቀን ጨዋታ ወላይታ ድቻ በሀላባ ስታዲየም በባህርዳር ከተማ 3ለ1 በተረታበት ጨዋታ ጨዋታው ሊጠናቀቅ በተሰጠው ጭማሪ 90+4ኛው ደቂቃ ላይ ሦስተኛውን ጎል ወላይታ ድቻዎች ባስናገዱበት ወቅት የዕለቱነወ ፌድራል ዋና ዳኛ መስፍን ዳኜን በመሳደባቸው በቀጥታ ቀይ ካርድ መውጣታቸው ይታወሳል። አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ በቀይ ካርድ እየወጡ ባሉበትም ወቅት ከአራተኛ ዳኛው ጋር በተፈጠረ ግቦግብ ለመማታት ሞክረዋል በሚል አሰልጣኙ በአንድ ጊዜ ሁለት ጥፋትን ሰርተዋል።
በሚል በድምሩ የአስር ጨዋታ እና የአስር ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣትን የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማህበር የውድድር እና ስነ ስርዓት ኮሚቴ ውሳኔን ያሳለፈ ሲሆን የወላይታ ድቻ ደጋፊዎች በድንጋይ ረዳት ዳኛን በመምታታቸው ተጨማሪ የ50 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት በክለቡ ላይ ተጥሏል። የባህርዳር ከተማ ከጨዋታ ውጪ የነበሩ ተጫዋቾች ወደ መልበሻ ክፍል ሳይፈቀድላቸው በመግባታቸው የ25 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት በጣናው ሞገድም ላይ ተጥሏል።
እንዲሁም በሌላ ቅጣት የኢትዮጵያ ቡናው ተከላካይ ድልአዲስ ገብሬ በነገሌ አርሲ ክለቡ 3ለ0 ሲረታ በቀይ ካርድ መውጣቱ የሚታወስ ሲሆን ተጫዋቹ ለፈፀመው ተግባር የሦስት ጨዋታ እና የሦስት ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት ተጥሎበታል።
አስተያየት ይስጡ