መነሻ ገጽ Uncategorized ​የቶታል አፍሪካ  ቻምፒዮንስ ሊግ እና የቶታል አፍሪካ  ኮንፌድሬሽን ዋንጫ ድልድል ዛሬ አመሻሽ ላይ ይፋ ሆኗል!!!
Uncategorized

​የቶታል አፍሪካ  ቻምፒዮንስ ሊግ እና የቶታል አፍሪካ  ኮንፌድሬሽን ዋንጫ ድልድል ዛሬ አመሻሽ ላይ ይፋ ሆኗል!!!

አጋራ
አጋራ

ቅዱስ ጊዮርጊስ እና መከላከያ የቶታል አፍሪካ  ቻምፒዮንስ ሊግና የቶታል አፍሪካ  ኮንፌድሬሽን ዋንጫ የቅድመ ማጣሪያ ፍልሚያቸውን በወጣላቸው መርሃ ግብር የሚያደርጉ ይሆናል፡፡ የፕሪምየር ሊጉ ሻምፒዮን ቅዱስ ጊዮርጊስ የሲሸልስ ሊግ ሻምፒዮኑን ኮት ደ’ኦርን ይገጥማል፡፡        

    


                                   

  የሁለቱ ክለቦች የመጀመሪያ ጨዋታ በየካቲት ወር መጀመሪያ በሲሸልስ  እና በካሜሩን የሚካሄድ ሲሆን የመልስ ጨዋታው ከሳምንት በኋላ ኢትዮጵያ ላይ የሚካሄድ ይሆናል፡፡                                   ቅዱስ ጊዮርጊስ በዚህ ዙር ኮት ዲ ኦርን አሸንፎ ካለፈ የኮንጎ ብራዛቪሉ ኤሲ ሊዮፓርድስ እና የካሜሩኑ ዩኤምኤስ ዴ ሉም አሸናፊን በ1ኛው ዙር ይገጥማል፡፡                                    በኮንፌዴሬሽን ዋንጫው የሚሳተፈው መከላከያ በቅድመ ማጣርያው የካሜሩኑ ያንግ ስፖርትስ አካዳሚን ያገኛል መከላከያ  የመጀመርያውን ጨዋታ ከየካቲት 3እስከ5 ባሉት ቀናት አዲስ አበባ ላይ ጨዋታውን ሲያደርግ ከሳምንት በኋላ የመልሱን ጨዋታ ባሜንዳ ከተማ ላይ ያደርጋል፡፡ መከላከያ ይህን ዙር ካለፈ የቱኒዚያው ሲኤስ ሴፋክሲየንን የሚገጥም ይሆናል፡፡

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
Uncategorized

ካሌብ በየነ ወሳኙን ግብ አስቆጥሮ ሸገር ሲቲን የድል ሦስት ነጥብ አስጨበጠ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው...

Uncategorized

“ግብ ጠባቂ ለኢትዮዽያ መምረጥ ከብዶናል” አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በመገኘት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና...

Uncategorized

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከስብስቡ አራት ተጫዋቾችን ከስብስቡ ቀንሷል።

በሀዋሳ ከተማ ዝግጅት እያደረገ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ትላንት ሶስት ተጫዋቾችን የቀነሰ...

Uncategorized

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በሰባት ስታዲየሞች ላይ ይደረጋል

ሊጉ የሚደረግባቸው ስታዲየሞች ታወቁ። የ2019 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መስከረም 30/2019 እንደሚጀመር ይታወሳል።...