ቅዱስ ጊዮርጊስ እና መከላከያ የቶታል አፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግና የቶታል አፍሪካ ኮንፌድሬሽን ዋንጫ የቅድመ ማጣሪያ ፍልሚያቸውን በወጣላቸው መርሃ ግብር የሚያደርጉ ይሆናል፡፡ የፕሪምየር ሊጉ ሻምፒዮን ቅዱስ ጊዮርጊስ የሲሸልስ ሊግ ሻምፒዮኑን ኮት ደ’ኦርን ይገጥማል፡፡
የሁለቱ ክለቦች የመጀመሪያ ጨዋታ በየካቲት ወር መጀመሪያ በሲሸልስ እና በካሜሩን የሚካሄድ ሲሆን የመልስ ጨዋታው ከሳምንት በኋላ ኢትዮጵያ ላይ የሚካሄድ ይሆናል፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ በዚህ ዙር ኮት ዲ ኦርን አሸንፎ ካለፈ የኮንጎ ብራዛቪሉ ኤሲ ሊዮፓርድስ እና የካሜሩኑ ዩኤምኤስ ዴ ሉም አሸናፊን በ1ኛው ዙር ይገጥማል፡፡ በኮንፌዴሬሽን ዋንጫው የሚሳተፈው መከላከያ በቅድመ ማጣርያው የካሜሩኑ ያንግ ስፖርትስ አካዳሚን ያገኛል መከላከያ የመጀመርያውን ጨዋታ ከየካቲት 3እስከ5 ባሉት ቀናት አዲስ አበባ ላይ ጨዋታውን ሲያደርግ ከሳምንት በኋላ የመልሱን ጨዋታ ባሜንዳ ከተማ ላይ ያደርጋል፡፡ መከላከያ ይህን ዙር ካለፈ የቱኒዚያው ሲኤስ ሴፋክሲየንን የሚገጥም ይሆናል፡፡

አስተያየት ይስጡ