በ 12ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ የአራተኛ ቀን ውሎ የምድብ ለ ሁለቱም ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ተጠናቀዋል።
በቅድሚያ 9:00 ላይ የተገናኙት መከላከያ ከ አዳማ ከነማ 1-1 በሆነ ውጤት ጨዋታቸውን አጠናቀዋል፡፡ አዳማ ከነማ በ 14ኛው ደቂቃ በረከት ደስታ ባስቆጠረው ጎል መምራት ቢችልም ይትሻ ግዛው 43ኛው ደቂቃ ላይ ለመከላከያ አስቆጥሮ አቻ ለመውጣት ተገደዋል፡፡
በጨዋታው ጥሩ ብቃት ያሳየው የአዳማ ከነማው አማካይ ደሳለኝ ደባሽ የጨዋታው ኮከብ ተብሎ ተሸላሚ መሆን ችሏል፡፡

11:30 ላይ የተገናኙት ቅ/ጊዮርጊስ እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ በተመሳሳይ ውጤት 1-1 ተለያይተዋል፡፡ 18ኛው ደቂቃ ላይ አልሀሰን ካሉሻ ኢትዮ ኤሌክትሪክን ቀዳሚ ማድረግ ቢችልም ተቀይሮ የገባው የፈረሰኞቹ አምበል እና አጥቂ አዳነ ግርማ 89ኛው ደቂቃ ላይ ያስቆጠራት ጎል ቡድኑን ከመሸነፍ ታድጋዋለች፡፡ በጨዋታው ጥሩ ብቃት ያሳየው ኢትዮ ኤሌክትሪኩ ዲድየር ሊብሬ የጨዋታው ኮከብ ተብሎ ተሸላሚ መሆን ችሏል፡፡

ሁለቱን ውጤቶች ተከትሎ ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ 4 ነጥብ ምድቡን መምራት ሲችል ሁለት ጊዜ አቻ የተለያዩት ቅ/ጊዮርጊስ እና መከላከያ 2 ነጥብ በመያዝ 2ኛ እና 3ኛ ደረጃ ሲይዙ አዳማ ከነማ 1 ነጥብ ብቻ በመያዝ የምድቡ ግርጌ ላይ ይገኛል፡፡
አስተያየት ይስጡ