“የሀገራችን ተጨዋቾች ያደጉ ትልቅ ደረጃምየደረሱ አይደሉም”- “ዘረኝነቱ ካልቀረ የተጨዋቾች እንጀራይዘጋል እንጂ እግር ኳሱ ቢታገድ ደስይለኛል”- “በሄድኩበት ቦታ ተጨዋቾቹ ሳይቀር ወደዘረኝነት መሄዳቸው ያሳስበኛል”የፋሲሉ አይናለም ኃይለ (ገብርዬ)

በዮሴፍ ከፈለኝ
ሀትሪክ– የማትረሣው ድል የትኛው ነው?አይናለም፡-በ2005 ከደደቢት ጋርየፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ ያነሣሁበትና በ2005ለደቡብ አፍሪካ የአፍሪካ ዋንጫ ያለፍንበትንአመት የማይረሣ ድሌ ነው፡፡ሀትሪክ፡- የአሰልጣኝ ሰውነት ቢሻውስብስብን እንዴት ትገልፀዋለህ?አይናለም፡- ያ ቡድን የሚገርም ነው፡፡ በወቅቱ የነበርነው ተጨዋቾች ጥሩ ነበርንማለፋችን ግን በችሎታ አይመስለኝም (ሳቅ)እግዚአብሔር ረድቶን በሞራል ተሳክቶልንህዝቡ በጣም አነሳስቶን ለማለፍ በቅተናል፡፡በግሌ ሶስት አመታት ያህል ለብሔራዊ ቡድንተጫውቻለው፡፡ሀትሪክ፡- በሶስት አመት ውስጥ በሶስትአሰልጣኞች ሰልጥነሀል፤… እስቲ ዘርዝርአድርገው?አይናለም፡- ለመጀመሪያ ጊዜ የጠራኝኦፌይ ኦኔራ ነው ያለቦታዬ አሠልፎኝጉድ ሰርቶኝ ነበር፡፡ ቀጥሎ ቶም ሴንትፊትመጥቶ አሰለጠነን በመጨረሻም አሰልጣኝሰውነት ቢሻው ከምክትል አሰልጣኝነት ወደዋና አሰልጣኝነት አድገው ስኬታማ ጊዜአሳልፈናል፡፡ሀትሪክ፡- የሰውነት ልጆች ከሚባሉመሃልኮ አንዱ አንተ ነህ? ታስታውሳለህ… ?አይናለም፡- ጥሩ ግንኙነት ነበርንማን ይግባ ማን ይውጣ ብዬ ግን ተነጋግሬአላውቅም አሰልጣኙ ከኔ ጋር ሲጠላ ነውየማውቀው ከሜዳ ሲያባርረኝ ውጣ ሲለኝ ነውትዝ የሚለኝ፤… በእርግጥ ፀቡ አባታዊ ነበር፡፡ አምበል ሆኜ ግን ስለ አሰላለፍ አውርቼአላውቅም፡፡
ሀትሪክ፡- ቡድኑ ለአፍሪካ ዋንጫ ያለፈውበብቃት ነው ማለት ይቻላል?አይናለም፡- ይሄን ደጋግሜ አውርቻለሁከፈጣሪ ጋር እድለኛም ነበርን፡፡ 5ለ3 በሱዳንተሸንፈን አዲስ አበባ ላይ 2ለ0 ረትተን ነውያለፍነው እድለኛ ነበርን ማለት ይቻላል፡፡በዚያ ላይ ታላቅ ሞራልም ነበረን፤ በዚያ ላይአዲስ ሕንፃ ተሳስቶ ጎል ገብቶብን ጉድ ሆነንነበርን፡፡ ዳኛው ቀድሞ ዞር ባይል ተሸንፈንህዝቡ በሙሉ ሀዘን በሀዘን በሆነ ነበር፡፡እንዳንወድቅ እድል አግዞናል ማለት ይቻላልትንሽም ብትሆን መልፋታችን መረሣትየለበትም፡፡ሀትሪክ– ከዚያ በኋላኮ ብሔራዊ ቡድኑጠፋ?አይናለም፡-ድብብቅ አልወድም የኛ ሀገርተጨዋች ያደግን ትልቅ ደረጃ የደረሰንአይደለንም፤ ስሙ ነው ፕሪሚየር ሊግየተባለው እንጂ ገና ነን፡፡ ተጨዋቹም ትንሽስትናገረው የሚከፋው ሆኗል ይሄ ደግሞአለመብሰል ነው፡፡ ትንሽ ስታሞግሰው ደግሞተበጥሶ እላይ ነው የሚደርሰው፤ አሁንያለው ብሔራዊ ቡድን እናንተም ጋዜጠኞችብታሞግሱት እላይ ይደርስ ነበር፡፡ ነገርግን ጠዋት ተነስተህ እስከ ማታ ጋዜጠኛሲተች ነው የምሰማው፤ አትተቹ ሳይሆንማበረታታቱን አስቀድሙ ለማለት ነው፡፡ በኛጊዜም ትችቱ ነበር፡፡ እዚያ ሀገር የተጨዋቾቹትልቁ ችግር የስፖርት ዜና ያዳምጣል፡፡ሀትሪክ– የስፖርት ዜና ማዳመጥ ችግርነው እያልክ ነው?አይናለም፡- አዎ ጠዋት ሬዲዮ ሰምቶትችት ካዳመጠ ልምምድ ላይ ሲሄድ ተበሳጭቶአብዶ ነው የሚሄደው ምክንያቱ ደግሞአላደግንም ብዬሃለሁ፡፡ በትችቱ ማደግ ሲችልይበሳጫል፡፡ በቃ ንዴቱን ደግሞ ጋዜጠኛውላይ ሳይሆን ተጨዋቾቹ ላይ ያበርዳል፡፡ ሬዲዮባይደመጥ ይሻላል የምለውም ለዚህ ነው፡፡ትችቱ አይቀርም ግን በሙገሳ ቢታጀብ ጥሩይመስለኛል አንድ ጊዜ ሳምንቱን ሙሉ ትችትብቻ የሰማሁበት ጊዜ ነበር፡፡ ያ መታረምአለበት፡፡ የኛ የስፖርተኞችም ጭንቅላትማደግ ይጠበቅበታል፡፡ የስፖርት ዜናንኮአሰልጣኝ ሰውነትም ይሰማል፡፡ ትሬኒንግ ላይይሰማል… ትችት ሰምቶ ይናደዳል አንዳንዴኮበንዴቱ አሰለጣጠኑን በስሜት ሊቀይርይችላል (ሳቅ)ሀትሪክ፡- ጥሩ ውጤት ሲመጣማበረታታት ውጤት ሲጠፋ ትችት ተገቢአይደለም?አይናለም፡- ትችቱ ይቅር እያልኩአይደለም፡፡ በኛ ጊዜኮ የምንበላው ጭምርይዘገብ ነበር ያ ተገቢ አይደለም እዚህ ቤትጨፈረ ጠጣ ከእከሌ ጋር ሄደ የሚለውንየውጪ ሀገር ስታይል ከኛ አገር ባህል ጋርአይሄድም፤ መታረም አለበት ትችቱ ሊቀርግን አይገባም መሆን ያለበት የሚያሳድግትችት ከፍ የሚያደርግ ማበረታታት ቢኖርየተሻለ ይመስለኛል፡፡ሀትሪክ፡- የተጨዋቾች ደመወዝናየተጨዋቾቹ አቅም ይመጣጠናል?አይናለም፡- በፍፁም አይገናኝም የኛ ሊግፕሪሚየር ሊግ ተባለ እንጂ ደረጃው ልክአይደለም በደመወዝ ደረጃ አንድ ተጨዋችሚሊየን ብር ቢከፈለው ምን አለበት…?ደስ ነው የሚለኝ ምክንያቱም ኑሮውንያስተካክልበታል የመንግሥት ብር እንዴትይባክናል? ከተባለ ክፍያው በርግጥም አሁንምአይመጣጠንም፡፡ በኔ በኩል ግን በየወሩሚሊዮን ብር ቢሰጡን ምናለበት? (ሳቅ በሳቅ)ሀትሪክ፡- 40/60 የማውቀውበኮንዶሚኒየም ነበር አሁን ግን በኳሱመጥቷል፡፡ ስትፈርም ብር አልተጠየክም?አይናለም፡- በፍፁም የጠየቀኝ ሰው የለምገጥሞኝም አያውቅም እኔማ አጋልጣቸውነበር ነገር ግን የጠየቀኝ የለም ነገሩ ግንበደንብ አለ አብዛኞቹ አሰልጣኞች ይወስዳሉ፡፡ሀትሪክ፡- ፊት ለፊት ተናጋሪ ነህ…አልተጎዳህበትም?አይናለም፡- አይናለም ቲቢተኛ ነውሊሉ ይችላሉ፡፡ ሌባውን ሌባ ነው አለማለትትልቅ ስህተት ነው፡፡ ሌባ ከሆነ በቃ ሌባ ነውየምለው ይሄ እውነትኮ ነው ብዙ አሰልጣኞችእንዲህ አትበል ይሉኛል፡፡ ውትድርና ቤትበፊት ለፊት እንጂ በድብብቆሽ አላደኩምደጉ ምርጥ ጓደኛዬ ነው ቢያጠፋ ላልፈውነው? ያኔማ ልክ አይደለሁም ማለት ነው፡፡ለኛ ሀገር ባይሆንም እኔ ግን ቀጠዬበታለሁበድድብቅ የሚሆን ነገር አይመቸኝም ከሚስቴጋር እንኳን ፊት ለፊት ነው የማወራው ምንይሁን ምን ፊት ለፊት ነው የማፍረጠርጠው፡፡ ይሄን ባህሪዬን ታውቀዋለች፡፡ በቃ አይናለምይሄ ነው ምን ይደረጋል? (ሣቅ)
ሀትሪክ– እግር ኳሱ ዘር ተኮር ፖለቲካተጨምሮበት እያየን ነው ምን ይሆንመፍትሔው?አይናለም፡- በጣም የምጠላው ጉዳይ ይሄነው፡፡ በሄድኩበት ቦታ ተጨዋቹ በሙሉ ወደዘረኝነት እየዞረ ነው፡፡ ኳስን ከዘር ጋር ምንምአያገናኘውም፡፡ እንዴት ነው የማናመዛዝነው?የዘር ጉዳይስ ምን ሊጠቅመን ይችላል?አይናለም ትግሬ ነው ምን ያመጣል ታዲያ?ጉራጌ በል አማራ፣ ኦሮሞ በል… ሌላ ዘርምንድነው ብልጫው? ሰው መሆናችን ብቻ በቂነው ዘር የምንጣላበት ርዕስ መሆን የለበትም፡፡ በተፈጥሮ “ሰውነት” ይበልጣል ሰው ክቡርነው፡፡ ፈጣሪ በአምሳያ ፈጥሮን በምክንያትሌላ ዘር ነው ብሎ ፈልጎ ሰው መግደል…ምን ትርፍ ሊያመጣ? ኳስ ላይ በዘርህትሳደባለህ… በጎን ደግሞ ድል ይጠብቃል?እኔ በጣም ተከፍቻለሁ፡፡ ጎንደር ላይ ለፋሲልስጫወት ደጋፊው ደስ ይላል ምርጥ ድጋፍአለው፡፡ ሌላ ቦታ ጋር ሲኬድ ግን ይቀየራልለምን? ለምን ጎንደር ላይ ያለው ድጋፍ ሌላክልል አይቀጥልም? ፋሲል ከመቐለ ሲጫወቱያለው ንግግር ጥቅሙ ምንድነው? ፍሬይገኝበታል? መሰዳደባቸው የሚያመጣውስጥቅም አለ? ለስፖርቱስ እድገት ያመጣል?ይሄ እድገት ሳይሆን ትልቅ ውድቀት ነው፡፡የዚህ ትልቅ ስህተት ዋነኛ ተጠያቂ ብሔራዊፌዴሬሽኑ ነው፡፡ ተጨዋቹ በቀይ ወጥቶመልሶ በቀጣዩ ጨዋታ ላይ ይገባል ይሄምይታለፋል ይሄ ነው መስተካከል ያለበት፡፡ሌላ ምሣሌ ልስጥህ… ክለቦቻችን የፈለጉትንአርማና ፎቶ መጠቀም መብታቸው ይሆንይሆናል፡፡ ነገር ግን መጣያቸው ሊሆን ይገባልብዬ አላምንም፡፡ ፌዴሬሽኑ ዘር ተኮር ጉዳዮችላይ ጠንካራ ርምጃ መቼ ወሰደ? ይህንን ደካማአካሄዶችን ለማረምስ የሰራው ነገር አለ? የዘርጉዳይ ካልቀረ የሰው እንጀራ ይዘጋል እንጂኳሱ ቢታገድ ደስ ይለኛል፡፡ ሰው ሞቶ ከምናይቢታገድ ይበጃል፡፡ የሚገርመኝ ፀቡ በዚህ ኳስያውም በሞተ ኳስ ሲጣላ ሳይ እበሳጫለሁ፡፡ሀትሪክ፡- የታይላንድ ባንኮክ ቆይታህ ምንይመስላል?አይናለም፡- ድሬደዋ ከፋሲል ሲጫወትነው ጉዳት የደረሰብኝ በወቅቱ አሰልጣኞችንጌጡ ይባል ነበር፡፡ ተጎድቼ በአምፑላንስተወሰድኩ፡፡ ተጎድቼ ከወጣሁ በኋላ በመልስምት ይጀመራል ሲባል ዳኛው ሪጎሬ ሰጠ፡፡መነሳት አቃተኝ እንጂ ከኳስ የምታገደው ያኔነበር፡፡ ተበሳጨሁ እግሬ ዞሮ አስወጡት አለናወጣው እንደወጣው በመልስ ምት ይጀመራልሲባል ፔናሊ ሰጠ ከወጣሁ ከ2 ደቂቃ በኋላ ነውየሰጠው፡፡ መጎዳቴ ነው እንጂ የማደርገውንአላውቅም ነበር፡፡ ወዲያውኑ ፊሽካ ሳይነፋ ከ2ደቂቃ በኋላ ሪጎሬ ነው ሲል ተናደድኩ ይሄንመቼም አልረሳውም፡፡ ነገር ግን የተፅናናሁትኳሱ ጎል ሳይሆን መቅረቱ ነው፡፡ በአምፑላንስተወስጄ መራመድኮ አቅቶኛል ኧረ ነገ ነውልምምዴን የምጀምረው ስለው አሰልጣኙ3 ቀንማ ማረፍ አለብህ አለኝ፡፡ እኔ ግንአልተቀበልኩትም፡፡ ለካ የምር ተጎድቻለውተንጠልጥዬ ነው የሄድኩት ከኤርፖርትምወደ ቤቴ የገባሁት በክራንች ነው፡፡ ለካተጎድቻለው አዲስ አበባ እንደመጣሁ ዶ/ርኤሊያስ የሚባል አራት ኪሎ አካባቢ ያለዶክተር ነው….እርሱ ጋር ሄድኩ… አየኝናኦፕሬሽን መደረግ አለብህ አለኝ ሌላ ቦታምስሞክር ኦፕሬሽን ታደርጋለህ አሉኝ የፋሲልሰዎችም ተጠራጠሩና ወደ ጎንደር እንድመለስአደረጉኝ፡፡ ዶ/ር አስቀምጠው ሲያየኝ እግርህኮዞሯል ሲለኝ ይህን ለነርሱ ንገር አልኩት፡፡ፋሲል ደደቢትን ያሸነፈበትን ጨዋታ አየሁናማታውኑ ተመለስኩ፡፡
ዶ/ሩ አዲስ አበባ በደንብካየኝ በኋላ ታይላንድ አሊያም ህንድ ሄደህመታየት አለብህ አለኝ፤ ከትንሽ ቀናት በኋላታይላንድ ሄድኩ እዚያም አዩኝና ኦፕሬሽንአያስፈልገውም ረዘም ያለ ዕረፍት አድርግይሻልሃል አሉኝ፡፡ ሌላ ቦታ ስታየው ያየችኝዶ/ር ዕረፍት ብቻ ነው የሚያስፈልግህ አለችኝወደ አዲስ አበባ መጣሁና እረፍት ወሰድኩ፡፡ ቆይቼ ሳየው ጤነኛ እየሆንኩ መጣውደስ አለኝና ከጎተራ ኮንዶሚኒየም ተነስቼኤርፖርት ድረስ በሶምሶማ በመሮጥ መዳኔንለማረጋገጥ ሞከርኩ… ስመለስ መራመድአቃተኝ በጣም ተበሳጭቻለሁ ይህን ጉዴንሳላይ ለፋሲል ከነማ አመራሮች እመጣለሁብዬኮ ሪፖርት አድርጌያለሁ፡፡ ወደ ክለቤ ዝምብዬ ከመሄድ ሁሉን ነገር ልይ ብዬ ቀረሁ፡፡ ውስጤ የማቆም ይመስለኛል እግዚአብሔርብሎ ካደነኝ ግን ደስ ይለኛል፡፡ሀትሪክ– የፋሲሎችና የአይናለም ፍቅርየሚበርድ አልሆነም… ስለዚህ ጉዳይ ምንትላለህ?አይናለም፡-እኔም ለእነርሱ ልዩ ፍቅርአለኝ፡፡ ከፋሲል በፊት ለዳሽን ተጫውቻለውሁሉም ያውቀኛል ከማንም ጋር ነውየምግባባው ማህበራዊ ግንኙነቴ ሁሉ ጠንካራከመሆኑ የተነሣ የምጠራበት ሁሉ ሰርግምይሁን ለቅሶ እሄድ ስለነበር የማያውቀኝየለም፡፡ ለዳሽን እየተጫወትኩ ፋሲል ሊያድግ4 ጨዋታ ሲቀረው አሰልጣኙ ዘማርያምመጥቶ ተጫወትልን አለኝ፡፡ እሺ በማለቴዳሽን እያለው ለፋሲል ገባ ተብሎ ተወርቶመነጋገሪያ ሆኜ ነበር፤ አራቱን ጨዋታበነፃ ነው የምጫወተው ስላቸው ተገረሙእንክፈልህ እያሉኝ እንቢ ማለቴ በመላከተማው ተሰማ… ተገረሙ ለኔ ያላቸውፍቅር የጨመረ የሆነውም ከዚህ ቀን ጀምሮነው፤ ዳሽን እያለው ሁሉ ቅፅል ስሜ ገብርዬነበር (የአፄ ቴዎድሮስ የቀኝ እጅ) በሁለታችንመሃል ጥሩ ፍቅር ነግሷል፡፡ ጉዳቱ ከእነርሱጋር እንዳያለያየኝ ግን ሰግቻለው አሰልጣኝውበቱም እጠብቅሃለው ብሎኛል ግን በጣምመታመሜን ለማን ላስረዳ ጉዳትህንኮአንዳንዴ እናትህ ላታውቅልህ ትችላለች፡፡
እነርሱ ለሌላ ክለብ ይፈርማል የሚል ስጋትገብቷቸዋል፡፡ በፍፁም አይደረግም አስቤውምአላውቅም ይሄን ወዳጅ ቡድን ጥዬ ከሄድኩንቀት ይሆንብኛል መቼም ቢሆን መልቀቂያአልጠይቅም ከዳንኩ የምጫወተው ለፋሲልብቻ ነው አለበለዚያ ግን ስንብት ይሆናልበግሌ የማረጋግጠው ፋሲሎችን ገፍቼ የትምአልሄድም የሰጡኝ ክብር የት ይገኛል?አስቤውም አላውቅም ሁሌም እወዳቸዋለው፡፡ሀትሪክ– ላንተ ኮከብ አሰልጣኝ ማነው?አይናለም፡- (ሳቅ) አሰልጣኝ ንጉሴደስታ ይመቸኛል፤ ሰው አቀራረቡ ሲያሰራምየምወደው የእርሱን ሥልጠና ነው አብረንምዋንጫ ወስደናል በዚህ አጋጣሚ በማረፉአዝኛለሁ ለቤተሰቡ፣ ለወዳጆቹ በሙሉመፅናናትን እመኛለሁ፡፡ሀትሪክ– ከአሰልጣኞች ጋር በመላተምትታወቃለህ… ፌዴሬሽኑ ቀጥቶህ ያውቃል?ፀቡ በአንተ አሸናፊነት ተጠናቅቆ ያውቃል?አይናለም፡- በቅጣት ከፌዴሬሽኑ ጋርተገናኝቼም አላውቅም አልተቀጣሁም፡፡ከአሰልጣኝ ሰውነት ጋር ተጋጭቻለሁ፡፡ ባንተአሸናፊነት ተጠናቀቀ ወይ ላልከው ያለነውኢትዮጵያ ውስጥ መሆኑ መታወቅ አለበት፡፡እዚህ ስትኖር ተጨዋች ፊት ለፊት እንዲናገርአይፈቀድለትም፡፡ ተጨዋቹ ተጨቁኖ ነውየሚኖረው፡፡ አንድ አሰልጣኝ የማይሆንነገር ተናግሮ ልክ አይደለም፤.. እንዲህ ነውካልክ ወቀሳው የሚጀምረው ከተጨዋቾቹነው፡፡ ለምን እንዲህ ትለዋለህ ይሉሃል…ግንኮ አጥፍቷል፡፡ ኃላፊዎችም ፊታቸውንይጥላሉ፡፡ አሰልጣኙ 2+2=5 ነው ካለ የግድማመን አለብህ፡፡ ይሄ አስቸጋሪ የእግር ኳስህይወታችን ነው፡፡ ፊት ለፊት መነጋገርቢቻል ችግር የለውም፡፡ ካጠፋ የማስተካክለውእውቀቴ የላቀ ሆኖ አይደለም በቃ ያቺ ቀንላይ ጥፋት ስለሆነ ለማረም መናገር ክፋትየለውም በኛ ሀገር ያለው ህይወት ይሄ ነውአንዴ ከአሰልጣኝ ሰውነት ጋር የተጋጨሁበትጉዳይ ይገርመኛል ሹት አመታት እያሰራንአጠፋው… አንተ ና ብሎ ተሳደበ፡፡ በጣምተናገረኝ ቅር ተሰኘሁና ከምትሰድበኝ ለምንእንዲህ ነው ብለህ አትናገረኝም ስለውአትመልሰልኝ…. ቆይ ላስረዳህ ስለው ውጣአለኝ፡፡ ውጣ ካለኝ መነጋገር አልፈለገምማለት ነው፡፡ ተነጋግረን መፍታት አይፈቀድምመፈትሔው ዝምታ ብቻ ነው መነጋገርሽንፈት ነው የሚመስላቸው ውጣልኝ ስትባልመብታቸው ነው፡፡ ትወጣለህ…. አልወጣምአትል? ስትወጣ ደግሞ ተሸናፊ ሆነህ ነውውይይት የለም ውጣ ስትባል ትወጣለህ…በቃ ታሪካችን ይሄ ነው!ሀትሪክ– ምርጡ ተጨዋችስ ላንተማነው?አይናለም፡- ያለ ጥርጥር ደጉ ደበበ ነዋ!ድሮም ተከላከይ ባይሆን ይሻላል እል ነበር፡፡አንዴ ከጋዜጠኞች ጋር ቃለ ምልልስ እያደረኩከውጪ ማንን ታደንቃለህ ሲሉኝ የአርሰናሉንአሌክሳንደር ህሌብ ስላቸው በሳቅ ሞቱ፡፡ ምነውስላቸው አስቀይሰው አለፉ ከቃለ ምልልሱበኋላ ግን ለምን ሳቃችሁ ብዬ ጠየኳቸው፤ተከላካይ ስለሆንክ ራሞስ.. ምናምን ትላለህብለህ ጠብቀን ነበር ሲሉኝ በተራዬ ሳቅኩ፡፡ሰርቪስ ላይ የኛ ተጨዋቾች ሰምተው ስለነበርገና ሲያዩኝ በጣም ሳቁ፤ የጠበቁት ተከላካይእንድጠራ ነበር፡፡ አሁንም ሌላውን ተጨዋችተወው ደጉን ብቻ አደንቃለሁ (ሳቅ)
ሀትሪክ፡- መከላከያና አይናለም እንዴትተገናኙ?አይናለም፡- (ሳቅ) ወታደር ያውም ም/ልአስር አለቃ ነበርኩ፡፡ ባህርዳር ምዕራብ ዕዝእያለው ኳስ እጫወት ነበር የየክልሉ ምርጦችአዲስ አበባ መጥተው ይጫወቱ ነበርናበወቅቱ ወክዬ የመጣሁት የአማራ ምርጥንነበር ያ ዘመን አሁን መቀየሩ ያማል፡፡ በፊትኮየአማራ ክልልን ወክዬ ተጫውቻለው፡፡ አሁንግን ታሪክ ተቀይሯል በጣም አዝናለው፡፡ አዲስአበባ መጥቼ ስጫወት አዲስ አበባ መከላከያእግር ኳስ ክለብ ውስጥ ሊያስቀሩኝ ፈለጉ፡፡ የኔ ፍላጎት ግን ለሀረር ቢራ ለመጫወትነበርና ከነሱ ጋር ተስማማሁ፡፡ ወታደርሆኖ ለካ አይቻልም በወቅቱ እንደማይቻልምአላውቅም ነበር፡፡ ባህርዳር ስጫወትፕሪሚየር ሊግ ምንድነው? አይገባኝም፡፡መከላከያ ና ስባል እንቢ ብዬ ባህርዳር ሄድኩ፡፡ እዚያ ስሄድ ደመወዝ የለም ፔሮል ላይ እኔየለውም ደመወዙ 201 ብር ነው ምነው ቀረስል ፔሮልህ አዲስ አበባ ነው ያው ብለውለ201 ብር ደመወዝ ከባህርዳር አዲስ አበባመጣሁ፡፡ እዚህ ደመወዝ ከወሰድኩ በቃ ቀረሁማለት ነው የግዴን ስለመጣሁ ቅር ብሎኛል፡፡ ቡድኑ ለዕረፍት በመበተኑ የሚቀበለኝ ሰውአጥቼ ለሶስት ቀን ያህል ተርቤ ነበር፤ ሰውአጣሁና ተከፋሁ፤ አሰልጣኝ አስራት ኃይሌከንጉሴ ደስታ ጋር መጡ፡፡ አሰልጣኝ አስራትንአይቼውም አላውቅም ሳየውም ማን እንደሆነአላወቅኩም፡፡ ተርቤ ተቸግሬ ቁጭ ብዬእንዳለ አስራት መጣና ሎቲ አድርጌ ስላየኝበቁጣ አውልቀው ሲለኝ አላውልቅም አንተማነህ አልኩት… ልንጣላ ነበር እርቦኝ ተቸግሬስለነበር ሲሰማ ግን ተበሳጭቶ ቢሮ በመሄድእንዴት ይሄ ነገር ሆነ…ወታደሩን እንዴትስየሚበላውን ያጣል ብሎ ተናዶና ተሳድቦ1000 ብር አምጥቶ ሰጠኝ፡፡ 1000 ብር ሳይየመጀመሪያ ጊዜዬ ስለነበር ተደሰትኩ፡፡ የ5ወር ደመወዝ በለው ተዝናናሁበት (ሳቅ) ብሩአሁን እንጂ ያኔ እኮ ውድ ነበር ጥሩ አቅምነበረው፡፡ ከዚያ የጀመረ አይናለም አሁንያለበት ድረስ ተጉዟል (ሳቅ)ሀትሪክ፡- ከጨዋታ ውጪ ወደ ቢዝነስየምታተኩር ይመስላል…. ካፌ ከፍተሃል…ቀጣይስ ምን አሰብክ?
አይናለም፡- ካፌዋ በባለቤቴ ነውየሚመራው ምናልባት ጉዳቱ አላጫውትብሎኝ ካቆምኩ የመኪና ቢዝነስ ውስጥ የምገባይመስለኛል፡፡ሀትሪክ፡- 50 አለቃ ወይስ 100 አለቃ?አይናለም፡- (ሳቅ በሳቅ) እንደ አሰልጣኝሰውነት ሆንክብኝሳ? ሃምሳ አለቃ ነኝ አባቱ!ሰውነት መቶአለቃ ሲለኝ ተው እንጂ የሰውማዕረግ ዝም ብሎ አይጠራም አልኩት (ሳቅ)በህጉ አይቻልምኮሀትሪክ– በማዕረግህ የምታገኘው ጥቅምአለ?አይናለም፡- ኧረ አስታውሼውምአላውቅም ከውትድርና ወጣው… በቃ! 7አመት ግዴታዬን ተወጥቼ በቃኝ አልኩ…ቀጥል ሲሉኝ እንቢ አልኩና ደብዳቤ አስገባሁመልቀቂያዬን ወስጄ ወጣሁ በቃ!ሀትሪክ፡- በትክክለኛ ውጊያ ላይ ተሳትፈህታውቃለህ?አይናለም፡- አዎ! ያውም ወደ ውትድርናሳልገባ ነው የተዋጋሁት ትግራይ እያለሁአዲግራት ላይ ለሰራዊቱ ውሃ አቀብልተብዬ ተያዝኩ፡፡ ሰራዊቱ እየተዋጋ ምግብእናቀርብ ነበር፡፡ ዛላንበሳ መረብ ስቲትስልጠና ወስጃለሁ፡፡ 10+1 ተማሪ ተብሎ ወደማሰልጠኛ ገባን፡፡ሀትሪክ– በውትድርና አለም ገጠመኝአለህ?አይናለም፡- አንዴ መረብ ሰቲት ላይጎርፍ ወስዶኝ ነበር… ኮሾሮ ላይ ተኝቼነበር ኤርትራ ውስጥ የዘነበ ዝናብ ወንዙየኢትዮጵያን ድንበር ነክቶ ያልፋል በተኛንበትወስዶን በትግል ተረፍን… ይሄማ መቼምአይረሳም፡፡
ሀትሪክ፡- የኛ ሀገር ኳስ የማደግ ተስፋአለው?አይናለም፡- አሁን ባለሁ እውነት እድገቱአይታየኝም፡፡ የተጨዋቾቹና የደጋፊው ነገርወደ ዘር እያዘነበለ ለውጥ አይታሰብም ከዚህመውጣት አለብን ያለበለዚያ ወደታች እንጂየምንወርደው ትንሽኳ ፈቅ አንልም፡፡ የዘርጉዳይ ላይ ሰው ፀጥ ብሏል፡፡ ግን ፀጥ ብሎሳይሆን አብጦ ነው ያለው… ከፈነዳ ደግሞአንገናኝም የወደፊት አደጋው ያሰጋኛል፡፡ዝምታው ውስጥ ለውስጥ ችግሩን ሳናየውእየባሰ እንዲመጣ አድርጓል፡፡ ፖለቲካ ቢሆንአያገባኝም ይባል ይሆናል ኳሱ ውስጥፖለቲካ አያገባውም ነገር ግን አሁን ገብቶእየበጠበጠ ነው፡፡ሀትሪክ፡- የክልል ክለቦች ሲቀጡ የክልልመንግሥታት ለፌዴሬሽኑ መደወላችውስተቀባይነት ይኖረዋል?አይናለም፡- የለውም፡፡ በፍፁም ልክአይደለም ፌዴሬሽኑ ነው ይህን ማስቆምያለበት፡፡ አመራሮቹ ጠንካራ ሆነው መታገልአለባቸው፡፡ ፋሲል ይሁን ጅማ መቀሌ ይሁንሌሎች ክለቦች ካጠፉ እርምጃ መውሰድ ምኑያስፈራል? በህጉ መቅጣት የግድ ይገባል ፋሲልሲቀጣ ክለቡ እንጂ አማራ ክልልን እንደቀጣመታሰብ የለበትም፡፡ ትግራይም ሌሎች አዲስአበባም የሚገኙ ክለቦችም እንዲሁ መታየትአለባቸው፡፡ የክልል ኃላፊዎች ፌዴሬሽንከመደወል ይልቅ ክለባቸውን ማበረታታት እናሕግን እንዲያከብር ማድረግ አለባቸው ያ ነውኃላፊነታቸው!ሀትሪክ፡- በቀጣይ ምን አሰብክ…ውስጥህስ ምን እያለህ ነው?አይናለም፡- አርሴማ የምትባል ገዳምአለች አንድ ጋዜጠኛ አግኝቶኝ ደነገጠ… ለምንእንደደነገጠ አልገባኝም በሠላም ነው ምነውሲለኝ አይ! እግሬን አሞኝ ነው አልኩትናተለያየን 7 ቀን እያደርኩ ፀበል አስመትቻለው፡፡ እግዚአብሔር የማያደርገው ነገር ስለሌለካዳነኝ ኳስ የማቆም ህልም የለኝምና ለፋሲልየምጫወት ይሆናል ገና ነኝኮ ገና ስምንትአመት ብቻ ነው የተጫወትኩት፡፡ ከተሻለኝለፋሲል 6 ወር በነፃ ነው የማገልገለው ብዬወስኛለው… ዋናው መዳኔ ነው… በህሊናዬግን አቆም ይሆን ብዬ ሰግቻለሁ፡፡ሀትሪክ፡- ለብሔራዊ ቡድን ለምን በቃኝአልክ?አይናለም፡- ሰለቸኛ! ድንገት ነው በቃኝያልኩት… የናንተ የጋዜጠኞች ንግግርናትችት ሰለቸኝ በቃ አቆምኩ ገና ነኝ ብዙመጥቀም እችል ነበር ባይ ነኝ፡፡ሀትሪክ፡- የመጨረሻ ቃል? የምታመሰግነውም ካለ?አይናለም፡- ፈጣሪዬን በጣምአመሰግናለው በሄድኩበት ክለቦች ውስጥ ያሉደጋፊዎች፣ መላው የሀገሬ ህዝብ፣ ቤተሰቦቼህዝቡ ለዋሊያዎቹ ድል ለሰጠው እውቅና፣ለባለቤቴና ልጄ ለጓደኞቼ… በኔ ነገር ላይድጋፋቸውን ላደረጉ ሀትሪክን ሳይቀር በጣምአመሰግናለሁ እግዚአብሔር ይስጥልኝ፡፡
አስተያየት ይስጡ