ዛሬ አንጋፋውን የቅዱስ ጊዮርጊስ የስፓርት ማህበር ከገጠመው የመፍረስ አደጋ ለመታደግ የተለያዩ አካላትን በማስተባበር የ100 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርገዋል።

አንጋፋው የቅዱስ ጊዮርጊስ የእግር ኳስ ማህበር የተጫዋቹ እና የማህበሩ እና የደጋፊው ብቻ ሳይሆን የመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጭምር ነው በሚል በዛሬው ዕለት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ክለቡን ለማዳን ከተቋቋመው ኮሚቴ እና ከሌሎች ድርጅቶች ጋር በጋራ ከተደረገ ውይይት በኋላ ለክለቡ የ100 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ስጦታ ለዚህ አመት ብቻ ተደርጓል።

ላለፉት ስድስት ወራት ገንዘብ ላልፈላቸው ተጫዋቾች እና ለሌሎች የዚህ አመት ወጪዎች እንዲሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ10 ሚሊዮን ፣ ቢጂአይ ኢትዮጵያ 40 ሚሊዮን እና አንጋፋው ተቋም ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የ50 ሚሊዮን በድምሩ ለክለቡ በዛሬው ዕለት በአዲስ ከተማ አስተዳደር ቢሮ ተበርክቷል።

አስተያየት ይስጡ