በኢራቅ ሊግ ቆይታ የነበረው አጥቂ ነገሌ አርሲን ይቀላቀላል።
ኪቲካ ጀማን በዝውውሩ የመዝጊያ ቀን ከመቐለ 70 እንደርታ ያስፈረመው አዲስ አዳጊው የሊጉ ክለብ ነገሌ አርሲ በአጋማሹ ሁለተኛ ፈራሚው ናይጄሪያዊውን የ28 አመት ዕድሜ አለው የተባለውን አጥቂውን ኒድፍሬክ ኢዶ ኢፍዮንግን ለማስፈረም በመስማማቱ ነገ ወደ ኢትዮጵያ ይገባል።

በሀገሩ ክለብ አቢያ ኮሜት እግር ኳስን ጀምሮ በመቀጠል አቢያ ዋሪሪየርስ እና አኩዋ ስታርስ በተባሉ ክለቦች ግልጋሎት ሰጥቶ ወደ ሊቢያ አምርቶ ለአል-ሀሊ በሞሮኮው ኦሎምፒክ ሳፊ በኢራቁ አልቁማል አልጃህ እና አልናፋት ከተጫወተ በኋላ በድጋሚ ወደ ሀገሩ ተመልሶ ለሪቨር ዩናይትድ በ2024/25 የውድድር ዘመን ደግሞ ወደ ኢራቅ በመመለስ ለኒው ሮዝ እንዲሁም በያዝነው አመት ደግሞ በዛው በኢራቅ ትልቁ ሊግ ኢራቅ ስታርስ ሊግ ላይ በአል ሄዶድ እየተጫወተ የቆየው እና ጋቶች ፓኖም ወደ ሳውዲ ከማምራቱ በፊት በአልናጃፍ ቆይታው አንድ ጎል ባስቆጠረበት እና በድምሩ ከ203 ጎል አስቆጣሪ ተጫዋቾች ባሉበት ሊግ በጎል አስቆጣሪ ዝርዝር ውስጥ የሌለው ይህ አጥቂ አዲሱ የነገሌ አርሲ ተጫዋች ለመሆን ተቃርቧል።
ኢራቃዊው መሐመድ አሊ በ27 ጎሎች በሚመራበት የኢራቅ ሊግ ነገሌን የሚቀላቀለው የናይጄሪያዊው አጥቂ ክለብ የሆነው አል ሁዶድ ከ20 ክለቦች 19ኛ ላይ ተቀምጦ ላለመውረድ እየተጫወተ ይገኛል።
አስተያየት ይስጡ