ወደ ልጅነት ክለቡ ኖንት ወይም ኮሞ የመዛወር ተስፋ ያለው ተከላካይ ማነው ?
የተወለደው በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በኮንሶ ወረዳ ገዋዳ ተብላ በምትጠራ ቦታ ሲሆን ዕድገቱ የሆነው ግን በፈረንሳዩዋ የኖንትስ ከተማ ውስጥ ነው። በቀኝ መስመር ተከላካይነት አልያም ደግሞ ወደ ቀኝ መስመር የማጥቃት ባህሪን ተላብሶ የሚጫወተው ማቲዮስ አማኑ ፒሊፕ እግር ኳስን የጀመረው በሚኖርባት ከተማ ባለችው እና በፈረንሳይ ሊግ ዋን ላይ በምናውቀው ኖንት ክለብ ውስጥ ነው።

በአሁኑ ሰዓት ሀያ አመቱን የደፈነው እና እና በኖንትስ ከ17 እና ከ19 አመት በታች እንዲሁም ከወር በፊት ከተለያየው ሄላስ ቬሮና ከ19 እና ከ20 አመት በታች ቡድን ውስጥ መጫወት ችሏል። በልጅነት ክለቡ ኖንት ከ21 አመት በታች ወይንም በሴስ ፋቭሪጋስ በሚሰለጥነው ኮሞ ከ21 አመት በታች ቡድን በቀጣይ ክረምት እንደሚቀላቀል የሚጠበቀው ይህ ተጫዋች ለተወለደባት ኢትዮጵያ መጫወትን እንደሚፈልግ ባደረኩት ቆይታ አጫውቶኛል።
አስተያየት ይስጡ