መነሻ ገጽ ሲዳማ ቡና ሊግ ካምፓኒው ሲዳማ ቡናን አስጠንቅቋል
ሲዳማ ቡናቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ

ሊግ ካምፓኒው ሲዳማ ቡናን አስጠንቅቋል

አጋራ
አጋራ

የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ካደረጉት ጨዋታ አስቀድሞ ለሊግ ካምፓኒው በጻፈው ደብዳቤ ዙሪያ የፕሪሚየር ሊጉ አክሲዮን ማህበር ሲዳማ ቡናን አስጠነቀቀ።

አክሲዮን ማህበሩ ሲዳማ ቡና የዳኛ ዕጥረት ያለ ይመስል ኢንተርናሽናል አርቢትር በአምላክ ተሰማ ሌላ ጨዋታ ካጫወተ 48 ሰአት ሳይሞላው መመደቡ ቅሬታ እንደፈጠረበት በተጨማሪም አርቢትሩ በግሉ የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊ በመሆኑ ከጨዋታው ምደባ እንዲቀየር ያቀረበውን ጥያቄ ተቀባይነት የሌለው ሲል ሊግ ካምፓኒው አጣጥሎታል።

ሊግ ካምፓኒው ለክለቡ ጥያቄ በሰጠው ምላሽ
“የዳኛ ይቀየርልን ጥያቄ በማንኛውም መስፈርት ህጋዊ አለመሆኑን ዳኛው ይቀየርልን የተባለው መረጃና ማስረጃ ሳይኖረው መሆኑ የዳኛውን ስነልቦና የሚጎዳና በህግ የሚያስጠይቅ ክለቡን ለከባድ ቅጣት የሚዳርግ ነው” ሲል አስረድቷል። በተጨማሪም “ከጨዋታው በኋላ አድልዎ አድርጎብናል የሚለው አቤቱታ የተጣሰውን የህግ አንቀጽ በመጥቀስ መክሰስ ሲገባው ባለመፈጸሙ የቀረበውን አቤቱታ አወዳዳሪው አካል አልተቀበለውም” በማለት ጥያቄያቸው ውድቅ መደረጉን ገልጿል።

ሊግ ካምፓኒው አጽንኦት ሰጥቶ በሰጠው ምላሽ ከደንብና ከመመርያ ውጪ የሚመጡ አቤቱታዎችን እንደማይቀበል ክለቡ ተመሳሳይ ድርጊት ፈጽሞ ከተገኘ አስፈላጊ የተባለውን የዲሲፕሊን ርምጃ እንደሚወስድ በመግለጽ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሲዳማ ቡናነጌሌ አርሲዜናዎችየኢትዮጵያ ዋንጫየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና አራተኛው የግማሽ ፍፃሜ ተፈላሚ ሆኗል

በኢትዮጵያ ዋንጫ የአራተኛ ቀን መርሀግብር የፕሪምየር ሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ወደ ግማሽ...

ሲዳማ ቡናዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

የሲዳማ ቡና ቡድን መሪ ታገደ

በዮሴፍ ከፈለኝ የፕሪምየር ሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና የቡድን መሪው የቀድሞው ዳኛ ዕግድ...

ሲዳማ ቡናዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ዩጋንዳዊው የሲዳማ ቡና ግብ ጠባቂ በዛሬው ጨዋታ አይሰለፍም

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና የግብ ዘብ ከዛሬ ምሽቱ ጨዋታ ውጪ ሆኗል። በትላንትናው...

ሲዳማ ቡናዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

የሲዳማ ቡናው ግብ ጠባቂ ታገደ

ዩጋንዳዊው የሲዳማ ቡና የግብ ዘብ ከማንኛውም እግር ኳስ ታግዷል። በዩጋንዳ ፕሪምየር ሊግ...