👉ፌዴሬሽኑና ሲሳይ አድርሴ ፕሮሞሽን መላ
ዘይደዋል።
ዋሊያዎቹ ለአፍሪካ ዋንጫ ፍልሚያ ወደ ካሜሩን በሚያደርጉት ጉዞ አብረው ወደ ስፍራው የሚያቀኑትን አካላት በተመለከተ ፌዴሬሽኑና ሃላፊቱን የወሰደው ሲሳይ አድርሴ ፕሮሞሽን ነገ በ 9 ሰአት በሸራተን አዲስ መግለጫ ይሰጣሉ።
ዋሊያዎቹ ወደ ውድድር ስፍራ ሲሄዱ አብረው የሚጓዙትን አካላት የጉዞ ሂደትና አጠቃላይ ጉዞውን በበላይነት የያዘው ሲሳይ አድርሴ ፕሮሞሽን በጉዳዩ ላይ ጠንካራ ዝግጅት እያደረገ ቆይቷል። ተቋሙ የልኡካን ቡድኑ በውድድሩ ስፍራ የኢትዮጵያ መልካም ገጽታን ለአለም በሚያሳይ መልኩ ለማከናወን ጥሩ ዝግጅት ሲያደርግ በመቆየቱ የጉዞው ሂደት ስኬታማ እንደሚሆን ይጠበቃል።
የተለያዩ የመንግስት ተቋማት በዚህ ዝጎጅት ላይ የራሳቸውን የሚጠበቅባቸውን ሚና ይወጣሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ከባለሀብቶች ጋር በመነጋገር 25 ጋዜጠኞችን ወጪያቸውን ችሎ ለመውሰድ መታቀዱም ታውቋል። በዚህ ጉዞ ላይ ደጋፊዎችና የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ይካተታሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በካሜሩን በቴሌቭዥን መስኮት አለም ሲመለከት ተጓዦቹ ራሱን የቻለ የአምባሳደርነት ሚና እንዲወጡ መታቀዱም ታውቋል።
አስተያየት ይስጡ