መነሻ ገጽ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ የተለያዩ ውሳኔዎች አስተላለፈ !
ቅዱስ ጊዮርጊስቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ

ቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ የተለያዩ ውሳኔዎች አስተላለፈ !

አጋራ
አጋራ

የቅዱስ ጊዮርስ ስፖርት ማህበር ስራ አመራር ቦርድ በ 2013 ዓ.ም የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ለሚሳተፈው ቡድን ከቅድመ ዝግጅት ጀምሮ በተሟላ ሁኔታ ውጤታማ እንዲሆን በሁሉም መስኮች አስፈላጊውን ሁሉ ማድረጉ ይታወሳል፡፡

ይሁን እንጂ ክለባችን ከተደረገለትና ከሚጠበቅበት ውጤታማነት አንጻር አርኪ የሚባል እንቅስቃሴዎችን እያደረገ አይደለም፡፡

የስራ አመራር ቦርዱ በቅርቡ ባደረገው ስብሰባ በቡድኑ ውስጥ ያሉ ችግሮችን በተመለከተ ሰፊና ጥልቅ ውይይት አድርጎ፣የተለያዩ የእርምት እርምጃዎች እንዲወሰዱ መመሪያዎችን ሰጥቷል፡፡

በቅርቡም የቡድኑ አልጣኝ ዳቪድስ ማሂር በቡድኑ ውስጥ ያሉ ችግሮችን በአፋጣኝ እንዲያስተካክሉ ከጅማ ወደ አዲስ አበባ በመጥራት በቦርዱ መመሪያ ተሰጥቷቸዋል፡፡

ቦርዱ በተጨማሪም የቡድኑ ቁልፍ ተጫዋች የሆነው ሳላህዲን ሰኢድ በተደጋጋሚ ጊዜ የፈጸማቸውን የዲስፕሊን ግድፈቶች በአንክሮ በማየት ወደ አዲስ አበባ እንዲመለስ አድርጓል፡፡

ሳላህዲንን ከዋናው ቡድን ጋር ለተጨማሪ ጊዜ አብሮ እንዲቆይ መፍቀድ በውድድሩ ላይ እየተፋለመ ለሚገኘው ቡድናችን ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ስለሚያመዝን ከቡድን መሪው በሥነ ምግባር ዙሪያ በዝርዝር በሚቀርበው ሪፖርት ላይ በቦርዱ ውሳኔ እስከሚገኝ ድረስ ከተስፋ ቡድን ጋር ልምምዱን እያደረገ እንዲቆይ መመሪያ መስጠቱን የክለቡ የ ፌስቡክ ገፅ አስነብቧል ፡፡

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ቅዱስ ጊዮርጊስኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየጨዋታ ዘገባ

ተጠባቂዉ የአዲስ አበባ ደርቢ በኢትዮጲያ ቡና 2ለ1 አሸናፊነት ተጠናቋል።

በአቤኔዘር አበበ ተጠባቂው 53ኛው የአዲስ አበባ ደርቢ በኢትዮጵያ ቡና 2–1 አሸናፊነት ተጠናቋል።...

ቅዱስ ጊዮርጊስነጌሌ አርሲዜናዎችየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ እና ሰጎኖቹ ነጥብ ተጋርተዋል

በአቤኔዘር አበበ በመጀመሪያ ሳምንት የሁለተኛ ቀን ውሎ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከአርሲ ነገሌ ጋር...

ቅዱስ ጊዮርጊስቅድመ ውድድር ዝግጅትዜናዎች

የክለቦች ዝግጅት | ቅዱስ ጊዮርጊስ

የ2019 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊው ቅዱስ ጊዮርጊስ የውድድር ዝግጅቱን ምን እንደሚመስል በዚህ...