የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 10ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ በዛሬው ዕለት ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ ግጥሚያ(ዎችን) ጨምሮ ሌሎች ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ሪፖርቶች ከመረመረ በኋላ የተለያዩ ውሳኔዎችን ስጥቷል።

በአስረኛው ሳምንት በተካሄዱ የ ቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ጨዋታዎች አስራ ስድስት ጎሎች ከመረብ አርፈዋል ።

የአዳማ ከተማው አብዲሳ ጀማል በዚህኛው ሳምንት ብቸኛው ሶስት ግቦችን በማስቆጠር ሀትሪክ መስራት የቻለው ተጫዋች ሆኗል ።

በአስረኛው ሳምንት ጨዋታዎች ሀያ ሰባት ተጫዋቾች የማስጠንቀቂያ ካርዶችን ሲመለከቱ በድምሩ 262 የቢጫ ካርዶች በሊጉ ላይ ታይተዋል። በአስረኛው ሳምንት ጨዋታዎች የኢትዮጵያ ቡናው ተክለማርያም ሻንቆ ፣ የሲዳማ ቡናው ፈቱዲን ጀማል እንዲሁም የአዳማ ከተማው ወጌሻ ዮሐንስ ጌታቸው የቀይ ካርድየተመለከቱ ተጫዋች ነው ።

የዲሲፕሊን ውሳኔ

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ሰኞ ጥር 24 2013 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ግጥሚያ(ዎች) ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ

1. ፈቱዲን ጀማል (ሲዳማ ቡና) ክለቡ ከ ሀዋሳ ከተማ ጋር ባደረገው የ አስረኛ ሳምንት እግር ኳስ ጨዋታ ላይ በ 76ኛ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦበታል ። ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት አንድ ጨዋታ እንዲታገድ ተወስኗል።

2. ተክለማርያም ሻንቆ (ኢትዮጵያ ቡና) ክለቡ ከ ባህርዳር ከተማ ጋር ባደረገው የ አስረኛ ሳምንት እግር ኳስ ጨዋታ ላይ በ 90+4 ኛ ደቂቃ ላይ የተጋጣሚን ቡድን ግልፅ ግብ የማግባት ዕድል በማበላሸት ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦበታል ። ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ አንድ ጨዋታ እንዲታገድ እና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 3000 /ሶስት ሺህ/ እንዲከፍል ወስኗል።

3. ዮሐንስ ጌታቸው ( አዳማ ከተማ ) ክለቡ ከ ሀዋሳ ከተማ ጋር ባደረገው ጨዋታ በፈፀመው ጥፋት ከሜዳ ስለመወገዱ ሪፖርት ቀርቦበታል ። ወጌሻው ለፈፀመው ጥፋት ሶስት ጨዋታ እንዲታገድ እና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 10,000 /አስር ሺህ / እንዲከፍል ወስኗል።

ከላይ ከተጠቀሱት ቅጣቶች በተጨማሪም ፦

ሲዳማ ቡና ክለቡ ከ ሀዋሳ ከተማ ጋር ባደረገው የ አስረኛ ሳምንት እግር ኳስ ጨዋታ የ ሲዳማ ቡና ቡድን ተጫዋች የሆኑት ያስር ሙገርዋ ፤ ሀብታሙ ገዛኸኝ ፤ ብርሀኑ አሻሞ ፣ ፈቱዲን ጀማል ፣ ጊትጋት ኩት እንዲሁም ዘራይ ሙሉ በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 65 (ሀ) መሰረት የገንዘብ ቅጣት ብር 5000 /አምስት ሺህ/ እንዲከፍል ወስኗል፡፡

አዳማ ከተማ እንደ ሲዳማ ቡና ሁሉ ታፈሰ ሰርካ ፣ በላይ አባይነህ ፣ ቴዎድሮስ ገ/እግዚአብሔር ፣ አብዲሳ ጀማል እንዲሁም ዮሐንስ ጌታቸው የማስጠንቀቂያ ካርድ መመልከታቸውን ተከትሎ የ 5,000 / አምሰት ሺህ / ብር ቅጣት ተላልፎባቸዋል ።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor