መነሻ ገጽ Uncategorized የሊጉ የ33ኛ ሳምንት ሦስት ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ተጠናቀዋል
Uncategorized

የሊጉ የ33ኛ ሳምንት ሦስት ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ተጠናቀዋል

አጋራ
አጋራ

መቻል ከሊጉ መሪ ጋር በነጥብ ዕኩል የሚሆንበትን ዕድል ከባህርዳር ከተማ ጋር አቻ በማጠናቀቁ ሳይጠቀምበት ሲቀር በተመሳይ ኢትዮጵያ መድን ከላይታ ድቻ ፣ ሀድያ ሆሳዕና ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ያለ ጎል ፈፅመዋል።

በአዲስ አበባ ስታዲየም በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን የመጀመሪያ ጨዋታ ኢትዮጵያ መድን እና ወላይታ ድቻ ተገናኝተውበት ጨዋታው ያለ ጎል መጠናቀቅ ሲችል ጨዋታው ተጠናቆ በተሰጠው ጭማሪ ደቂቃ ላይ የታየው አስቃቂ ጉዳት ግን ብዙሀኑን ያሳዘነ ነበር። 90+8ኛው ደቂቃ ላይ የወላይታ ድቻው የመስመር አጥቂ ቅዱስ ቂርቆስ በመድኑ የመሐል ተከላካይ እስማኤል አብዱልጋኒዮ ባስተናገደው ጉዳት በቀኝ እግሩ በታች አደገኛ ጉዳት በማስተናገዱ ብዙሀኑ ያሳዘነ ድርጊት የነበረ ሲሆን ለተጨማሪ ህክምና ወደ ቤተዛታ ሆስፒታል ተጉዞ ህክምና ተደርጎለት ማምሻው ወደ ሶዶ ከተማ ክርስቲያን ሆስፒታል ለተጨማሪ ህክምና አምርቷል።

ሌላኛው በአዲስ አበባ ስታዲየም በነበረው ጨዋታ ሀድያ ሆሳዕናን ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቢያገናኝም ጎል ሳይቆጠርበት 0ለ0 መጠናቀቅ ችሏል።

በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ሜዳ ላይ የአሰልጣኝ ሙሉጌታ ምህረቱ መቻል ከሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ጋር በነጥብ ዕኩል የሚሆንበትን ዕድል ከባህርዳር ከተማ ጋር ነጥብ በመጋራቱ መጠቀም ሳይችል ቀርቷል። ባህርዳሮች ገና 4ኛው ደቂቃ ላይ ከአማኑኤል ገብረሚካኤል የደረሰውን ኳስ አንተነህ ተፈራ ከመረብ አዋህዶ ቡድኑን ቀዳሚ ማድረግ ሲችል በጨዋታው ኳስን በመቆጣጠሩ የተሻሉ ይመስሉ የነበሩት መቻሎች ከዕረፍት መልስ ጨዋታው ሊጠናቀቅ ሰባት ደቂቃዎች ብቻ እየቀሩ ቸርነት ጉግሳ ላይ ሳጥን ውስጥ በተሰራ ጥፋት የተገኘችውን የፍፁም ቅጣት ምት ተከላካዩ ፈቱዲን ጀማል የፔፕ ሰይዶ መረብ ላይ በማሳረፍ ቡድኑን አቻ በማድረግ 1ለ1 በሆነ ውጤት ጨዋታው ተጠናቋል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
Uncategorized

ካሌብ በየነ ወሳኙን ግብ አስቆጥሮ ሸገር ሲቲን የድል ሦስት ነጥብ አስጨበጠ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው...

Uncategorized

“ግብ ጠባቂ ለኢትዮዽያ መምረጥ ከብዶናል” አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በመገኘት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና...

Uncategorized

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከስብስቡ አራት ተጫዋቾችን ከስብስቡ ቀንሷል።

በሀዋሳ ከተማ ዝግጅት እያደረገ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ትላንት ሶስት ተጫዋቾችን የቀነሰ...

Uncategorized

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በሰባት ስታዲየሞች ላይ ይደረጋል

ሊጉ የሚደረግባቸው ስታዲየሞች ታወቁ። የ2019 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መስከረም 30/2019 እንደሚጀመር ይታወሳል።...