በሊጉ ለመቆየት እየዳዱ የሚገኙት መቐለ 70 እንደርታዎች ረዳት አሰልጣኝ ሾመዋል።
በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ ውስጥ ለሀያ ሁለት አመታት በእግር ኳስ ተጫዋችነት በወጥነት ያገለገለው የቀድሞው ተከላካይ ገረሱ ሸመና አዲሱ የመቐለ 70 እንደርታ የአሰልጣኞች ቡድን አባል ሆኖ ተቀጥሯል። ከአርባምንጭ ከተማ ከተገኘ በኋላ ለሀዋሳ ከተማ ፣ ትራንስ ኢትዮጵያ ፣ ኒያላ ፣ ሜታ ቢራ ፣ ደቡብ ፓሊስ እና ወራቤ እንዲሁም ደግሞ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን መጫወት የቻለው ይህ የቀድሞው ተጫዋች ወደ ስልጠናው በመግባት በከፍተኛ ሊግ ክለቦች በኋላም በሀዋሳ ከተማ እና አርባምንጭ ከተማ ካሳለፈው የረዳት አሰልጣኝ ቆይታ በኋላ በሀዋሳ ከተማ አብሮ ከሰራው አሰልጣኝ ዘርአይ ሙሉ ጋር ዳግሞ ለመስራት ረዳት አሰልጣኝ ሆኖ መቐለ 70 እንደርታን ተቀላቅሏል።
ከአሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያም የነበረውን ጉዳይ አለመፍታቱን ተከትሎ እስከ አሁን አዲሱን አሰልጣኝ ዘርአይ ሙሉን በቴክኒክ ቦታው ላይ ማግኘት ያልቻለው ክለቡ ዛሬም ከሸገር ከተማ ጋር በሚያደርገው ጨዋታ አዲሱ አለቃውን አሁንም እንደማያገኝ ማረጋገጥ ችያለሁ።
አስተያየት ይስጡ