በ33ኛ ሳምንት የሊጉ የመጨረሻ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በደረጃ ሰንጠረዡ ግርጌ የሚገኘውን አርባምንጭ ከተማን 3ለ0 በመርታት ወሳኝ ነጥብን ሲያገኝ አዳማ ከወልዋሎ ፣ ነገሌ አርሲ ከምድረገነት ሽረ በተመሳሳይ ያለ ጎል ቋጭተዋል።

እጅግ ከፍ ባለ ተነሳሽነት ጨዋታውን የጀመሩት ሲዳማ ቡናዎች ከአራት ጨዋታዎች በኋላ የሊጉ ግርጌ ላይ የሚገኘውን አርባምንጭ ከተማን አስተናግዶ 3ለ0 በሆነ ውጤት መርታት ችሏል። 17ኛው ደቂቃ ላይ ከግራ የሜዳው ክፍል ከማዕዘን ምት ሬድዋን ናስር ያሻማውን ኳስ ደስታ ደሙ ገጭቶ ዘግይቶ የተነሳው መስፍን ታፈሠ በግንባር ገጭቶ መረቡ ላይ በማስቀመጥ ሲዳማ ቡናን መሪ ማድረግ ችሏል።

አዞዎቹ ሴኔጋላዊውን አማካይ ማማዱ ሴክን ሲዳማ ቡናዎች በበኩላቸው ተገፍትሮ ከአሰልጣኝ አዲሴ ካሳ ጋር በመጨረሻ ንክኪ ጉዳት ያስተናገደውን ወሳኙን አጥቂ አቤል ያለውን በጉዳት በማጣት በተለይ አቤል ለተጨማሪ ህክምና ወደ ቤተዛታ ሆስፒታል የተወሰደ ሲሆን ጨዋታውም ቀጥሎ 40ኛው ደቂቃ ላይ ሲዳማ ቡና ሁለተኛ ጎልን አግኝተዋል። የግብ ዘቡ አላዛር መርኔ ከራሱ የግብ ክልል በረጅሙ የለጋውን ኳስ በግንባር ተነካክቶ የመጨረሻውን ኳስ ብርሀኑ በቀለ በግንባር ገጭቶ አቀብሎት መስፍን ታፈሠ ለራሱ እና ለቡድኑ ሁለተኛዋን ጎል መረቡ ላይ ማሳረፍ ችሏል።
ከዕረፍት መልስም ጨዋታው ቀጥሎ አሁንም ከፍ ባለ በራስ መተማመን ወደ ሜዳ የገቡት ሲዳማ ቡናዎች 78ኛው ደቂቃ ላይ የግብ መጠናቸውን ወደ ሦስት ማሳደግ ችለዋል። መስፍን ታፈሠ ወደ ጎል የላከውን ኳስ ኤፍሬም ታምራት ለማውጣት ጥረት ሲያደርግ በራሱ መረብ ላይ በማሳረፉ በመጨረሻም ሲዳማ ቡና 3ለ0 አሸንፎ ጨዋታው ተቋጭቷል።

በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ስታዲየም አዳማ ከተማ ከወልዋሎ እንዲሁም ደግሞ ነገሌ አርሲ ከምድረገነት ሽረ ጋር በተመሳሳይ ያለ ጎል 0ለ0 መቋጨት ችለዋል።
አስተያየት ይስጡ