በሀብታሙ ምትኩ
በኦማኑ ክለብ አል ሸባብ አስደናቂ የውድድር ዘመን እያሳለፈ የሚገኘው ከነዓን ማርክነህ የኩዌቱን አል አረቢ ክለብ ለመቀላቀል ተቃርቧል።

ከነዓን የኩዌቱን ክለቡ ለመቀላቀል ስለመቃረቡ በኦማን የስፖርት ሚዲያዎች እየተዘገበ የሚገኝ ሲሆን ሲሆን የአል ሸባብ ደጋፊዎች በከነአን ከክለቡ መለያየት ቅር ተሰኝተዋል።
አዲሱ የከነዓን ክለብ አል አረቢ ለ17 ጊዜ የኩዌት ፕሪሚየር ሊግ አሸናፊ ሲሆን ያለፉትን 3 ተከታታይ አመታት 2ኛ ሆኖ አጠናቋል።
ክለቡ ከ8 ቀናት በፊት በኤዥያ ቻሌንጅ ሊግ (የኤዥያ 3ኛው እርከን የክለቦች ውድድር ማለትም እንደ አውሮፓው ኮንፈረንስ ሊግ) ሻምፒዮን ሆኗል።
በውድድሩ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታ አል ሸባብ በዚህ ክለብ(አል አረቢ) በድምር 5 ለ 3 ተሸንፎ ነበር ከውድድር ውጪ የሆነው።
በዚህ ጨዋታ ላይ ተጫዋቹ 2 ግቦችን አስቆጥሮባቸው ነበር።
ከንዓን የመጨረሻ የአል ሸባብ ጨዋታውን በመጪው ቅዳሜ የሚያደርግ ሲሆን ከባህላው ክለብ ተጫዋች አብዱልሰላም አል ሹካሊ ጋር ተመሳሳይ 18 ግቦችን አስቆጥረው ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነቱን በጥምር እየመሩ ነው።
አስተያየት ይስጡ