ሀድያ ሆሳዕና አሰልጣኙ ደካማ ውጤት በማስመዝገባቸው ከክለቡ ጋር ተለያዩ

ሀዲያ ሆሳዕና እግር ኳስ ክለብ ዋና አሰልጣኝ ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩትን አሰልጣኝ ሳምሶን አየለን ከኅዳር 17 ቀን 2019 ዓ/ም ጀምሮ ከዋና አሰልጣኝነት ኃላፊነታቸው ማንሳቱን በይፋ አሳውቋል።
ውሳኔው የክለቡ ፕሬዚዳንት አቶ ሳምሶን ወ/ጊዮርጊስ በተገኙበት የቦርድ አባላት ባደረጉት አስቸኳይ ስብሰባ የተላለፈ ሲሆን፣ ቡድኑ ባደረጋቸው አምስት ጨዋታዎች ያስመዘገበው ውጤት በክለቡ የዉስጥ ውል ስምምነት መሠረት ከተቀመጠው መስፈርት በታች መሆኑን ተከትሎ የተወሰደ እርምጃ ነው መባሉን ሀገረረ ቴሌቭዥን አውቋል።
አሰልጣኝ ሳምሶን አየለ ለሁለት አመት ለክለቡ መፈረማቸው የሚታሰወ ቢሆንም ለመሰናበት በጊዜ ተገደዋል። አሰልጣኙ በሐረ ር ቢራ ፣ ምድረገነት ሽረ ፣ ድሬዳዋ ከተማ እና ኢትዮዽያ ቡና አሰልጥነው አልፈዋል።
አስተያየት ይስጡ