መነሻ ገጽ ዜናዎች የ6ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች።
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የ6ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች።

አጋራ
አጋራ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች


1. በረከት ካሌብ (መቻል) : ክለቡ ከ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ ጋር ባደረገው የ 6 ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ በ6ዐኛ ደቂቃ ላይ ሁለተኛ ቢጫ ካርድ የሚያስጥ ጥፋት በመፈፀሙ በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦበታል ። ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 2 አንቀፅ 35(መ) መሰረት 1 እንዲታገድ የየውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።

2. ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ : ክለቡ ከባህርዳር ከተማ ጋር ባደረገው የ4 ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ የወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ ቡድን ተጫዋች የሆኑት

  • በየነ ባንጃ
  • ካርሎስ ዳምጠው
  • በረከት ሳሙኤል
  • አፈወርቅ ኃይሉ
  • ነፃነት ገ/መድህን

    በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 65 (ሀ) መሰረት የገንዘብ ቅጣት ብር 5ዐዐዐ / አምስት ሺ/
    እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል፡፡

3. ኢትዮ ኤሌትሪክ ክለቡ ከሀላባ ከተማ ጋር ባደረገው የ6 ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ የኢትዮ ኤሌትሪክ ቡድን ተጫዋች የሆኑት

  • ካሌብ ስቲፍ
  • አቤል ሀብታሙ
  • ሐብታሙ ሸዋለም
  • ብሩክ ታምራት
  • አካሉ አቲሞ

    በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 65 (ሀ) መሰረት የገንዘብ ቅጣት ብር 5000 /አምስት ሺ/
    እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል፡፡

4. ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ: ክለቡ ከፋሲል ከነማ ጋር ባደረገው የ6 ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቡድን ተጨዋች የሆኑት

  • አቤል ማሙሽ
  • በረከት አሰፋ
  • እዮብ ተስፋዬ
  • ቅዱስ ዳዊት
  • ቢኒያም ካሣሁን
  • ሄኖክ ኤርሚያስ

    በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 65 (ሀ) መሰረት የገንዘብ ቅጣት ብር 5ዐዐዐ /አምስት ሺ/
    እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል፡፡

5. ወላይታ ድቻ: ክለቡ ከ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረገው የ6ኛ ሳምንት የእግር ኳስ ጨዋታ ከሁለተኛዋ ግብ መቆጠር በኋለ ከ66ኛው ደቂቃ ጀምሮ የክለቡ ደጋፊዎች ውሀ የያዙ ፕላስቲክ ኮዳዎችን ወደ ሜዳ ሲወረውሩ እንደነበር የሚገልጽ ሪፖርት ቀርቦበታል። ስለሆነም ደጋፊዎቹ ለፈጽሙት ጥፋትና ከዚህ በፊት ተመሳሳይ ጥፋት ፈጽመው በተላለፈባቸው ቅጣት ሊታረሙ ባለመቻላቸው ክለቡ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 አንቀጽ 66 በተራ ቁጥር 3ሀ መሠረት ብር 75000/ ሰባ አምስት ሺህ/ እንዲከፍል ወስኗል፡፡

6. ኢትዮጵያ ቡና: ክለቡ ከ ወላይታ ድቻ ጋር ባደረገው የ6ኛ ሳምንት የእግር ኳስ ጨዋታ፣ የክለቡ ደጋፊዎች 2 ወንበሮች ስለመሰበራቸው ሪፖርት ቀርቦበታል። ስለሆነም ክለቡ የተሰበሩትን ወንበሮች እንዲያሠራ ወይም የስታዲየሙ ባለቤት አሠርቶ የሚያቀርበውን ወጪ እንዲከፍል ወስኗል።

7. ወላይታ ድቻ: ክለቡ ከ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረገው የ6ኛ ሳምንት የእግር ኳስ ጨዋታ፣ የክለቡ ደጋፊዎች 1 ወንበር ስለመስበራቸው ሪፖርት ቀርቦበታል። ስለሆነም ክለቡ የተሰበረውን ወንበር እንዲያሠራ ወይም የስታዲየሙ ባለቤት አሠርቶ የሚያቀርበውን ወጪ እንዲከፍል ወስኗል።

8. ነገሌ አርሲ: ክለቡ ከ ጋሞ ጨንቻ ጋር ባደረገው የ6ኛ ሳምንት የእግር ኳስ ግጥሚያ ከተወሰነለት ሰዓት በ4 ደቂቃ ዘግይቶ እንዲጀመር ምክንያት መሆኑን የሚገልጽ ሪፖርት ቀርቦበታል። ስለሆነም ክለቡ ለፈጸመው ጥፋት በ2019 በተሻሻለው የውድድር ደንብ ክፍል 1፣ አንቀጽ 13፣ ንዑስ አንቀጽ 13.2፣ በተራ ቁጥር 19 እና 20 መሠረት ብር 15000/አስራ አምስት ሺህ እንዲከፍል ወስኗል። እንዲሁም በጨዋታው መዘግየት ምክንያት የቀጥታ ስርጭት መብት የወሰደው ድርጅት ለአክሲዮን ማህበሩ ካሳ እንዲከፈለው ከጠየቀ፣ አክሲዮን ማህበሩ የሚከፍለውን ካሳ ሙሉ በሙሉ ክለቡ እንዲሸፍን ወስኗል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ባህርዳር ከተማወልዋሎዜናዎችየጨዋታ ዘገባ

ባህርዳር ከተማ እና ወልዋሎ አዲግራት ዩ. ነጥብ ተጋርተዋል

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም. የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የአራተኛ ሳምንት ተስተካካይ ጨዋታ...

ሲዳማ ቡናአዳማ ከተማዜናዎችየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና በመጨረሻ ደቂቃ ጎል አዳማ ከተማን አሸነፈ

በአቤኔዘር አበበ ሲዳማ ቡና አዳማ ከተማን 2-1 በማሸነፍ ወሳኝ ሶስት ነጥቦችን ወስዷል።...