መነሻ ገጽ ሲዳማ ቡና ሲዳማ ቡና በመጨረሻ ደቂቃ ጎል አዳማ ከተማን አሸነፈ
ሲዳማ ቡናአዳማ ከተማዜናዎችየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና በመጨረሻ ደቂቃ ጎል አዳማ ከተማን አሸነፈ

አጋራ
አጋራ

በአቤኔዘር አበበ

ሲዳማ ቡና አዳማ ከተማን 2-1 በማሸነፍ ወሳኝ ሶስት ነጥቦችን ወስዷል።

በጨዋታው የመጀመሪያ አጋማሽ አዳማ ከተማ የተሻለ የጨዋታ ብልጫ በመውሰድ ተቀስቅሷል። ሆኖም ያደረገውን የበላይነት ወደ ጎል መቀየር ተስኖት አጋማሹ ያለ ጎል ተጠናቋል። ሲዳማ ቡናም በአጋማሹ የሚጠቀስ የጎል እድል ሳይፈጥር ወደ ዕረፍት ሰዓት ገብቷል።
በሁለተኛው አጋማሽ የሁለቱም ቡድኖች የተሻለ እንቅስቃሴ በማሳየት ጥሩ ፉክክር አድርገዋል። በ78ኛው ደቂቃ ሲዳማ ቡና ያገኘውን እድል መስፍን ታፈሰ በምገባ በመጠቀም የቡድኑን የመሪነት ጎል አስቆጥሯል።አዳማ ከተማ ግን ተስፋ ሳይቆርጥ በ88ኛው ደቂቃ ከማዕዘን ምት የተሻማውን ኳስ እዮብ ማቲያስ በግንባሩ በመግጨት የአቻነት ጎል አስቆጥሮ ጨዋታውን ወደ 1-1 አድርሷል።ጨዋታው ወደ መጨረሻው ደቂቃ በተቃረበበት 90+4ኛው ደቂቃ አቤል ያለው የሲዳማ ቡናን የድል ጎል በማስቆጠር ቡድኑን ወሳኝ ሶስት ነጥቦች አስገኝቷል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ባህርዳር ከተማኢትዮጵያ መድህንዜናዎችየጨዋታ ዘገባ

ባህር ዳር ከተማ በሶስት ጎል ሶስት ነጥብ አሳካ!

በአቤኔዘር አበበ ባህር ዳር ከተማ ኢትዮጵያ መድንን 3-1 በማሸነፍ ሙሉ ሶስት ነጥብ...

ሀዋሳ ከተማሸገር ከተማኢትዮጵያ ቡናወላይታ ድቻዜናዎችየጨዋታ ዘገባ

ሸገር ከተማ እና ኢትዮጵያ ቡና በተመሳሳይ ጎል አሸነፉ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም. የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ስድስተኛ ሳምንት ሁለተኛ ቀን...

ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...