መነሻ ገጽ ዜናዎች የሁለተኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች።
ዜናዎችየዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የሁለተኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች።

አጋራ
አጋራ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች


1. ዋንጫ ቱት (ኢትዮጵያ መድን ) : ክለቡ ከ ሃዋሳ ከተማ ጋር ባደረገው የ 2 ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ በ46ኛ ደቂቃ ላይ ከባድ የአጨዋወት ጥፋት በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦበታል ።
ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3አንቀፅ 63 በተቁ 1 (ለ) እና በተቁ 2 መሰረት 3 ጨዋታ እንዲታገድ ና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር3000 /ሶስት ሺህ/ እንዲከፍል የየውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።

2. አብዱል ጋንዩ (ኢትዮጵያ መድን ) : ክለቡ ከ ሃዋሳ ከተማ ጋር ባደረገው የ 2 ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ በ85ኛ ደቂቃ ላይ ሁለተኛ ቢጫ ካርድ የሚያስጥ ጥፋት በመፈፀሙ በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦበታል ።
ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 2 አንቀፅ 35(መ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ የየውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።

3. አዲቢዬ ማርሴል (ሃዋሳ ከተማ) : ክለቡ ከ ኢትዮጵያ መድን ጋር ባደረገው የ 2 ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ በ9ኛ ደቂቃ ላይ ከግብ ክልል ውጭ ኳስ በእጅ በመያዝ በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦበታል ።
ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 63 በተቁ1 (ሀ) እና በተቁ 2 መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ ና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር3000 /ሶስት ሺህ/ እንዲከፍል የየውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።

4. በረከት ወልደዮሐንስ (ኢትዮጵያ ቡና) : ክለቡ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ባደረገው የ 2 ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ በ90+5ኛ ደቂቃ ላይ ሁለተኛ ቢጫ ካርድ የሚያስጥ ጥፋት በመፈፀሙ በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦበታል ።

ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 2 አንቀፅ 35(መ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ የየውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።

5. በፍቃዱ አለማየሁ (ኢትዮጵያ ቡና): ክለቡ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ባደረገው የ 2 ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ በ9ዐ+6ኛ ደቂቃ ላይ የተጋጣሚን ተጫዋች በመማታት በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦበታል ።
ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 63 በተቁ 1 (ሠ) እና በተቁ 2 መሰረት 4 ጨዋታ እንዲታገድ ና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 3000 /ሶስት ሺህ/ እንዲከፍል የየውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።

6. ያሬድ የማነ (ቅዱስ ጊዮርጊስ) : ክለቡ ከ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረገው የ 2 ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ በ9ዐ+6ኛ ደቂቃ ላይ የተጋጣሚን ተጫዋች በመማታት በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦበታል ።
ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 63 በተቁ 1 (ሠ) እና በተቁ 2 መሰረት 4 ጨዋታ እንዲታገድ ና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር3000 /ሶስት ሺህ/ እንዲከፍል የየውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።

7 ኢትዮጵያ ቡና ክለቡ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ባደረገው የ2 ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ የኢትዮጵያ ቡና ቡድን ተጫዋች የሆኑት
1 ድልአዲስ ገብሬ
2በረከት ወልደዮሐንስ
3 አብዱሰላም ዩሱፍ
4 በረከት ወልደዮሐንስ
5 በፍቃዱ አለማየሁ

በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 65 (ሀ) መሰረት የገንዘብ ቅጣት ብር 5000 /አምስት ሺ/
እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል፡፡

8. ኢትዮጵያ መድን :ክለቡ ከሃዋሳ ከተማ ጋር ባደረገው የ2 ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ የኢትዮጵያ መድን ቡድን ተጫዋች የሆኑት
1 አብዱል ጋንዩ
2ዋንጫ ቱት
3ወሊድ ኡስማን
4ወገኔ ገዛኸኝ
5 አብዱል ጋንዩ

በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 65 (ሀ) መሰረት የገንዘብ ቅጣት ብር 5000 / አምስት ሺ/
እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል፡፡

9. ሀዲያ ሆሳዕና : ክለቡ ከ ወላይታ ድቻ ጋር ባደረገው የ2ኛ ሳምንት የእግር ኳስ ጨዋታ ወቅት የቡድን ፎቶ አነሳስ ደንብን መጣሱን የሚገልጽ ሪፖርት ቀርቦበታል። ስለሆነም ክለቡ ለፈጸመው ጥፋት ክለቡ በ2019 በተሻሻለው የውድድር ደንብ ክፍል 1፣ አንቀጽ 13፣ ንዑስ አንቀጽ 13.2፣ በተራ ቁጥር 17 መሠረት ብር 5000/ አምስት ሺህ/ እንዲከፍል ወስኗል።

10. ቅዱስ ጊዮርጊስ: ክለቡ ከ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረገው የ2ኛ ሳምንት የእግር ኳስ ጨዋታ፣ የክለቡ ደጋፊዎች 12 ወንበሮች ስለመነቀላቸው እንዲሁም 6 ወንበሮችን ስለመሰበራቸው ሪፖርት ቀርቦበታል። ስለሆነም ክለቡ በአጠቃላይ የተነቀሉትንና የተሰበሩትን 18 ወንበሮች እንዲያሠራ ወይም የስታዲየሙ | ባለቤት አሠርቶ የሚያቀርበውን ወጪ እንዲከፍል ወስኗል።

11. ኢትዮጵያ ቡና ክለቡ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ባደረገው የ2ኛ ሳምንት የእግር ኳስ ጨዋታ፣ የክለቡ ደጋፊዎች 10 ወንበሮች ስለመነቀላቸው እንዲሁም 4 ወንበሮችን ስለመሰበራቸው ሪፖርት ቀርቦበታል። ስለሆነም ክለቡ _ በአጠቃላይ የተነቀሉትንና የተሰበሩትን 14 ወንበሮች እንዲያሠራ ወይም የስታዲየሙ ባለቤት አሠርቶ የሚያቀርበውን ወጪ እንዲከፍል ወስኗል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...